Thursday, March 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየአፄ ቴዎድሮስ ቁንዳላ በማኅበረ ሥላሴ ገዳም እስከሚቀበር በ‹‹ብሔራዊ ሙዚየም›› ይቆያል

የአፄ ቴዎድሮስ ቁንዳላ በማኅበረ ሥላሴ ገዳም እስከሚቀበር በ‹‹ብሔራዊ ሙዚየም›› ይቆያል

ቀን:

ለዘጠኝ አሠርታት ግድም በመሳፍንት ተከፋፍላ የነበረችው ኢትዮጵያ አንድነቷን እውን ያደረጉት ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ናቸው፡፡

የዘመናዊ ኢትዮጵያ ታሪክ በ19ኛው ዓመት የተጀመረውም አባ ታጠቅ በሚባለው የፈረስ ስማቸው በሚታወቁት በኚሁ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ቴዎድሮስ ዘመን መሆኑ ይወሳል፡፡

ዳግማዊ ቴዎድሮስ የአሥራ ሦስት ዓመት የንግሥና ዘመናቸው (1847-1860) ያበቃው በመቅደላ አምባ ከእንግሊዝ ሠራዊት ጋር በነበረው ጦርነት ፍጻሜ ላይ ‹‹እጄን አልሰጥም›› ብለው ራሳቸውን በጀግንነት ባጠፉበት ቅፅበት ነበር፡፡ በጄኔራል ናፒር ይመራ የነበረው ጦር የመቅደላ አምባን ሲወር ከዘረፋቸው ቅርሶች በተጨማሪ ከንጉሠ ነገሥቱ አስክሬን ላይ ቁንዳላቸውን (ጉንጉን ፀጉራቸውን) ቆርጦ መውሰዱ ይታወቃል፡፡

የታሪክ ሰነዶች እንደሚያሳዩት፣ ሁለት ቁንዳላን ቆርጦ የወሰደው መቶ አለቃ ፍራንክ ጀምስ ነው፡፡ ጀምስ ሠዓሊም በመሆኑ በቃሬዛ ላይ የነበሩትን የአፄ ቴዎድሮስን ገጽታ በንድፍ በሚሥልበት ወቅት ነበር ቆርጦ የወሰደው፡፡ የጀምስ ቤተሰብ ሁለቱን ቁንዳላዎች ከ100 ዓመት በኋላ እ.ኤ.አ. በ1959 ለብሔራዊ የጦር ሙዚየም ሰጥቷል፡፡

በለንደን ከተማ ብሔራዊ ጦር ሙዚየም ለስድሳ ዓመታት የተቀመጠውን ሁለት ቁንዳላ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ፈቃደኛነቱን ያሳየው ሙዚየሙ መጋቢት 11 ቀን 2011 ዓ.ም. ቁንዳላዎቹን ለባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሒሩት ካሳው (ዶ/ር) አስረክቧል፡፡

ዘ አርት ኒውስፔፐር እንደዘገበው፣ በትንሽ ሳጥን ውስጥ ሆኖና የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የለበሰውን ቁንዳላውን የሙዚየሙ ዳይሬክተር ጀስቲን ማክጂውስኪ ለሚኒስትር ሒሩት ካሰው (ዶ/ር) አስረክበዋል፡፡

ሁለቱን ቁንዳላዎችን የያዘው ሳጥን ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን አዲስ አበባ እንደሚደርስ፣ ለዕይታ እንደማይበቃና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም በጥብቅ ስፍራ እንደሚቆይ የሙዚየሙ ዳይሬክተር አቶ ኤፍሬም አማረ ለዘአርት ኒውስፔፐር ገልጸዋል፡፡ ከጥቂት ሳምንታት ቆይታ በኋላ በሰሜን ኢትዮጵያ ቋራ በሚገኘው ማኅበረ ሥላሴ ገዳም የቁንዳላዎቹ ሥርዓተ ቀብር እንደሚፈጸምም አቶ ኤፍሬምን ጠቅሶ ድረ ገጹ ዘግቧል፡፡

በብሔራዊ የጦር ሙዚየም በነበረው ሥነ ሥርዓት ላይ ዲስኩር ያሰሙት በለንደን የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍሥሐ ሻውል፣ በመቅደላ ጦርነት በእንግሊዝ ወታደሮች የተዘረፉት ቅርሶች እንዲመለሱም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በእንግሊዝ በጥቂቱ 1,500 ቅርሶች የብሪቲሽ ሙዚየም፣ የቪክቶሪያ ኤንድ አልበርት ሙዚየም እና የብሪቲሽ ላይብረሪን ጨምሮ እንደሚገኙም አመልክተዋል፡፡

በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ከተገኙት መካከል በለንደን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ጎርጎርዮስ ይገኙበታል፡፡

በሌላ በኩል ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ማኅበራዊ ገጽ የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው፣ የኢትዮጵያ የልኡካን ቡድን በለንደን የብሪቲሽ  ሙዚየምን በጎበኘበት ወቅት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሒሩት ካሳው (ዶ/ር)በሙዚየሙ የሚገኙ ጽላቶች ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ምዕመናን ልዩ ክብርና ቦታ ያላቸው፣ ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙባቸው ሕያው በመሆናቸው ወደ ትክክለኛ ቦታቸው እንዲመለሱ ጠይቀዋል። የሙዚየሙ ኃላፊዎች በበኩላቸው ሐሳቡን እንደሚጋሩትና የሕግ ጉዳይ ሆኖ መወሰን ባይችሉም፣ በመጪው ሐምሌ  በሚኖረው ስብሰባ ለአገሪቱ ሙዚየም ባለአደራ ቦርድ አቅርበው ምላሽ እንደሚሰጡ ገልጸዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...

አይ የእኛ ነገር!

የዛሬው ጉዞ ከጀሞ ወደ ፒያሳ ነው፡፡ መንገዱ ለሥራ በሚጣደፉ፣...

የዓለም ኢኮኖሚ መናጋት ለወቅታዊው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ነው?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ባለፈው ማክሰኞ መጋቢት 16...