ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኰንን፣ በባሕር ዳር ከተማ በአዲሱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አምባቸው ከበደ (ዶ/ር) በዓለ ሲመት ላይ ባለፈው ሳምንት የተናገሩት።
የከተማዋ ዕድገት ማንንም ሳይጋፋና ማንንም ሳይጎዳ ሁሉንም ሊጠቅም በሚችል መልኩ መሆን ይገባዋል ያሉት አቶ ደመቀ፣ በከተማዋ ማደግና መስፋፋት ምክንያት ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎችን በዝርዝር አጥንቶ በዘላቂነት እንዲቋቋሙ ማድረግ የሁሉም ኃላፊነትና ግዴታ መሆኑን ሳይጠቁሙ አላለፉም፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው፣
ከተማዋ ማንም የተለየ ባለቤትነት ስሜት እንደፈለገ የሚያንፀባርቅበት፤ አንዱን ባለቤት ሌላውን ባይተዋር የሚያደርግበት መሆን የለበትም፡፡ ከዚህ ጋር የሚነሱ ጉዳዮች ካሉ ሕጎችን መሠረት አድርጎ በጋራ ተወያይቶ መፍታት ይገባል፡፡