አስፈላጊ ግብዓቶች
- ዶሮ
- ሽንኩርት
- አዋዜ (በርበሬ)
- ቅቤ
- ሎሚ ( ለማጠቢያ )
- ኮረሪማ
- ነጭ ሽንኩርትና ዝንጅብል
- ጨው
ለዳቦው
- የስንዴ ወይም የፉርኖ ዱቄት
- እርሾ
- ስኳር (ካስፈለገ)
- ጨው
- ዘይት
- ነጭ አዝሙድ
- ጥቁር አዝሙድ
አዘገጃጀት
- ዶሮው ፀጉሩ እንዲለቅ በፈላ ውኃ እየነከሩ መግፈፍና ብልቶቹን አውጥቶ በሎሚ መዘፍዘፍ፡፡
- ሽንኩርት በደቃቁ መክተፍና መጣድ ውኃውን ጨርሶ ጠቆር ሲል አዋዜና ቅቤ ጨምሮ ማቁላላት፡፡
- የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት ዝንጅብልና ኮረሪማ ጨምሮ ሞቅ ያለ ውኃ ጠብ እያደረጉ ማቁላላት፡፡
- የተዘፈዘፈውን ዶሮ አጥቦ፣ አለቅለቆና አድርቆ ቁሌቱ ውስጥ መጨመር፡፡
- ዶሮው ውኃ እንዳይኖረው ከቁሌቱ ጋር ካበሰልነው በኋላ ጨውን አስተካክሎ ማውጣት፡፡
ለዳቦው
- እርሾውን ለብ ባለ ውኃ ብርጭቆ ውስጥ መበጥበጥ፡፡
- ኩፍ ሲልልን ዱቄት፣ ስኳር፣ ጨው፣ ዘይት፣ ነጭ አዝሙድና ጥቁር አዝሙድ በደንብ አዋህዶ ማቡካት እናም ኩፍ እስኪል መጠበቅ፡፡
- ኩፍ ሲል መጋገርያው ላይ ግማሹን ሊጥ መዘርጋትና በስሎ የተዘጋጅውን ዶሮ መገልበጥ፡፡
- ከዚያም ቀሪውን ሊጥ እላዩ ላይ ገልብጦ በጥንቃቄ መሸፈንና ማብሰል
-
- ሰዋስው
-