Thursday, December 1, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊ በጊቤ ፓርክ የጉማሬዎች ሞት መንስዔ እየተጣራ ነው

   በጊቤ ፓርክ የጉማሬዎች ሞት መንስዔ እየተጣራ ነው

  ቀን:

  ሰሞኑን በደቡባዊ ምዕራብ ኢትዮጵያ በጊቤ ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክ፣ የሞት አደጋ የደረሰባቸው ባብዛኛው በውኃ ውስጥ የሚኖሩት ጉማሬዎች አሟሟትን የሚመረምር የባለሙያዎች ቡድን ወደ ሥፍራው ማቅናቱን፣ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

  የባለሥልጣኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ሰሎሞን ወርቁ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በፓርኩ ውስጥ ከሚያዝያ 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በአንድ ሳምንት ውስጥ 28 ጉማሬዎች ሞተው ተገኝተዋል፡፡

  ጉማሬዎች ምግባቸው የሚመገቡት ሌሊት ከወንዝ ወጥተው በየመስኩ በመንቀሳቀስ ሲሆን፣ የሞት አደጋው የደረሰው ምናልባት ተመርዘው ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬ እንዳለ ጠቁመዋል፡፡

  የጉማሬዎቹን ሞት መንስዔ ለማጣራት ከባለሥልጣኑ፣ ከብሔራዊ የእንስሳት ምርምር ማዕከልና ከፖሊስ የተውጣጡ ባለሙያዎች በሥፍራው ይገኛሉ፡፡ የላቦራቶሪ ባለሙያዎች ከወሰዱት ናሙና በሚደረገው ምርመራ መንስዔው ሊታወቅ ይችላል ተብሏል፡፡

  በፓርኩ በሚገኙ ሌሎች እንስሳትና አዕዋፋት የተከሰተ ችግር እንደሌለም አቶ ሰለሞን ገልጸዋል፡፡

  ምግቡን ለማግኘት ምሽት ላይ ከውኃ የሚወጣው ጉማሬ ቀኑን ሙሉ የሚያሳልፈው በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ በውኃ ተሸፍኖ ነው፡፡ እስከ ሦስት ቶን የሚመዝን ሲሆን፣ በአንድ ምሽትም እስከ 40 ኪሎ ግራም ድረስ እንደሚመገብ፣ የሚመደበውም ከቅጠላ ቅጠል በሊታዎች እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

  ከአዲስ አበባ በጅማ መንገድ 178 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘውና የጊቤ ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክ በ2003 ዓ.ም. የተመሠረተ ሲሆን፣ 200 ጉማሬዎች በአካባቢው እንደሚኖሩ ይገመታል፡፡ የተለያዩ የዱር እንስሳትም ይገኙበታል፡፡

  በጉራጌ ዞን ከዘቢዳር ሰንሰለታማ ተራራ ባሻገር የሚገኘው ጊቤ ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክ 36 ሺሕክታር መሬት አካሎ የያዘ ሲሆን፣ በደንና በቁጥቋጦ የተሸፈኑ የተለያዩ የዕፀዋት ዝርያዎች ይገኙበታል፡፡ 17 ዓይነት አጥቢ የዱር እንስሳትም አሉበት፡፡ ከእነዚህም መካከል አምበራይሌ፣ አጋዘን፣ ድኩላ፤ በወንዙ ሸለቆም ጉማሬና አዞ  ይገኛሉ፡፡ ባለ ቀለም የጦጣ ዝርያዎችና ከ200 በላይ የአዕዋፋት ዝርያዎችም በአካባቢው ይታያሉ፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...