Saturday, April 1, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ25 ቢሊዮን ዶላር ኩባንያ ለመሆን አቅዷል

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

በከፍተኛ ደረጃ ዕድገት እያስመዘገበ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ እ.ኤ.አ. በ2035፣ 25 ቢሊዮን ዶላር የሚወጣ ኩባንያ ለመሆን ማቀዱ ተሰማ፡፡ የአየር መንገዱ ማኔጅመንት የራዕይ 2025 ቀጣይ የሆነውን ራዕይ 2035 በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ ታውቋል፡፡ የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም፣ አየር መንገዱ ራዕይ 2025 ከመገባደጃ ጊዜው ቀድሞ በማሳካቱ አዲሱ ዕቅድ መዘጋጀቱን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ አየር መንገዱ ራዕይ 2025 ከመገባደጃ ጊዜው በስምንት ዓመት ቀድሞ ማሳካቱን የተናገሩት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ከዚህ በኋላ ስለራዕይ 2025 ማውራት እንደማያስፈልግ ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም ለቀጣዮቹ 15 ዓመታት የሚመራበትና ድርጅቱን 25 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ የሚያደርገውን ዕቅድ በተወሰኑ ወራት ይፋ እንደሚያደርግ ታውቋል፡፡ አየር መንገዱ እ.ኤ.አ. በ2010 ራዕይ 2025 ይፋ ሲያደርግ 1.3 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ የነበረ ሲሆን፣ አሁን ግን 4.1 ቢሊዮን ዶላር የሚወጣ ድርጅት ነው፡፡

 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች