Thursday, September 21, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናፍርድ ቤት የዋስትና ጥያቄ እንዲያቀርቡ የፈቀደላቸው እነ አቶ በረከት ስምዖን ዋስትና ተከለከሉ

ፍርድ ቤት የዋስትና ጥያቄ እንዲያቀርቡ የፈቀደላቸው እነ አቶ በረከት ስምዖን ዋስትና ተከለከሉ

ቀን:

የጊዜ ቀጠሮ ምርመራ መዝገባቸው ሲዘጋ የዋስትና መብት መጠየቅ እንደሚችሉ ፍርድ ቤት የነገራቸው አቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ካሳ፣ ፍርድ ቤቱ በነገራቸው መሠረት የዋስትና ጥያቄ ያቀረቡ ቢሆንም ተቀባይነት አላገኙም፡፡

አቶ በረከትና አቶ ታደሰ ለአማራ ክልል የባህር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ፣ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ዋስትና ተከልክለው የክልሉ የሥነ ምግባር ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን ምርመራ ሲያደርግባቸው መክረሙንና የምርመራ መዝገቡ በጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ መዘጋቱን ገልጸዋል፡፡ አሁን ባሉበት ሁኔታ ነፃ መሆናቸውን፣ የከሰሳቸው አካል አለመኖሩን፣ ነገር ግን ማን እንዳሰራቸው እንኳን ሳያውቁ በእስር ላይ መሆናቸውን በማስረዳት፣ በነፃ እንዲሰናበቱ ወይም የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጠይቀው ነበር፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የጠየቁትን የዋስትና መብት የክልሉ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ ተቃውሟል፡፡ የተቃውሞው ምክንያት ደግሞ ሁለቱም ግለሰቦች ሊከሰሱበት የሚችሉት የፀረ ሙስና አዋጅ ቁጥር 881 አንቀጽ 13(3) ከአሥር እስከ 25 ዓመታት የሚያስቀጣ በመሆኑ፣ በራሱ አዋጁ ዋስትና ስለሚከለክል ጥቄያቸው ውድቅ እንዲደረግ ጠይቆ ነበር፡፡

የሁለቱን ወገኖች ክርክር የመረመረው የባህር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ የአቶ በረከትንና አቶ ታደሰን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የዓቃቤ ሕግን ተቃውሞ ተቀብሏል፡፡ በመሆኑም ተጠርጣሪዎቹ ክስ እስከሚቀርብባቸው ድረስ በእስር እንዲቆዩ ትዕዛዝ በመስጠት ለሚያዝያ 10 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...