Sunday, May 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናየአማራና የትግራይ ክልል መንግሥታት በመካከላቸው ለጠፋው ሰላም በተጠያቂነት ተወነጃጀሉ

የአማራና የትግራይ ክልል መንግሥታት በመካከላቸው ለጠፋው ሰላም በተጠያቂነት ተወነጃጀሉ

ቀን:

ሰሞኑን መደበኛ ስብሰባውን ያካሄደው የአማራ ክልል ምክር ቤትአማራና በትግራይ ወንድማማች ሕዝቦች መካከል ልዩነት እንዲፈጠርና ወደ ጦርነት እንዲገቡ ለማድረግ የፀብ አጫሪነት ተግባር በትግራይ ክልል እየተፈጸመበት መሆኑን ሲገልጽ፣ የትግራይ ክልል በበኩሉ የተሰነዘረበትን ወቀሳ በማስተባበል የጦርነት አታሞ እየተጎሰመ ያለው በእሱ ወገን እንዳልሆነ ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት ጉባዔን አስመልክቶ ረቡዕ የካቲት 27 ቀን መግለጫ የሰጡት  የክልሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማኸኝ አስረስ፣ ከትግራይ ክልል ጋር እየተፈጠረ ያለውን የፀጥታ ሁኔታ ምክር ቤቱ  በዝርዝር ገምግሟል ብለዋል፡፡

ሁለቱ ሕዝቦች በታሪክ፣ በባህል፣ በሃይማኖትና አገርን በመገንባት ዘመን ተሻጋሪ ታሪክ እንዳላቸው ምክር ቤቱ መገምገሙን አቶ አሰማኸኝ አመላክተዋል፡፡  በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ምንም ዓይነት ልዩነት፣ ፀብም ሆነ መቃቃር እንደሌለና አብረው የኖሩና የሚኖሩ መሆናቸውን ምክር ቤቱ በአጽንኦት መገምገሙንም አስታውቀዋል፡፡

- Advertisement -

ሁለቱ ሕዝቦች ጥረው ግረውና ለፍተው የሚያድሩ፣ ዘመን ተሻጋሪ ግንኙነታቸው ወደፊትም  የሚዘልቅ መሆኑን  እምነት እንዳለው ምክር ቤቱ አቅጣጫ ማስቀመጡን ጠቁመዋል።

በትግራይ ክልል አመራሮች በኩል የጦርነት ቅስቀሳዎች፣ ሰፊ ወታደራዊ ዝግጅት፣ ወደ አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ሠራዊት የማቅረብና አንዳንድ ፀብ አጫሪ አካሄዶች በመኖራቸው በአስቸኳይ እንዲቆሙ፣ አመራሮቹም ከዚህ ድርጊታቸውም እንዲታቀቡ ምክር ቤቱ ማሳሰቡን ገልጸዋል፡፡

በትግራይ ክልል የመሸገው፣ በተለይ በለውጡ የተገፋው፣ ሥልጣኑን ያጣውና ዘራፊው ቡድን፣ ጦርነት ለመቀስቀስ ቢፈልግ እንኳ ሰላም ወዳዱ የትግራይ ሕዝብ ዝም ብሎ ይመለከተዋል የሚል እምነት እንደሌለው የምክር ቤቱ እምነት መሆኑን ገልጸዋል፡፡  

ከእርስ በርስ ጦርነት ኪሳራ እንጂ ትርፍ የለም ያለው ምክር ቤቱ፣ የትግራይ ሕዝብ ለመሸጉትና ሕዝብን መከታ አድርገው ለሚንቀሳቀሱት ጥሪና ትንኮሳ ምንም ዓይነት መልስ ባለመስጠት ሰላም ወዳድነቱን በተግባር እንዲያስመሰክር ምክር ቤቱ ማሳሰቡን አቶ አሰማኸኝ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

በአማራ ክልል በኩልም ግጭት ከሚፈጥሩ ትንኮሳዎችና የትግራይ ሕዝብን ሥጋት ላይ ከሚጥሉ ፀብ አጫሪ ንግግሮች ማንኛውም አካል እንዲቆጠብ፣ እንዲህ ዓይነት ንግግሮች ለሰላም ፈላጊው የአማራ ሕዝብ እንደማይመጥኑትና ይኼንን በሚያደርጉ አካላት ላይ የእርምት ዕርምጃ እንዲወሰድ ምክር ቤቱ መወሰንም ተናግረዋል፡፡

የትግራይ ክልል የሕዝብ ግንኙነትና የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሐሙስ የካቲት 28 ቀን 2011 ዓ.ም. ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት የሰነዘረበትን ወቀሳ አስተባብሏል።

‹‹የአማራ ክልል የፀጥታ ጉዳዮችን አስመልክቶ በትግራይ ክልል መንግሥትና ሕዝብ ላይ አስተላልፎታል የተባለው ውሳኔ ለአማራም ሆነ ለትግራይ ሕዝብ ስለማይበጅ፣ ጉዳዩን ዳግም እንዲያጤነው የትግራይ ሕዝብና መንግሥት ጥሪያቸውን ያቀርባሉ፤›› ሲል ጠይቋል፡፡

መግለጫው በትግራይ ላይ የተሰነዘረውን ወቀሳ በማጣጣል በግላጭ ትንኮሳና የጦርነት አታሞ ሲጎስም የከረመው ከየትኛው ወገን እንደሆነ ጥያቄ ቢነሳ፣ ምላሹን ሰላም ወዳድ ዜጎች ምስክርነት ሊሰጡበት እንደሚችሉ ይገልጻል፡፡

‹‹ሽፍቶችን ጨምሮ የተለያዩ ፀረ ሰላምና ፀረ ልማት ኃይሎች የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን ተጠቅመው፣ ላለፉት ሦስት ዓመታት ያለ እረፍት ቀንና ለሊት የጦርነት ቅስቀሳና ትንኮሳ ከማካሄድ አልፎው፣ በትግራይ ወሰኖች ሄድ መለስ ሲሉ ቆይተዋል፤›› የሚለው የትግራይ ክልል መግለጫ፣ ‹‹የትግራይ ክልል ተወላጆች ብቻ በመሆናቸው በአማራ ክልል የተለያዩ ቦታዎች በድንጋይ ተቀጥቅጠው ሲገደሉ፣ 50 ሺሕ በላይ ዜጎች ጥረው ግረው ያፈሩት ሀብትና ንብረታቸው ተዘርፈውና እትብታቸው ከተቀበረበት ቀዬ ሲፈናቀሉ፣ እንዲሁም የአማራና የትግራይ ሕዝብ እንዳይገናኝ አውራ መንገዶችን ዘግቶ ባይሳከለትም የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት እንዲሻክር የተፍጨረጨረው ፀረ ሰላምና ፀረ ልማት ኃይሉን ታሪክ ይቅር የማይለው በደልና ክህደት በትግራይ ላይ ፈጽሟል፤›› ሲል የአጸፋ ወቀሳውን ሰንዝሯል፡፡

የትግራይ ሕዝብና መንግሥት 17 ዓመታት የትጥቅ ትግል ወቅት ወታደራዊን ደርግ ለመደምሰስ በተደረገው መራራ ትግል፣ የአማራ ሕዝብ ከወንድሙ የትግራይ ሕዝብ ጎን ተሠልፎ ተገቢው መስዋዕትነት መክፈሉን እንደማይዘነጋ አስረድቷል፡፡ በመሆኑም የትግራይ ሕዝብና መንግሥት የታገሉለትን ሕዝባዊ መስመር አንግበው ወደፊት ከመገስገስ ውጪ፣ ወንድም በሆነው የአማራ ሕዝብ ላይ አፈሙዝ የሚያዞሩበት አንዳች ምክንያት እንደሌላቸው አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች መከፈት አገር በቀል ባንኮችን ለምን አስፈራቸው?

የማይረጥቡ ዓሳዎች የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ሙግት ሲሞገት! - በአመሐ...

የምርጫ 97 ትውስታ!

በበቀለ ሹሜ      መሰናዶ ኢሕአዴግ ተሰነጣጥቆ ከመወገድ ከተረፈ በኋላ፣ አገዛዙን ከማሻሻልና...

ሸማቾች የሚሰቃዩት በዋጋ ንረት ብቻ አይደለም!

የሸማች ችግር ብዙ ነው፡፡ ሸማቾች የሚፈተኑት ባልተገባ የዋጋ ጭማሪ...

መንግሥት ከለጋሽ አካላት ሀብት ለማግኘት የጀመረውን ድርድር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርላማው አሳሰበ

የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል አዲስ አበባ...