Saturday, June 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትመፍትሔ የታጣለት የክለብ ደጋፊዎች ሁከት ዘንድሮም ቀጥሏል

መፍትሔ የታጣለት የክለብ ደጋፊዎች ሁከት ዘንድሮም ቀጥሏል

ቀን:

በእግር ኳስ ጨዋታ ታሪክ ውስጥ በተለያዩ አገሮች ሊግ ላይ የሚስተዋል የአልሸነፍነት ስሜት እንደየዘመኑ የራሱን ታሪክ አስፍሮ አልፏል፡፡ የሁሉም አገሮች ሊግ መልካም፣ መጥፎ፣ አስደንጋጭ፣ አከራካሪ፣ አሳዛኝና አስቆጪ የሆኑ ክንውኖች ነበሩት፡፡ በሁለት ክለብ ደጋፊዎች መካከል በሚፈጠር የአልሸነፍ ባይነት ስሜትና ፀብ አጫሪነት በስታዲየሞች የሚገኙትን ተመልካቾች ወደ ማያስፈልግ ሁከት ውስጥ ሲከት ይስተዋላል፡፡

በሌሎች አገሮች መካከል የሚፈጠረው የባላንጣነት ስሜት እግር ኳስና እግር ኳስን መሠረት ያደረገው ሚዛኑ ይደፋል፡፡

በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በተለይ በክልል ስታዲየሞች በርካታ ሁከቶች ተከስተው በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ የተመልካቾች አካል መጉደል፣ የስታዲየም መሠረተ ልማቶች መጥፋትና ለቀጣይ ውድድር ቂም ቋጥሮ፣ አንድ ክለብ ወደ ሌላ ክልል ስታዲየም ሄዶ ጨዋታ ሲያደርግ እስከመበቀል ደረጃ ተደርሷል፡፡ ሒደቱ በክልል ከተማ ሳይወሰን በአዲስ አበባም መስተዋሉ በብዙዎች ዘንድ አግራሞትን የጫረ ነገር ያደርገዋል፡፡

ከ2010 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በተለያዩ ስታዲየሞች በርካታ አሳዛኝ ክስተቶች መፈጠራቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ የዓምናው ጠባሳ ለዘንድሮ ተርፎ በተለይ ሁለቱ የሰሜን ክለቦች አማራና ትግራይ መካከል ጨዋታ ለማድረግ ቀላል አልነበረም፡፡

ለዚህም ሁለቱ ክለቦች 2010 ዓ.ም. ላይ በተፈጠረው ችግር ጨዋታቸውን በአዲስ አበባ ስታዲየም እንዲያደርጉ መገደዳቸውን ተከትሎ፣ የዘንድሮን መርሐ ግብር በአማላጅነት ማከናወናቸው ይታወሳል፡፡

እሑድ ሚያዝያ 13 ቀን 2011 ዓ.ም. በደቡብ ፖሊስና ወላይታ ድቻ መካከል ሊከናወን የነበረው 21ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በተመልካቾች መካከል በተፈጠረ ግጭት ወደ ሌላ ቀን ተዛውሯል፡፡ በሁከቱ በርካታ ተመልካቾች መጎዳታቸው እየተገለጸ ይገኛል፡፡

የድቻ እግር ኳስ ክለብ ቀደም ሲል በሐዋሳ በተከሰተ ችግር ምክንያት ጨዋታው በገለልተኛ ሜዳ ይሆንልኝ የሚል ጥያቄ ለብሔራዊ ፌዴሬሽን የጠየቀ ቢሆንም በሊግ ኮሚቴው ግን ተቀባይነት አላገኘም፡፡ ኮሚቴው ጨዋታው በወጣው መርሐ ግብር መከናወን እንዳለበት ቢያሳውቅም በደጋፊዎች ላይ በደረሰ ድብደባና እንዲሁም በክለቡ መኪና ላይ በደረሰ ጥቃት ባለመከናወኑ ወደ ሌላ ቦታ እንዲዘዋወር ተወስኗል፡፡

በድቻ ጥያቄ መሠረት ከደቡብ ፖሊስ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ሚያዝያ 17 በአዲስ አበባ ስታዲየም እንዲካሄድ ተወስኗል፡፡ በሌላኛው 21ኛ ሳምንት መርሐ ግብር በሐዋሳ ስታዲየም ሊከናወን የነበረው የሐዋሳና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ በተመሳሳይ ዕለት በአሰላ ከተማ እንደሚደረግ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡

በዚህም ምክያት የ22ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ወደ ማክሰኞ ሚያዝያ 22 ቀን መዘዋወራቸው ታውቋል፡፡

በተለያዩ ስታድየሞች የሚከሰቱን ሁከቶች ተከትሎ በርካታ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተለያዩ መድረኮች ቢሰናዱም ችግሮች ሲፈቱ አይስተዋልም፡፡

‹‹የስፖርታዊ ጨዋነት ምንጮች›› በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ በቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ማኅበር አዘጋጅነት ለሁለት ቀናት በሸራተን አዲስ ተካሂዷል፡፡ በዝግጅቱም ለስፖርታዊ ጨዋነት መንስዔ ናቸው ያሏቸውን ጉዳዮች ሲመክርበት ቆይቷል፡፡ በውይይቱም ለስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ዳኝነት አንደኛው መንስሔ መሆኑ ተገልጿል፡፡

መድረኩ እግር ኳስና ፖለቲካው ተቀላቅሏል፣ ፌዴሬሽኑ በሕጉ መሠረት አለመቅጣቱ እንደ ችግር ተጠቅሷል፣ በተለያዩ ስታዲየሞች ደግሞ ችግሩ ለማገርሸቱ ምክንያት መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

ጎሳ፣ ዘር፣ ፖለቲካን መሠረት ያደረጉ የክለብ አደረጃጀቶች፣ ዓርማቸውና መጠሪያቸው መስተካከል እንዳለበት አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ተመልካቾችም ቢሆን የሥነ ምግባር ትምህርት መማር እንዳለባቸውና ክለቦችም ግዴታቸውን መወጣት እንዳለባቸው ተጠቁሟል፡፡

የውይይት መድረኩ በቀጣይ ችግሮችን ይፈታል ተብሎ ቢታመንም፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተንሰራፋ ያለው የብሔር ፖለቲካ በእግር ኳስ ውስጥ ጣልቃ መግባት ጥንቃቄ ሊደረግበት እንደሚገባ በርካታ አስተያየቶች እየተሰጡ ይገኛሉ፡፡ ከዚህም ባሻገር በክልልና የከተማ ክለቦች መካከል አንዱ ወደ አንዱ ጨዋታ ሲያመራ ቋጥሮ የሚመጣው ‹‹ቂም በቀል›› መቆም እንዳለበት የባለሙያዎች አስተያየት ነው፡፡ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑም ተመጣጣኝ የሆነና ጥፋተኛው ክለብ በአግባቡ በመለየት ተገቢውን ቅጣት ማስተላለፍ እንዳለበት ተጠቅሷል፡፡ ክለቦችም ደጋፊዎቻቸውን ከመቆጣጠር አንጻር የራሳቸውን ኃላፊነት መወጣት ይኖርባቸዋል ተብሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...