Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ልናገርየለውጡ እንቅፋቶች የሚወገዱት አገር ከሥልጣንም ሆነ ከሀብት ስትቀድም ነው

የለውጡ እንቅፋቶች የሚወገዱት አገር ከሥልጣንም ሆነ ከሀብት ስትቀድም ነው

ቀን:

በንጉሥ ወዳጅነው

ጋዜጠኛና ገጣሚ ነብይ መኮንን “ይድረስ ለወራሼ” የሚል ረዘም  ያለ  ግጥሙን “ብሌን”  በተሰኝ የደራሲያን ማኅበር መጽሔት ላይ ከዓመታት በፊት አንብቤው ብቻ ሳይሆን፣ ደጋግሜ አጣጥሜዋለሁ፡፡ እናም ለወጣቱ ላደርሰው ላሰብኩት ወቅታዊ  መልዕክት ስለሚስማማኝ ለዚህ ጽሑፍ እንደ መግቢያ ጥቂት ቀዳሚ ስንኞችን ለመምዘዝ ወድጃለሁ፡፡

አንተ ወራሼ ወጣት ሆይ፣

- Advertisement -

ነብስ  እንደ ሱፍ አበባ፣ ለነገ ፀሐይ ትከፈት 

እንደጉጉ ወጣት ምኞት፣ ያላየህውን ናፍቅበት!

      ፂሙ ቢሻክርህ እንኳ፣ እያንዳንዱን ቀን ሳመው

በፍቅርህም በሞትህም፣ ቀርበህ ሳተውቀው፣ ዘመድ ነው

ክፉ ቀን እንደፈተና፣ ደጉን እንደቀኝ ምርኩዝ

ሀጋይና ቁር ለይበት ክረምቱን ከበጋ አይተህ ያዝ!!

የህልም ድህነት ነው ክፉ የሩቅ አሳቢን ልብ የሚያም

የራስ አንገት ሽታ እሚያከስም

አዲስ ራዕይ የሚያጨልም፣ ይላል፡፡

 ይህ ሐሳብ ለዚህ ዘመን ትውልድ ክፉን ከደጉ ለይቶ፣ ሩቅ አልሞ እንዲንቀሳቀስ ከመምከር ባለፈ ክፉውን ቀን እንደ ፈተና፣ መልካሙን አጋጣሚም እንደ ቀኝ ምርኩዝ አድርጎ እንዲጓዝበት ያሳስበዋል፡፡ በእኔ እምነት አሁን ለአገራችን ወጣቶች ከትናንት የተሻለ በጎ ጊዜ ቢመጣም፣ እየተገዳዳረን ያለው የጥላቻና የዘረኝነት የዞረ ድምር ግን በአሉባልታ እየታጀበና ተጠራጣሪነትን እያሰፋ መሄዱ አደገኛ ሆኖ ይሰማኛል፡፡

በመሠረቱ አሁን ባለው የየትኛውም ዓለም ትውልድ ዕውቀት መረጃም ሆነ አብዮት በማኅበራዊ ድረ ገጽ የሚከወን ሲሆን፣ መርጦና ለይቶ ወይም የሚበጀውን ፈልጎ መጠቀም ካልተቻለ ግን ዳፋው ለትውልድና ለአገርም ሊተርፍ የሚችል ነው፡፡ እንደ ቅርብ ጊዜ መረጃዎች ከሆነ እስካሁን በአገራችን ከ35 እስከ 40 ሚሊዮን የሚደርስ የሞባይል ተጠቃሚ ሲኖር፣ እስከ አምስት ሚሊዮን የሚደርሰውም ማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ እንደሆነ ይገመታል፡፡ ይህ ኃይል ዘመናዊውን የግንኙነት አውታር በአግባቡ ተጠቅሞ አገሩንና ራሱን ካልጠቀመ ጉዳቱ ከፍተኛ መሆኑ አይቀርም፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደምንታዘበው ማኅበራዊ ድረ ገጽን በአሉታዊ መንገድ በመጠቀም የፈረሱና ለጨነገፈ አብዮት የተጋለጡ የዘመናችን አገሮች ቁጥራቸው ትንሽ አይደለም፡፡ ምናልባት ሙሉ በሙሉ ምክንያቱ እሱ ነው ለማለት ቢያዳግትም፣ የፀደይ አብዮት የበተናቸው የዓረብ አገሮች (ሶሪያ፣ ሊቢያ፣ የመን፣ ግብፅ (ባትፈርስም ዴሞክራሲያዊነት እንደራቃት ነች) አሁን ደግሞ አልጄሪያን እንደ አብነት መጥቀስ ይቻላል፡፡

  እነዚህ ወገኖች ምንም እንኳን የውስጥ ዴሞክራሲ ዕጦት ያፈናቸውና በምጣኔ ሀብት ከእኛ ቢሻሉም፣ አምባገነናዊ አገዛዞች ያማረሯቸው ሕዝቦች የሞሉባቸው ስለነበሩ ወደ ለውጥ አምርተዋል፡፡ ይሁንና በዋናነት በወጣቱ ኃይል ያልተቋረጠና ውጤቱ በማይተዋቅ የፌስቡክ እሩምታና ሁካታ ጭምር ነው ለክሽፈት የተጋለጡት የሚለውን ድምዳሜ መዘንጋት ያዳግታል፡፡ ለነገሩ እስከ መፍረስ ባይደርሱም በወጣቱ ኃይል የማኅበራዊ ድረ ገጽ ውዥንብር (እንደኛ የጥላቻ ፖለቲካና ዘረኝነት ባይሆንም) የተናጉ የምዕራቡ ዓለም አገሮችም አልጠፉም ነበር፡፡

ነገሩን ወደኛ ነባራዊ ሁኔታ ስናመጣው ማኅበራዊ ድረ ገጽን በአሉታዊ መንገድ የመጠቀምና የሐሰት መረጃ በማስተላለፍ ትርምስ የመፍጠር ምልክት እየተስፋፋ መምጣቱን እንገነዘባለን፡፡ በዚህም ሊፈጠር ከሚችል ቀውስና አገርን ከዕልቂት አደጋ መጠበቅ የመንግሥት ብቻ ሳይሆን፣ የሁሉም ዜጎች የጋራ ኃላፊነት መሆኑን ከወዲሁ ካልተገነዘብን ችግሮች መባባሳቸው አይቀርም ፡፡

ዜጎች (በተለይም አዲሱ ትውልድ) የአገራቸው ጉዳይ ያገባቸዋል፡፡ በገዛ አገራቸው የሚፈጠሩ ጉዳዮችን ችላ ማለትም ሆነ የተፈጠረውን እንዳልተፈጠረ መተው፣ እንዲሁም የተፈጠረውን ችግር በማቀጣጠል ማራገብም አይገባቸውም፡፡ አይኖርባቸውም፡፡

 በመሠረቱ ማኅበራዊ ድረ ገጽ ኖረም አልኖረም በአገር ላይ ሰላም፣ ዴሞክራሲና ልማት ይቀጥል ከተባለ ሁሉም በአገሩ ጉዳይ ላይ የባለቤትነት ስሜትኖረው ይገባል፡፡ ማናቸውም የመንግሥት፣ የሕዝብና የፖለቲካ ኃይሎችና የማኅበራዊ ድረ ገጽ ተዋናዮች  ተግባርም በሰላም፣  በዴሞክራሲያዊ መንገድና ለአገር በሚጠቅም አኳኋን እየተፈጸመ እንደሆነ እርግጠኛ መሆን ይጠቅማል፡፡ እዚህ ላይ ሚዲያዎች፣ ትምህርት ቤቶችና ሲቪክ ማኅበራትም ከፍተኛ ሥራ ሊያከናውኑበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን መጠቆም ያስፈልጋል፡፡

አሁን አሁን በማወቅም ይሀን ባለማወቅ ከሰላማዊና አብሮነታዊ ገለጻ ውጪና በተቃራኒው መቆም እየተለመደ ነው፡፡ ለበጎም ተብሎ ቢሆን ሕዝብን ከሕዝብ ማበላላጥ፣ ሌላውን ማንኳሰስ እንደ ዋዛ ሲነዛ ማየት ያሳቅቃል፡፡ በተለይ ደግሞ ሙሉ ኃላፊነት የማይወሰድበት ብሎም ለውዥንብርና አሉባልታ የተጋለጠው ፌስቡክን በመጠቀም ረገድ ያለው ክፈተት እየተባባሰ ነው፡፡

 አንዳንዶች ሥልጣንን (ጊዜያዊ ጥቅምንና ተራ የፖለቲካ ትርፍን ለማጋበስ)  ታሳቢ በማድረግ ብቻ ብሔርን፣ ማንነትን፣ የፖለቲካ አመለካከትን፣ ሃይማኖትንና ሌሎች ልዩነቶችን መሠረት በማድረግ ኃላፊነት በጎደለው መንገድ የጥላቻ ንግግሮችን፣ ሐሰተኛ መረጃዎችን፣ ብሎም ግጭት ቀስቃሽ የቃላት እሩምታን እያሠራጩ ነው፡፡ ስድብና ፀብ አጫሪ ንግግሮችም ቢያንስ ሲቀንሱ አለመታየታቸው ሁሉንም ሊያሳስብ ይገባል፡፡

የዚህ እኩይ ድርጊት አራማጆች አደገኛው ሥልታቸው ደግሞ ማንነታቸውን ሸሽገው ዘርን ከዘር ላማጫረስ በማይወክሉት ብሔር ስም ስድብና ጥለቻ እያራመዱ መሆናቸው ነው፡፡ እነዚህ ቅጥረኞች ወይም የጥፋት ኃይሎች ዛሬ የተፈጠሩ ሳይሆኑ ከዚህ ቀደምም በከፍተኛ ክፍያና አንዱን ከአንዱ ለማጋጨት በሚሰጥ አቅጣጫ ታግዘው የሚሠሩ እንደነበሩ የሚታወቅ ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህ ወገኖች ያነገቡትን  ህቡዕ  ዓላማ ዜጎች ተገንዘብው ማውገዝና አለማዳመጥ (ብሎክ ማድረግ) ብቻ ሳይሆን፣ ለብሔራዊ ጥቅም ሲባል ማንነታቸውን ማጋለጥም አለባቸው፡፡ እዚህ ላይ መንግሥትም የመዋቅር መዳከም ሳይገጥመውና ራሱን አጠናክሮ ሕገወጦች በሕግና በሥርዓት አደብ እንዲይዙ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

 ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገራችን በማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይ በተደረገ ጥናት (ከሁለት ዓመታት በፊት በመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት የተደረገ ጥናት ነበር) በአገሪቱ ብዛት ያላቸው የጥላቻ ሐሳቦች የሚስተጋቡ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ ነገሩ ከዚም ወዲህ ተባብሶ ቀጥሎ እንደሆነ እንጂ ላለመቀነሱ አሁንም የምንመለከተውና የምንታዘበው እውነታ ነው፡፡ እውነት ለመናገር አሁን ደግሞ አጥንቶ እንኳን መፍትሔ ሊያመላክት የሚችል፣ ወይም በመረጃ ፍሰት ውሸቱን እያጋለጠ ፈጥኖ ትክክለኛና የእርምት መረጃ የሚሰጥ የፌዴራል ተቋም ባለመኖሩ ችግሩ ይባባስ እንደሆን እንጂ፣  በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሊስተካከል አይችልም ፡፡

በተለያዩ ሐሰተኛ ስሞችና ማንነቶች የተከፈቱ የፌስቡክ ገጾች አማካይነት የሚሠራጩ መረጃዎች ብዙ ጉዳት እያደረሱ ነው፡፡

 እነዚህ ወገኖች ሐሰተኛና የተጋነኑ መረጃዎችና ትንተናዎች የሚጠቀሙት ተወደደም ተጠላም ለውጡ እንዲቀለበስ፣ አይሣካላቸውም እንጂ ሕዝብና ሕዝብ ተጋጭቶ አገር ወደ ትርምስ እንድትገባ ነው፡፡ ከማኅበራዊ  ድረ ገጽ ተጠቃሚዎች መካካል ግን አንዳንዶቹ ሳይረዱ፣ አንዳንዶችም የጥላቻ ገለጻውን ተረድተውና አምነውበት ነገር ግን በአገር፣ በሕዝብ፣ በቤተሰባቸውም ሆነ በራሳቸው ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ሳያስተውሉ ያስተጋቡታል፣ ያሠራጩታልም፡፡ ይህም የሚያስከትለው መዘዝ የከፋ እንደሆነ ወለል ብሎ እየታየ ነው፡፡ ፈጥነን ካላረምነውም ውድ ዋጋ ሊያስከፍለን እንደሚችል ዕሙን ነው፡፡

ከዚህ ቀደምም በገሃድ እንደታየው በጎሳ ፌዴራሊዝም የመነጣጣል አዙሪትና የጥላቻው ትርክት ምክንያት ሕዝብ ለሕዝብ አብሮ እንዳይቆምና ኅብረት እንዳይፈጥር ሰፊ የማቃቃር ዘመቻ ተሠርቶብናል፡፡ ቀድመው ይህ ችግር እንደሚመጣ ያወቁ አንዳንድ ዘራፊና አፋኝ ኃይሎች ሀብታቸውን አሽሽተውና ልጆቻቸውን ውጭ ልከው እነሱ በምሽጋቸው ውስጥ ገብተዋል፡፡ በእነሱ እምነት አገር ቢተራመስም ወላፈኑ የሚነካቸው አልመሰላቸው ይሆናል፡፡ በዚያ ብቻ ግን እንደማያበቃ አለመማር ተላላነት ነው፡፡

 ጦርነቱ እዚያው ተለኩሶ እዚያው ያልቃል የሚለው የአንዳንዶች መተበይ የመጣውም ከዚህ ዓይነቱ የተሳስሰተ ግምገማ መሆኑ እርግጥ ነው፡፡ እሳቱ አይለኮስ እንጂ  ከተነሳ ግን የማያነደው ወገን እንደሌለ መታወቅ አለበት፡፡

       በመሠረቱ አሁን እየታየ ያለው ድርጊት እንዳው ጥሎብንና ከውጭ የመጣን ነገር ሁሉ ተስገብግበን የመውሰድ ልምድ ተስፋፍቶብን እንጂ፣ እንደ ግለሰብ ለአሉባልታና ለወሬ በሚል የፌስቡክ ተጠቃሚነቱስ ቢቀርና አደብ እንዲይዝ ቢደረግ ምንኛ በተሻለ የሚያስብል ነው፡፡ በመሠረቱ በፌስቡክም ሆነ በሌላ መንገድ  #K¨_ ¾K¨< õ_$ vM ¾U”cT¨< ŸÉa ËUa ’¨<:: አዲሳችን ›ÃÅKU :: #Ù` Ÿð¨<  ¨_ ¾ð¨<$ Sባሉ”U ²S’<” ›MqÖ`’¨<Uንጂ ŸØ”ƒ ËUa ¾T>’Ñ` ’¨<:: ¨_ ÁM•[uƒ ጊዜ ¾TÃјuƒ ሥፍራ ¾KU:: ለዚህ ትውልድ ግን ቴክኖሎጂን ለዕውቀት፣ ለትክክለኛ መረጃና እንደ ስሙ ለማኅበራዊ ትስስር እንጂ ለወሬና ለመነጣጣል ማዋል እንደማይገባው ግልጽ መሆን ይኖርበታል፡፡ u}Kà ’Ñ\” KØL‰ ¨_“ KTnn` SÖUU ”Å ’` SqÖ` ›Kuƒ::

   በእርግጥ የማይካደው እውነት ¨_ ¾Tu^© ¡e}ƒ ð`Ï የመሆኑ ጉዳይ ’¨<:: ›õ ¾}ðÖ[¨< KT¨<^ƒ ቢሆ”U ›”ǔʉ‹” Ó” ›ó‹” Là (uôeu<¡ ÅÓV `“ Lá LÝŠSw^ƒ“ ¨< q×] ባይuÏM” •a uT>[ባውU’ uTÃ[ባውU SeS^‹” Ãs[Øw” ’u`:: ያገኘነውን ሁሉ ነው በአሉባልታ መልክ የምናዥጎደጉደው፡፡ ሳያጠሩና ለጥላቻ አስበው የሚያወሩምና የሚጽፉም  (ከላይ እንደተጠቀሱት ያሉት) በእጅጉ ብዙ ናቸው፡፡

     በተለይአሁኑ ትውልድ ላይ እየተጫነ ያለው የፌስቡክ ¨_ ª“¨< Ñ<ǃ ¾}×SS ¨ÃU ¾}³v ”ö`T@i” (S[Í) ¾T>Áe}LMõ ብቻ ሳይሆን፣ በፍጥነት ሰፊ ሥፍራ የሚያዳርስም uSJ’< ’¨<:: የማኅበራዊ ሚዲያ ¨_ S[} e dx‹”U õ u”óe  õØ’u[[ ŸKU ݝeŸ Ýõ LÑ–¨< c¨< G< (ልጅ አዋቂ ሳይል) ስለሚያደርስ ጉዳቱ እንደ ቀላል የሚታይ አይደለም፡፡ እንደኛ ባለው አገርና የፖለቲካ ሁኔታም አገር ሊበትንና የሕዝብን አብሮነትን ሊያፈርስ ስለሚችል፣ ጥንቃቄ ካልተደረገበት አደጋው እንደ ሰደድ እሳት መሆኑ አይቀርም፡፡ በተለይ ለወጣቱ ትውልድ ‹‹ነገን አስብ ሩቁን ተመልከት›› የሚያስብለው ሀቅ መነሻውም ይኼው ነው፡፡

      በእርግጥ አገር ለማበጣበጥ የሚሹ የፖለቲካ ኃይሎች መታገያ መድረካቸውን ፌስቡክ በማድረግ ሕዝብና ሕዝብን ለማጠዛጠዝ እንደተሠለፉ፣ በብዛት የአማራና የኦሮሞ ብሔርን ስም ለማሳሳቻነት እንዴት እንደሚጠቀሙበት ከላይ ካነሳናቸው አካውንቶችም በላይ በርካታ አብነቶችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ እሱ ብቻ ሳይሆን በአገር ስምና በተዳራጁ አካላት ስም ማኅበር፣ ኅብረት፣ ፎረም፣ ወዘተ እየተፈበረከ የሚነዛው የጅምላ ፍረጃ እንዲጋለጥ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል፡፡ በሁሉም ዘንድ አገር ማዳንና መውደድም በዚህ ተግባር ሊገለጽ ይገባል፡፡

      በዚህ ረገድ አሁን አገራዊ ለውጥና የተሻለ ምዕራፍ ሊመጣ በሚችልበት ጊዜ እንኳን የሐሳብ ነፃነትና የዴሞክራሲ ምኅዳር መስፋትን ምክንያት በማድረግ፣ ጥፋትን ለመጋበዝ የሚዳዳው መብዛቱን ተረድቶ ለመለወጥ መሥራት ያስፈልጋል፡፡ በተለይ ለውጡን ያልተቀበለውና ተሸናፊ የሚመስለው ወገን ሒሳብ ማወራረጃ በማኅበራዊ ድረ ገጾች የሚስተዋለው የጥላቻ ሐሳብ፣ ከግለሰቦች አልፎ ተርፎ ብሔሮች ላይ ማነጣጠሩ ለአገር ህልውና ጠንቅ እስከመሆን መድረሱ መታመን አለበት፡፡ አሁን ድረስ በዚህ መድረክ የሚታዩና የሚቀሰቅሱ የጥላቻ ሐሳቦች ምን ያህል አሳሳቢ መሆናቸውን እያንዳንዱ ዜጋ ሊረዳም ይገባል፡፡ ይህ ሲሆን ነው ለለውጥ መነሳት የሚቻለው፡፡

በመሠረቱ እንኳን ዛሬ ሁሉም በነፃነት በአገሩ ምድር እንዲንቀሳቀስ ተፈቅዶ አይደለም፡፡ መቼም ቢሆን የተለያዩ አቋሞች ያሉዋቸው የፖለቲካ ኃይሎች በአገራችን መኖራቸው ኃጢያት አይደለም፡፡ ነገር ግን የፖለቲካ ሥልጣንን ብቻ በማሰብ የጋራ አገራዊ እሴትንና የሕዝቦችን ጥቅም ለመጉዳት የሚደረገው ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ሁሉ መገታት አለበት፡፡ ይህ ደግሞ በሕዝብ ቅንነትና በመሪዎች ልመና ብቻ ሊረጋጋጥ ስለማይችል፣ የሕግ ልጓምን ማጠናከርና የጥላቻና አፍራሽ ንግግርን ሥርዓት ማስያዝ የሚበጅ ይሆናል፡፡

 በመድረክም ሆነ በማኅበራዊ ድረ ገጽ ማንኛውም የፖለቲካ ተፎካካሪ፣ ጦማሪም ሆነ የመብት ተሞጋች ቢሆን ለሕዝቦች አንድነት፣ እኩልነትና ፍትሕ ቅድሚያ መስጠት አለበት፡፡ ደግሞም ይኖርበታል፡፡ በተለይ የሕወሓት/ኢሕአዴግ ሥርዓት ከጣለብን የጥላቻ ትርክት በመውጣት አብሮነትን የማጠናከር ጉዳይ ቀዳሚ ተግባራችን ሊሆን ይገባል፡፡ የፖለቲካ ድርጅትም ከሥልጣን በፊት አገርን ሊያስቀድም ይገባል፡፡ ሁሉም ነገር ከአገር ቀጥሎ የሚመጣ ነው፡፡ አገር ከሌለች ሥልጣንም ሆነ ሀብት ማግኘት አይቻልም፡፡ ለለውጡ እንቅፋቶች መወገድና ወንጨፍ ለዛሬ ያነሳሁት ምክር ይኼው ነበር፡፡

 ከአዘጋጁጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ማግኘት ይቻላል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...