ቀንድ አውጣዎች በአብዛኛው አትክልታማ ቦታ የሚገኙ ቢሆንም፣ አመጋገባቸው ተክል ላይ ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ አንዳንዶቹ ተክልና ሥጋን ሲመገቡ አንዳንዶቹ ተክል ብቻ ተመጋቢ ናቸው፡፡
ፀሐያማ በሆኑ ከተሞች በሚገኙ የአትክልት፣ ገጠራማ አካባቢ በሚገኙ ቀዝቃዛ ተራራማ ሥፍራዎችና በተለያየ የአየር ንብረት ውስጥ ይኖራሉ፡፡
በሺዎች የሚቆጠር ዝርያ ያላቸው ቀንድ አውጣዎች፣ በመሬትና በውኃ ውስጥ መኖር ይችላሉ፡፡ ለአፍሪካ ብርቅዬ የሚባለው ትልቁ የአፍሪካ ቀንድ አውጣ እስከ 20 ሴንቲ ሜትር ይረዝማል፡፡ በጓሮ አትክልቶች ውስጥ በብዛት የሚኖረው ቀንድ አውጣ፣ 1.3 ኢንች የሚረዝም ሲሆን፣ በአብዛኛው የሚገኘው በሜድትራኒያን፣ በምዕራብ አውሮፓ፣ በእስያና በሰሜናዊ ግብፅ ነው፡፡
- ፎቶ ክሬዲት ሻተር ስቶክ