የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ዕጣ ወጥቶላቸው ከነበሩት የጋራ መኖሪያ ቤቶች መካከል ከ18 ሺሕ በላይ የሚሆኑ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ ስመ ሀብታቸው ለባለዕድለኞች እንዳይተላለፍ ፍርድ ቤት አገደ፡፡
ዕግዱን የጣለው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ስምንተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ሲሆን፣ ምክንያቱ ደግሞ መቶ በመቶ ክፍያ የፈጸሙ 98 ግለሰቦች ክስ በመመሥረታቸው ነው፡፡
ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ግንቦት 29 ቀን 2011 ዓ.ም. ምላሽ እንዲሰጡ ብሏል፡፡
በሁለቱ ወገኖች መካከል ክርክር ለማድረግ ለሰኔ 10 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡