Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትተለዋዋጩን የእግር ኳስ ዳኝነት ሕግ በኢትዮጵያ የማስረፅ ሒደት

ተለዋዋጩን የእግር ኳስ ዳኝነት ሕግ በኢትዮጵያ የማስረፅ ሒደት

ቀን:

አሉታዊ አስተዋፅኦ ጉልህ መሆኑ በዓለም አቀፍም፣ በክለቦች ደረጃም በሚካሄዱ ጨዋታዎች ላይ የውጤት ለውጥ በማሳደር አንዱን ሲያስደስት ሌላውን ሲያስከፋ ታይቷል፡፡ የዓለም አቀፍ እግር ኳስ አስተዳዳሪ ፊፋ የዳኝነት ሕጎችን በየጊዜው የሚያሻሽለው ከዚህ በመነሳት እንደሆነም ይታመናል፡፡

እንዲህም ሆኖ በእግር ኳስ ዳኝነት ላይ በርካቶች ሁለት ዓይነት አመለካከቶችን ሲያራምዱ ይስተዋላል፡፡ በቅርቡ በእግር ኳስ ታላላቅ የሚባሉት የአውሮፓ አገሮች ሰዋዊ ከሆነው የእግር ኳስ ዳኝነት በተጨማሪ በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ ያደረጉበት አጋጣሚ ተፈጥሯል፡፡ በዚህም እስካሁን ስምምነት ላይ መድረስ እንዳልተቻለ የሚያምኑ አሉ፡፡ አንዳንዶቹ እንደሚሉት በተለይ ከዳኝነቱ ሕግጋት ጋር የእግር ኳስ ውበቱና ጣዕሙ ሰዋዊነቱ በመሆኑ ዳኞች የሚሠሩት ስህተት ላይ ብቻ ማተኮር አይገባም፣ ከእነ ስህተታቸውም ጨዋታዎችን ያለ ቴክኖሎጂ ጣልቃ ገብነት እንዲመሩ ይፈቅዱላቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በተለይም አውሮፓውያኑ አገሮች በቪዲዮ የታገዘ የዳኝነት ሚና በየውድድሮቻቸው እንዲተገበር ማድረግ ከጀመሩ ሰነባብተዋል፡፡

ይሁንና እንዲህ ያለው አካሄድ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ የተገላቢጦሽ ይሆናል፡፡ በኢትዮጵያ እግር ኳስ እንቅስቃሴ ውስጥ የእግር ኳስ ዳኞች በቴክኖሎጂ ተደግፈው ውሳኔ የሚሰጡበት ዕድል ገና አልተፈጠረም፡፡ ተለዋዋጭ የሆነውን ይህን የእግር ኳስ የዳኝነት ሕግ በአገሪቱ ሊግ ለማስረፅ የሚደረግ ጥረት አለ፡፡ ከሰሞኑ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከብሔራዊ ሊግ እስከ ፕሪሚየር ሊግ ለሚዳኙ 400 በላይ ለሚደርሱ የእግር ኳስ ዳኞችና ረዳቶቻቸው የብቃት ማረጋገጫ ፈተና (ኩፐር ቴስት) ሰጥቷል፡፡ .. 2018 እና 2019 የእግር ኳስ ሕጎችን ወደ አማርኛ በመመለስ ለዳኞቹ አስተዋውቋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በአትዮጵያ እግር ኳስ የዳኞች ውሳኔ አጨቃጫቂ ብቻም ሳይሆን ዳኞችን ለድብደባ ሲዳርጋቸውም የታዩባቸው ውድድሮች ጥቂት አይደሉም፡፡ ዓለም በየጊዜው በሚያሻሽለው በዚህ የእግር ኳስ ሕግ ያውም ከስፖርቱ መርህ ውጪ የሆነውንና በወንጀልም ሊያስጠይቁ የሚገባቸው ድርጊቶች በዳኞችና በውድድር አስፈጻሚዎች ላይ በአደባባይ እየታዩ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ቴክኖሎጂዎችን ልጠቀም ብትል ሊመጣ የሚችለውን ለመገመት አያዳግትም፡፡ ይሁንና ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የዳኞችን ክህሎት፣ ብቃት፣ ዕውቀት፣ እንዲሁም በየጊዜው ከሚለዋወጠው የስፖርቱ ሕግና ደንብ ጋር የሚግባቡና የሚተዋወቁ እንዲሆኑ በሥልጠናዎች እየተሰጡዋቸው ነው፡፡

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ፣ ‹‹ሁሉም እንደሚያውቀው የእግር ኳስ ዳኝነት ሕግ ከሚታሰበው በላይ ተለዋዋጭና በየጊዜው የሚሻሻል ነው፡፡ ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ ለብሔራዊ ሊግ፣ ለከፍተኛው ሊግ (ሱፐር ሊግ) እና ለፕሪሚየር ሊጉ የእግር ኳስ ዳኞቻችን በየሦስት ወሩ ነው የብቃት ማረጋገጫ ፈተና የሚሰጠው፣ ከሰሞኑ የተደረገውም ይህ ነው፤›› ብለዋል፡፡

ከብቃት ማረጋገጫ ፈተናው በተጨማሪ ሕጎቹ ወደ አማርኛ እየተመለሱ ለዳኞቹ እንደሚሰጥ ጭምር አቶ ዮሴፍ ያስረዳሉ፡፡ ፈተናውን አስመልክቶ በአሁኑ ወቅት በብሔራዊ ሊግ እየዳኙ የሚገኙ በአጠቃላይ 116 የእግር ኳስ ዳኞች 14ቱ፣ በከፍተኛው ሊግ ደግሞ 113 ለፈተና ቀርበው ዘጠኙ፣ እንዲሁም ከፕሪሚየር ሊጉ 80 ቀርበው አራት የእግር ኳስ ዳኞች የብቃት ማረጋገጫ ፈተናውን ማለፍ እንዳልቻሉ ጭምር ተናግረዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...