የኢትዮጵያ ቦይንግ 737-800 ማክስ አውሮፕላን 149 መንገደኞችን አሳፍሮ ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ያቀናው ባለፈው እሑድ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ነበር፡፡ ከጠዋቱ 2፡38 ሰዓት ላይ ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተነስቶ ለስድስት ደቂቃ ያህል ከበረረ በኋላ በመከስከሱ፣ የአውሮፕላኑ ስብርባሪ በቢሾፍቱና ሞጆ ከተሞች መካከል ኤጄሬ የተባለ አካባቢ ተገኝቷል፡፡ ሁሉም ተሳፋሪ በአደጋው የሞት ሰለባ ሆኗል፡፡ ፎቶዎቹ የአደጋውን ሥፍራ፣ የአስክሬንና የስብርባሪ ፍለጋ ዘመቻውን በከፊል ያሳያሉ፡፡