ጥሬ ዕቃዎች
- 1/2 ኪሎ ግራም ስኳር
- 1 ከሩብ ኪሎ ግራም የፉርኖ ዱቄት
- 12 ዕንቁላል
- 3 የሾርባ ማንኪያ ቤኪንግ ፓውደር
- 1 ሊትር ዘይት
አዘገጃጀት
- ጥሬ ዕቃዎቹን በሙሉ ደባልቆና አሽቶ በፕላስቲክ ሸፍኖ ለሃያ ደቂቃ ማስቀመጥ፤
- በቀጭኑ ረዘም አድርጎ ማድበልበልና በ8 ቁጥር ቅርፅ ወይም እንደገመድ መቋጠር፤
- ዘይቱን አግሎ የተድበለበለውን ወርቃማ ቡና መልክ እስኪያወጣ እያገላበጡ ጠብሶ ማውጣት፤
- የኬክ መጠቅለያ ወረቀት ላይ ማድረግ፤
- ሲቀዘቅዝ መጠቀም፡፡
በዚህ መልክ የተዘጋጀ ብስኩት ታሽጐ እስከ አሥር ቀን ሊቆይ ይችላል፡፡
- ደብረወርቅ አባተ (ሱ ሼፍ) ‹‹የውጭ ምግቦች አዘገጃጀት›› (2002)