Sunday, April 14, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ኒያላ ኢንሹራንስ ለዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ አሥር ሚሊዮን ብር በላይ ካሳ ሊከፍል ነው

ተዛማጅ ፅሁፎች

የግዙፉ የሲሚንቶ ፋብሪካ ማሽነሪ ላይ በደረሰበት አደጋና ከዚሁ ጋር በተያያዘ ለተፈጠረው የቢዝነስ መቋረጥ ጉዳት ኒያላ ኢንሹራንስ 10.7 ሚሊዮን ብር ካሳ ሊከፍል መሆኑ ተገለጸ፡፡

ኒያላ ኢንሹራንስ ይህንን የጉዳት ካሳ ክፍያ የሚከፍለው ከዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ጋር በገባው ውል መሠረት ነው፡፡ በዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ውስጥ ለምርት እንቅስቃሴ ዋነኛ ሚና ነበረው የተባለው ማሽነሪ መጎዳትና ከዚሁ ጋር ተያይዞ ለተፈጠረው የቢዝነስ መቋረጥ ፋብሪካው ከኒያላ ኢንሹራንስ ጋር በገባው የመድን ሽፋን ውል መጠን መሠረት የ10.7 ሚሊዮን ብር የጉዳት ካሳ ሊከፈለው መሆኑ ታውቋል፡፡ በግል ኢንሹራንስ ኢንዱስትሪው ውስጥ ከፍተኛ የተባለውን ይህንን የጉዳት ካሳ ዛሬ መጋቢት 11 ቀን 2011 ዓ.ም. እንደሚከፍል ከኒያላ ኢንሹራንስ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡

ኒያላ ኢንሹራንስ በኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከ23 ዓመታት በላይ የዘለቀ ሲሆን፣ ለዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ የሚከፈለው የጉዳት ካሳ እስካሁን ከከፈላቸው ከፍተኛ ከሚባሉት ጥቂት የጉዳት ካሳዎች ውስጥ አንዱ በመሆን የሚጠቀስ ነው፡፡ ማሽነሪዎቹን ለመተካትና ለደረሰበት የቢዝነስ መቋረጥ ጉዳት ካሳ የሚከፈለው ዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ከ600 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የተገነባ ፋብሪካ ሲሆን፣ በዓመት 2.5 ሚሊዮን ቶን የማምረት አቅም ያለው ፋብሪካ ነው፡፡

ኒያላ ኢንሹራንስ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ የግል የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በገበያ ድርሻው የመጀመርያውን ደረጃ የሚይዝ ሲሆን፣ በዓመታዊ የትርፍ መጠኑም ቀዳሚውን ደረጃ መያዙ ይታወቃል፡፡

ወደ ሁለት ቢሊዮን ብር የሚገመት የሀብት መጠን ያለው ኒያላ ኢንሹራንስ፣ በ2010 የሒሳብ ዓመት የሰብሰበው የዓረቦን መጠን 769.4 ሚሊዮን ብር ሲሆን፣ ይህ የዓረቦን መጠን ከግል ኩባንያዎች አንፃር ሲታይ ከፍተኛው ነው፡፡

በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት ኩባንያው ለሕይወትና ሕይወት ነክ ላልሆኑ የመድን ሽፋን በጠቅላላው ለጉዳት ከፍሎ የነበረው አጠቃላይ የካሳ መጠን 163.5 ሚሊዮን ብር እንደነበር መግለጹ አይዘነጋም፡፡   

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች