Saturday, December 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ የሲስኮ ፕሮግራም በሙያ ተቋማት መስጠት ተጀመረ

 የሲስኮ ፕሮግራም በሙያ ተቋማት መስጠት ተጀመረ

ቀን:

በመሠረታዊ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ የኮምፒዩተር ጥገና፣ ሳይበር ሴክዩሪቲ፣ ኔትወርኪንግና በመሳሰሉት ሥልጠና የሚሰጥበት የሲስኮ ፕሮግራም ከዩኒቨርሲቲ ባለፈ በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ማሠልጠኛ ተቋማት መስጠት ተጀምሯል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሰጥም እንቅስቃሴ መጀመሩን በጅማ ዩኒቨርሲቲ የአይሲቲ ዳይሬክተርና የሲስኮ አካዴሚ ተወካይ ግሩም ከተማ (ዶ/ር) ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ሲስኮ የሚሰጣቸው ፕሮግራሞች በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ማሠልጠኛ ተቋማትም እንዲሰጥ ለማድረግ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ስምምነት ተፈራርመው እንደነበርም ዶ/ር ግሩም ገልጸዋል፡፡ በዚያ መሠረትም ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከ13 ተቋማት የተወጣጡ 26 መምህራንን አሠልጥኖ ወደ ሥራ እንዲገቡ ማድረጉን፣ ነገር ግን በአጥጋቢ ሁኔታ መተግበር አለመቻሉን አስረድተዋል፡፡ ፕሮግራሙን በስፋት ለማስተግበር የኔትወርክ መሠረት ልማት ደካማ የግንዛቤ ችግር ተግባራዊነቱን ወደ ኋላ ጎትቶታል ብለዋል ዶክተሩ፡፡ በክልሎች እንዲስፋፋም ከክልል ትምህርት ቢሮዎች ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በኢትዮጵያና በሶማሊያ የሚተገበረውን የሲስኮ ፕሮግራም የሚያስተባብረው ጅማ ዩኒቨርሲቲ የሲስኮ ፕሮግራም በጂቡቲና በኤርትራ ለማስጀመር ዕቅድ እንዳለውም ዶ/ር ግሩም ገልጸዋል፡፡ በምሥራቅ አፍሪካ በኢትዮጵያና በኬንያ የሚገኘውን ፕሮግራም የሚመራው መቀመጫውን በኬንያ ያደረገ የሲስኮ ቡድን ሲሆን፣ በጂቡቲና በኤርትራ እንደሚጀመሩ የሚጠበቁትን ፕሮግራሞች የሚያስተባብረው ጅማ ዩኒቨርሲቲ ነው፡፡ 

እንደ ዶ/ር ግሩም ገለጻ፣ በኤርትራ ይጀመራል የተባለው ፕሮግራም ገና በዕቅድ ደረጃ ሲሆን፣ በጂቡቲ እንዲጀመር ግን ተቀማጭነቱን በኬንያ ያደረገው የሲስኮ ቡድን ከሚመለከታቸው ጋር ውይይት ማድረግ ጀምሯል፡፡ ዩኒቨርሲቲው የሲስኮ ፕሮግራም አስተባባሪ ሆኖ ሲሠራ የማሠልጠኛ ማዕከላትን የመክፈት፣ ለመምህራን ሥልጠና የመስጠት እንዲሁም ለሚያጋጥሙ ችግሮች መፍትሔ የመስጠት ኃላፊነት ይኖርበታል፡፡ በጂቡቲ ለሚከፈተው ማሠልጠኛ መምህራን የማሠልጠን ኃላፊነቱ ግን ፈረንሣይኛ ቋንቋ ለሚናገሩ ከሴኔጋል ለሚመደቡ መምህራን መተዉን ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡ ከዚያ ውጭ ያሉ ማናቸውምንም ዓይነት ድጋፎች የሚያገኙት ግን ከጅማ ዩኒቨርሲቲ እንደሚሆን ታውቋል፡፡

ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ መተግበር የጀመረው በ1998 ዓ.ም. ሲሆን፣ እስካሁን በሺዎች የሚቆጠሩ ተመርቀዋል፡፡ ጅማ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ እስካሁን 13 ሺ ተማሪዎች ማስመረቁን ተወካዩ አብራርተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...