ጥሬ ዕቃዎች
- 4 መካከለኛ ጭልፋ (600 ግራም) ቅጠሉ ብቻ በመቀቀያ አፈር የተቀቀለና ደቆ የተከተፈ የአበሻ ጐመን
- 1 መካከለኛ ጭልፋ (150 ግራም) በክብ ቅርጽ የተከተፈ ነጭ ሽንኩርት
- 1 መካከለኛ ጭልፋ (150 ግራም) ደቆ የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
- 4 የሾርባ ማንኪያ ለጋ ቅቤ
- ግማሽ የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ኮረሪማ
- 4 ፍሬው ወጥቶ የተገረደፈ ቃርያ
- 2 የሻይ ማንኪያ ጨው
አዘገጃጀት
- ቀይ ሽንኩርቱን በውኃ ብቻ ማብሰል፤
- ሲበስል ሁለት የሾርባ ማንኪያ ቅቤ መጨመር፤
- ጐመኑን ጨምሮ በትንሽ ውኃ ሳይከድኑ ማብሰል፤
- ነጭ ሽንኩርቱን ለብቻው በትንሽ ውኃና በአንድ የሾርባ ማንኪያ ቅቤ መቀቀል፤
- ነጭ ሽንኩርቱ ሲበስል ጐመንና ኮረሪማውን ጨምሮና ጨውን አስተካክሎ ማውጣት፤
- ጐመኑና ሽንኩርቱን አንድ የሾርባ ማንኪያ ቅቤ አድርጐ ነጭ ሽንኩርቱ እንዳይፈራርስ በጥንቃቄ እያማሰሉ ቃርያ ነስንሶ ከደባለቁ በኋላ ማውጣት፡፡
[ጐመኑና ነጭ ሽንኩርቱ አረንጓዴና ነጭ ሆኖ መታየት አለበት፡፡ ሽንኩርቱ ለብቻ የሚቀቀለው እንዳይቦካና መልኩ እንዳይጠፋ ነው፡፡]
- ደብረወርቅ አባተ ‹‹የባህላዊ ምግቦች አዘገጃጀት›› (2003)