አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
- 10 ትላልቅ ቃርያ
- ሩብ ሊትር ዘይት
- 2 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) በጣም የደቀቀ ቀይ ሽንኩርት
- 2 የሾርባ ማንኪያ በጣም የደቀቀ ነጭ ሽንኩርት
- 6 የሾርባ ማንኪያ (100 ሚሊ ሊትር) ውሃ
- 3 የቡና ስኒ (150 ግራም) የፉርኖ ዱቄት
- 1 መካከለኛ ጭልፋ (150 ግራም) ፍሬው ወጥቶ በጣም የደቀቀ ቲማቲም
- 2 የሻይ ማንኪያ ጨው
- 2 የሻይ ማንኪያ ነጭ ቅመም
አዘገጃጀት
- አምስት የሾርባ ማንኪያ ዘይት ጥዶ ሞቅ ማድረግ፤
- ነጭ ሽንኩርቱን፣ ቀይ ሽንኩርቱንና ቲማቲሙን ጨምሮ ለብለብ ማድረግ፣
- ጨው ጨምሮ ማውጣት፤
- ቃርያውን ሰንጥቆ በተዘጋጀው ቁሌት መሠነግ፤
- የፉርኖ ዱቄቱ ላይ ነጭ ቅመም ጨምሮ በውሃ ማሸት፤
- በጠርሙስ እየዳመጡ በስሱ መጠፍጠፍ፤
- የተሰነገውን ቃርያ መያዣ አስቀርቶ በሊጡ መጠቅለል፤
- በቀረው ዘይት አግሎ መጥበስ፤
- በትኩሱ ለገበታ ማቅረብ፡፡
- ደብረወርቅ አባተ (ሱ ሼፍ) ‹‹ባህላዊ ምግቦች አዘገጃጀት›› (2003)