ጥሬ ዕቃዎች
- 7 ከግማሽ ጆግ (5 ኪሎ ግራም) የፉርኖ ዱቄት
- ግማሽ ጆግ ንጹሕ የተጠለለ የጤፍ እርሾ (ውኃው ብቻ)
- የ5 ፍሬ ጤና አዳም ውኃ (ጨፍለቅ፣ ጨፍለቅ ተደርጐ በ5 የሾርባ ማንኪያ ውኃ ተበጥብጦ የተጠለለ)
- 2 የሾርባ ማንኪያ የዳቦ ቅመም
አዘገጃጀት
1. ዱቄቱን ከዳቦ ቅመም ጋር በደረቁ መቀላቀል፤
2. የጤና አዳም ውኃውን፣ ዱቄቱንና እርሾውን ጨምሮ በትንሽ፣ በትንሹ ውኃ እየጨመሩ ማቡካት፤
3. ወፈር አድርጐ አሽቶ እንዲቦካ መተው፤
4. በወፍራሙ ጥቅልል አድርጐ ሊጥ ማስቀመጫ ውስጥ መተው፤
5. በሦስተኛው ቀን በውኃ ቀጠን አድርጐ አቡክቶ መተውና አንድ ቀን ማሳደር፤
6. ውኃው ከላይ እንደ ጤፍ ቡኮ በደንብ ስለማይጠል በትንሹም ቢሆን ያቀረረውን አጥልሎ እንደ ጤፍ አብሲት አቅጥኖ ማዘጋጀት፤
7. ኩፍ ብሎ በረድ ሲል እንደ እንጀራ መጋገር፡፡
– ደብረ ወርቅ አባተ ‹‹የባህላዊ ምግቦች አዘገጃጀት›› (2002)