Wednesday, April 17, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ለሦስት ነባር የባንክ ባለሙያዎች ዕውቅና ተሰጠ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር ለበርካታ ዓመታት ያገለገሉና፣ ከግል ባንኮችም ትልልቆቹን ሦስት ባንኮች በፕሬዚዳንትነት ለመሩ ባለሙያዎች ዕውቅና ሰጠ። በባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምሥጋና በማቅረብ፣ ማኅበሩ ዕውቅና የሰጣቸው ለአቢሲኒያ፣ ለወጋገንና ለንብ ባንኮች የቀድሞ ፕሬዚዳንቶች ናቸው። ሐሙስ የካቲት 21 ቀን 2011 .. በሒልተን ሆቴል በተዘጋጀ ፕሮግራም፣ በማኅበሩ ዕውቅናና ሽልማት የተሰጣቸው የአቢሲኒያ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ አስማረ፣ የወጋገን ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ገብረ እግዚአብሔር አርዓያና የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ክብሩ ፎንዣ ናቸው። ለማኅበሩም ለግል ባንኮችም የነበራቸውን አበርክቶ በማስታወስ ለተሰናባቾቹ ፕሬዚዳንቶች ዕውቅናውና ሽልማቱን የሰጡት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (/) ነበሩ። በየባንኮቹ በተካሄዱ የለውጥ እንቅስቃሴዎች ኃላፊነታቸውን ከሁለት ወራት ወዲህ የለቀቁት ሦስቱ የባንክ ባለሙያዎች በአገሪቱ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ በርካታ ዓመታት ያገለገሉ ስለመሆናቸው ተጠቅሷል። እንዲህ ዓይነቱ የዕውቅና ፕሮግራም ከዚህ ቀደምም በማኅበሩ በኩል ማካሄዱን የጠቀሱት የማኅበሩ ፕሬዚዳንት አቶ አዲሱ ሃባ፣ ለኢንዱስትሪው ባበረከቱት አስተዋጽኦ መመስገን አለባቸው ብለዋል። የቀድሞዎቹ ኃላፊዎች በአዳዲስ ፕሬዚዳንቶች የተተኩ ሲሆን፣ የአቢሲኒያ ባንክ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ አስማረን የቀድሞው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ በቀሉ ዘለቀ እንዲተኳቸው መደረጉ ይታወሳል። ወጋገን ባንክን ከአሥር ዓመታት በኋላ በፕሬዚዳንትነት ያገለገሉት አቶ ገብረ እግዚአብሔርን ተክተው እንዲሠሩ በወጋገን ባንክ የተሾሙት የቀድሞ የንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ዳባይ መሐሪ ናቸው። የንብ ኢንተርናሽናል ባንክም አቶ ክብሩ ኃላፊነታቸውን ለምክትላቸው አቶ ገነነው ሩጋ በማስረከብ ከፕሬዚዳንትነታቸው የለቀቁ ናቸው። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአገሪቱ ባንኮች አዲሱን የኦዲት ሪፖርት አቀራረብና አተገባበር ዕውን እንዲሆንና ሁሉም ባንኮች እንዲጠቀሙበት በማስቻል አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለሙያዎችም በተመሳሳይ ዕውቅና ሰጥቷል።

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች