Thursday, February 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ከኃላፊነታቸው ተነሱ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ከኃላፊነታቸው ተነሱ

ቀን:

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ከዘጠኝ ወራት በላይ በኮሚሽነርነት ሲመሩ የቆዩት ሜጀር ጄኔራል ደግፌ በዲ ከኃላፊነታቸው ተነሱ፡፡

ኮሚሽኑን ለዓመታት ሲመሩ የነበሩትን አቶ ይህደጎ ሥዩምን ተክተው በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሰኔ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. የተሾሙት ሜጀር ጄኔራል ደግፌ፣ ከኃላፊነታቸው በድንገት የተነሱበት ዝርዝር ምክንያት ለጊዜው ባይታወቅም፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 1 ቀን 2011 ዓ.ም. የደረሳቸው የስንብት ደብዳቤ ግን ‹‹በጡረታ›› የሚል መሆኑ ታውቋል፡፡

ኮሚሽነሩ ለበርካታ ዓመታት በመከላከያ ሠራዊት አባልነት የሠሩ ናቸው፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ተደርገው ሲሾሙ፣ የሁለቱ ተቋማት ተግባርና የሥራ አፈጻጸም ሁኔታ ለየቅል በመሆኑ ለጊዜው ግርታን ፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ነገር ግን ላለፉት ዘጠኝ ወራት ኮሚሽኑን ሲመሩ ቆይተው፣ ከሚያዝያ 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በጡረታ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ታውቋል፡፡

ሜጀር ጄኔራል ደግፌ በጡረታ የተሰናበቱት በተቋም ደረጃ ምንም ዓይነት ችግር ገጥሟቸው ሳይሆን፣ በሕመም ምክንያት መሆኑንና ይኼንንም ከመንግሥት ጋር ውይይት አድርገው መተማመን ላይ በመድረሳቸው መሆኑን የሪፖርተር ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ማስተካከያ

በሪፖርተር ጋዜጣ ረቡዕ ጥር 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ዕትም...

[ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የቀረበላቸውን ምክረ ሐሳብ እያደመጡ ነው]

ችግሩ ምን እንደሆነ በትክልል ለይተነዋል ግን ግን ምን? በይፋ መናገር አልነበረብንም። ለምን? ችግሩን...

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትና እንደምታው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የትምህርትን...

ንግድ ባንክ ከቪዛና ማስተር ካርድ ጋር ተደራድሮ ያስጀመረው የገንዘብ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂና ፋይዳው

ከውጭ ወደ አገር በሕጋዊ መንገድ የሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) መጠን...