Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊዩኒቨርሲቲዎች በሦስት መስኮች ተደልድለው እንዲያስተምሩ የሚያስችል ጥናት እየተጠናቀቀ ነው

ዩኒቨርሲቲዎች በሦስት መስኮች ተደልድለው እንዲያስተምሩ የሚያስችል ጥናት እየተጠናቀቀ ነው

ቀን:

የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች የምርምር፣ የቲቺንግና የፖሊ ቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ ተብለው ለሦስት ተከፍለው እንዲሠሩ የሚያደርግ ጥናት እያለቀ መሆኑንና በጥናቱ ውጤትም ላይ በቅርቡ ውይይት እንደሚደረግ፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚኒስትር ሒሩት ወልደ ማርያም (ዶ/ር) ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ ምደባው ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ብለዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎችን በተልዕኮና በትኩረት አቅጣጫ የመደልደል ነገር በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ተመልክቷል ያሉት ሚኒስትሯ፣ ለምርምር የተሻለ የመሠረት ልማትና የሰው ኃይል ያላቸው ዩኒቨርሲቲዎች የጥናትና ምርምር ዩኒቨርሲቲ መደብ ውስጥ እንደሚገቡና በዶክትሬት ዲግሪ ደረጃ ፕሮግራሞችንም እንደሚሰጡ አስረድተዋል፡፡ የንድፈ ሐሳብና ተግባራዊ ትምህርት አጣምረው የሚሰጡ ፖሊ ቴክኒክ ዩኒቨርሲቲዎች መደብ ሥር የሚገቡት ለተግባር ትምህርት የተሻለ የመሠረተ ልማት ዝግጅት ያላቸው ይሆናሉ ተብሏል፡፡ ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት የሚሆኑ ሠልጣኞችን እንዲያፈሩና ለቴክኒክና ሙያ ተቋማትም የበቁ መምህራንን እንዲያወጡ ይጠበቅባቸዋል ያሉት ዶክተር ሒሩት ናቸው፡፡ የተቀሩት ቲቺንግ ዩኒቨርሲቲዎች ሆነው እንደሚቀጥሉም ታውቋል፡፡

በሦስት መስኮች ዩኒቨርሲቲዎቹን መደልደል ያስፈለገው፣ እስካሁን የትምህርት ተቋማቱ በሁሉም የትምህርት ዘርፎች ለማስተማር ያደረጉት ጥረት እምብዛም ውጤታማ ስላልነበር እንደሆነ ተነግሯል፡፡

‹‹ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በማስተማሩም፣ በምርምሩም፣ በቴክኖሎጂውም፣ በግብርናውም፣ በሁሉም ዘርፎች ነው የሚያስተምሩት፡፡ ይህ ደግሞ ውጤታማ ሊሆኑ በሚችሉበት መስክ እንዳይሠሩና ሀብትም እንዲበታተን አድርጓል፤›› ያሉት ሚኒስትሯ፣ ድልድሉም ዩኒቨርሲቲዎቹ እንዳላቸው የመሠረት ልማት ዝግጅትና ያሉበት አካባቢ ከሚሰጣቸው መልካም አጋጣሚ አንፃር እየታየ ነው ብለዋል፡፡

እንደ ላሊበላና አክሱም ባሉ አካባቢዎች የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች አርኪዮሎጂ ላይ ያተኮሩ የልህቀት ማዕከላት ቢሆኑ የተሻለ ውጤት እንደሚያስገኙ፣ በግብርና ላይ ተሞክሮና ታሪክ ያላቸው እንደ ሐሮማያ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ በግብርና ውጤታማ የሆነ ባለሙያዎች ማፍራት እንደሚችሉ አስረድተዋል፡፡ ‹‹ሁሉም ላይ እንሥራ ሲሉ ግን ችግር ነው፡፡ በሁሉም ዘመናዊ ማሽኖችን፣ የምርምር ግብዓቶችን፣ ሪፈራል ሆስፒታሎችን መገንባትና ማሟላት አይቻልም፣ የአገርም ሀብት ይባክናል፤›› ብለዋል፡፡

ከዚህም ጎን ለጎን በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ በተደረገ ጥናት ውጤት ላይ የተመሠረተ የሥርዓተ ትምህርት ለውጥም ይኖራል ተብሏል፡፡ በጥናቱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሠረታዊ የቋንቋ ችግር፣ እንግሊዝኛ ቋንቋን ተጠቅሞ የመጻፍና የማንበብ እንዲሁም የማዳመጥ ችግር፣ ሚዛናዊና ምክንያታዊ ሆኖ ነገሮችን የማገናዘብ ክፍተትና የሥሌት ክህሎትም እንዲሁ ችግር መሆኑ በጥናቱ መታየቱን ሚኒስትሯ ጠቁመዋል፡፡

የተደረገው የሥርዓተ ትምህርት ለውጥም ያሉትን ችግሮች መፍታት እንዲችል ተደርጎ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ እንደ እሳቸው ገለጻ ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ፣ ተማሪዎች ስለአገራቸው ብሎም ስለዓለም የሚያውቁባቸው ኮርሶች እየተዘጋጁ ነው፡፡ መሠረታዊ የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ክህሎት የሚያገኙበት አዲስ ኮርስም ይካተታል ብለዋል፡፡ በቀጣዩ ዓመት ወደ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገቡ ተማሪዎች ወደ ዲፓርትመንቶቻቸው ከመደልደላቸው በፊት፣ የሚወስዷቸው ኮመን ኮርሶች ይኖራሉ፡፡ ካሪኩለሙን እያዘጋጁ የሚገኙት ከዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ምሁራንና የካሪኩለም ባለሙያዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...