Sunday, March 26, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ለሰባት ኩባንያዎች የማዕድን ፍለጋ ፈቃድ ተሰጠ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ለሰባት ኩባንያዎች ስምንት የማዕድን ፍለጋ ፈቃድ ሰጠ፡፡ ሚኒስቴሩ የፍለጋ ፈቃድ የሰጠው ለሰቆጣ የማዕድን ኃላፊነቱ የግል ማኅበር፣ ለአይጋ ትሬዲንግ ኢንዱስትሪስ፣ ለአጎዳዮ ሜታልስና ሌሎች ማድናት ኩባንያ፣ ለአፍሪካ ማይኒንግና ኢነርጂ፣ ለአልታው ሪሶርስስ ሊሚትድ፣ ለሰን ፒክ ኢትጵያና ለሒምራ ማይኒንግ ነው፡፡ የማዕድን ኩባንያዎቹ በአማራ፣ በአፋርና በትግራይ ክልሎች የማዕድን ፍለጋቸውን እንደሚያከናውኑ ታውቋል፡፡ ከማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ የአገር ውስጥና የውጭ የማዕድን ኩባንያዎቹ በወርቅ፣ በብረት፣ በፓታሽ፣ በድንጋይ ከሰልና በኖራ ድንጋይ ፍለጋ ይሰማራሉ፡፡ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ከ88 ሚሊዮን ብር በላይ ኢንቨስት እንደሚያደርጉ ማስታወቃቸው ተጠቁሟል፡፡ የኩባንያዎቹ ኃላፊዎች ከሚኒስትር ዴኤታው አቶ አሰፋ ኩምሳ ጋር ረቡዕ ሚያዝያ 9 ቀን 2011 ዓ.ም. ስምምነት ፈጽመዋል፡፡ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትሩ አቶ ሳሙኤል ኡርካቶ እንዳስታወቁት፣ በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የማዕድን ፍለጋ ፈቃድ ለማግኘት 56 ኩባንያዎች ጥያቄ አቅርበዋል፡፡፡ ሰባቱ ኩባንያዎች የሚኒስቴሩን መመዘኛዎች ማሟላታቸውን ሚኒስትሩ አስረድተው፣ ኩባንያዎቹ ለአካባቢ ጥበቃና ፕሮጀክቶቹ የሚገኙባቸውን ማኅበረሰቦች ጥቅም በማረጋገጥ ሥራቸውን ማከናወን አለባቸው ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች