Thursday, June 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምየቱርክ ገዢ ፓርቲ በዋና ዋና ከተሞች የተሸነፈበት አካባቢያዊ ምርጫ

የቱርክ ገዢ ፓርቲ በዋና ዋና ከተሞች የተሸነፈበት አካባቢያዊ ምርጫ

ቀን:

በቱርክ ከተሞችን የሚያስተዳድሩ ከንቲባዎችንና የምክር ቤት አባላትን ለመምረጥ እሑድ በተካሄደ አካባቢያዊ ምርጫ፣ የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋን ኤኬ ፓርቲ በዋና ዋና ከተሞች ተሸነፈ፡፡

ፓርቲው በዋና ከተማ አንካራ፣ በአገሪቱ ካሉ ከተሞች በስፋቷ በምትታወቀው ኢስታምቡል እንዲሁም በኢዝሚር መሸነፉን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ገዢው ‹‹ጀስቲስ ኤንድ ዲቭሎፕመንት (ኤኬ) ፓርቲ በሦስቱ ትላልቅ ከተሞች የከንቲባ ምርጫዎችን መሸነፉ ለፕሬዚዳንት ኤርዶጋን ውድቀት ነው ተብሏል፡፡

አልጀዚራ በአገሪቱ በመንግሥት የሚተዳደረውን አናዶሉ ሚዲያ ኤጀንሲ ጠቅሶ እንዳሰፈረው፣ የአገሪቱ ምርጫ ቦርድ የምርጫውን ይፋዊ ውጤት የሚያሳውቀው ከሁለቱም ፓርቲዎች በኩል የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ለማስተናገድ ያስቀመጠውን የሦስት ቀን ጊዜ ገደብ ሲያጠናቅቅ ይሆናል፡፡

ሆኖም አናዶሉ ይፋዊ ያልሆነውን የምርጫ መረጃ የለቀቀ ሲሆን፣ በዚህም በአገሪቱ ትልቋ ከተማና የኢኮኖሚ እምብርት ኢስታምቡል የሪፐብሊካን ፒፕልስ ፓርቲ (ሲኤችፒ) ዕጩ ኢክሪም ኢማሞግሉ 48.8 በመቶ ድምፅ በማግኘት፣ 48.5 በመቶ ያስመዘገቡትን የኤኬ ፓርቲ ዕጩ ቢናሊ ይልዲሪም አሸንፈዋል፡፡

የቱርክ ገዢ ፓርቲ በዋና ዋና ከተሞች የተሸነፈበት አካባቢያዊ ምርጫ

 

በቱርክ ዋና ከተማ አንካራ የሲኤችፒ ዕጩ ማንሱር ያቫስ 50.9 በመቶውን የምርጫ ድምፅ በማግኘት 47.2 በመቶ ድምፅ ያገኙትን የኤኬ ፓርቲ ዕጩ መህመት አዚሃስኪ ረትተዋል፡፡

በአገሪቱ ሦስተኛዋ ትልቅ ከተማ ኢዝሚርም የሲኤችፒ ዕጩ ማሸነፋቸው ተገልጿል፡፡ በኢዝሚር የተቃዋሚው ሲኤችፒ ዕጩ ሙስጠፋ ቱራክሶየር 58 በመቶ ድምፅ በማግኘት 38.8 በመቶ ድምፅ ያገኙትን የኤኬ ፓርቲ ኒሃት ዘይቢክ አሸንፈዋል፡፡

ሁሉም የምርጫ ውጤቶች የተቆጠሩት በሦስቱ ትላልቅ ከተሞች ሲሆን፣ የኢስታምቡሉ ምርጫ ደግሞ ተቃዋሚዎችና ገዥው ፓርቲ አንገት ለአንገት የተያያዙበት ነበር፡፡ ሁለቱም ፓርቲዎችም በጠባብ ልዩነት በተለያዩበት የኢስታምቡሉ አካባቢያዊ ምርጫ ‹‹እኔ አሸንፌያለሁ›› እየተባባሉ ነው፡፡

ኤኬ ፓርቲ በእሑዱ አካባቢያዊ ምርጫ በሦስቱ ዋና ዋና ከተሞች መሸነፉ ለፕሬዚዳንት ኤርዶጋን መንግሥት ትልቅ ኪሳራ ነው፡፡ በተለይ የአገሪቱ ገንዘብ በአሜሪካ ዶላር ሲሰላ ዋጋ እያጣ መምጣቱና የአንድ ሊራ የመግዛት አቅም 40 በመቶ ያህል ዋጋ ከማጣቱ ጋር በእሑዱ አካባቢያዊ ምርጫ በዋና ዋና ከተሞች ድምፅ ማጣት ለገዥው ፓርቲ ከባድ ኪሳራ ነው ሲሉ ተንታኞች አስፍረዋል፡፡

ላለፉት 16 ዓመታት ቱርክን የገዛው ፓርቲ ምን አለ?

ካለፉት 16 ዓመታት ወዲህ ቱርክን እየመራ ያለው ገዥው ፓርቲ ኤኬ በተለይ በአንካራ በነበረው ምርጫ ማጭበርበር እንደነበረ መግለጹን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

እንደ ቢቢሲ፣ በአንካራ ከነበሩት 12,158 ምርጫ ጣቢያዎች በአብዛኞቹ ሕገወጥ ምርጫና ማጭበርበር እንደነበር የፓርቲው ዋና ፀሐፊ ፋቲህ ሻሂን ‹‹ሕጋዊ መብታችንን አሟጠን እንጠቀማለን፡፡ የሕዝባችን ፍላጎት በአንካራ እንዲቀለበስ አንፈልግም›› ሲሉ ትዊት አድርገዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ኤርዶጋንም፣ በአገሪቱ ትልቋ ከተማ ኢስታምቡልና በምሥራቃዊ ከተማዋ ኢግዲር ውጤት ላይ ‹‹ይግባኝ እንጠይቃለን›› ብለዋል፡፡

ከአካባቢያዊ ምርጫው በኋላ በሰጡት መግለጫ፣ እ.ኤ.አ. በ2023 የሚካሄደውን ብሔራዊ ምርጫ በመጥቀስ፣ ‹‹ከፊታችን ብዙ ዓመታት አሉ፡፡ እነዚህ ጊዜያት የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ ሕጋችንን ሳንነካ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች የምናደርግበት ይሆናል፡፡ በዚህ መሀል ችግር ከገጠመን ችግሩን ማረም የእኛ ኃላፊነት ነው፤›› ብለዋል፡፡

የምርጫ ቅስቀሳው እንዴት ነበር?

ቱርክ ባለፈው ዓመት ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ካካሄደች በኋላ የአሁኑ የመጀመርያው አካባቢያዊ ምርጫ ነው፡፡ በዚህ ምርጫ የከተሞች ከንቲባዎችንና የምክር ቤት አባላት የሚመረጡበት ሲሆን፣ ኤኬ ፓርቲ ሥልጣን ከያዘበት እ.ኤ.አ. ከ2002 ወዲህ በአካባቢያዊ ምርጫ ተሸንፎ አያውቅም፡፡

ለሁለት ወራት ያህል የተካሄደው የፕሬዚዳንት ኤርዶጋን ፓርቲ ቅስቀሳ 100 ያህል የድጋፍ ሠልፎች ተጠርተውበታል፡፡ በዚህም ‹‹ምርጫው የአገሪቱና የፓርቲያችን የመኖር ህልውና ነው፤›› ብለው ነበር፡፡

ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቅስቀሳ ለማድረግ ምቹ ሁኔታ ያላገኙ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ መንግሥታዊም ሆኑ ለመንግሥት የወገኑ ሚዲያዎች ያቀነቀኑትም ለፕሬዚዳንት ኤርዶጋን ፓርቲ ነበር፡፡

የኩርድ አቀንቃኝ የሚባለው ሌላው ተቃዋሚ ፓርቲ ኤችዲፒ ምርጫው ፍትሐዊ ያልነበረና ብዙ ዕጩዎቹም ከምርጫ ራሳቸውን ያገለሉበት እንደነበር ተናግሯል፡፡ አንዳንድ መሪዎችም የአሸባሪ ቡድን አባላት ናቸው ተብለው ታስረዋል ሲል ቅሬታውን ገልጿል፡፡

የቱርክ ገዢ ፓርቲ በዋና ዋና ከተሞች የተሸነፈበት አካባቢያዊ ምርጫ

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...