Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊተፈናቃዮች በሚገኙባቸው ክልሎች የጤና ባለሙያ እጥረት ተከስቷል

ተፈናቃዮች በሚገኙባቸው ክልሎች የጤና ባለሙያ እጥረት ተከስቷል

ቀን:

በጎ ፈቃደኛ ጤና ባለሙያዎች እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀረበ

ተፈናቃዮች በሚገኙባቸው ክልሎች ከፍተኛ የጤና ባለሙያ እጥረት መኖሩን የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በየነ ሞገስ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ቁጥራቸው ከሦስት ሚሊዮን ከሚበልጡ ተፈናቃዮች 758,480 ያህሉ ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው የተመለሱ ቢሆንም፣ የጤና አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትም ሆነ ባለሙያዎች እጥረት ተከስቷል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከተመላሾቹ መካከል አብዛኞቹ የኦሮሚያ፣ የሶማሌና የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች ተፈናቃዮች መሆናቸውን፣ እነዚህንም በጤና ለመድረስ በጎ ፈቃደኛ ጤና ባለሙያዎች እንደሚያፈልጉ ተናግረዋል፡፡

በበጎ ፈቃድ ማገልገል የሚፈልጉ የጤና ባለሙያዎች በኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ድረ ገጽ ላይ ከሚያዝያ 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ እንዲመዘገቡም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በየአካባቢው የጤና ተቋማት እጥረት ቢኖርም ከክልሎችና አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የጤና አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን የገለጹት ዶ/ር በየነ፣ በደቡብ ክልል በጌዲኦ ዞን ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከሌሎች የጤና አገልግሎቶች በተጨማሪ የሥነ አዕምሮ ሕክምና በመሰጠት ላይ መሆኑንና በአጠቃላይ ከ660 በላይ ሰዎች መታከማቸውን ተናግረዋል፡፡ አገልግሎቱን ሌሎች ተፈናቃዮች በሚገኙባቸው ክልሎች ለማስፋፋት እንዲቻል ለአማራና ለሶማሌ ክልል የጤና ባለሙያዎች ሥልጠና መሰጠቱንም ገልጸዋል፡፡

በሶማሌና በደቡብ ክልሎች በአተት በሽታ ምልክቶች የተጠረጠሩ ታካሚዎች የነበሩ ሲሆን፣ ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር በመተባበር በሽታውን ለመመርመር የሚያስችሉ መሥሪያዎች እንዲሁም በሽታው ቢከሰት ለ210 ሺሕ ሰዎች ሕክምናውን ለመስጠት የሚያስችሉ መድኃኒቶች ወደ ክልሎቹ መላካቸውን፣ ሆኖም ምንም ዓይነት የአተት ወረርሽኝ እንዳልተከሰተ ገልጸዋል፡፡

በደቡብ ክልል 210,000 ተፈናቃዮችን ማከም የሚያስችሉ መደኃኒቶችና የጤና ግብአቶች በክልሉ የመድኃኒት ማከማቻ ለመጠባባቂያነት እንዲቀመጥ ተደርጓል፡፡

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከማሺ ዞን በግጭቱ ምክንያት ጤና ባለሙያዎች ለቀው በመውጣታቸውና የጤና ተቋማት ላይም ጉዳት በመድረሱ አገልግሎት የሚሰጡ የጤና ተቋማት ቁጥር እጅግ አናሳ ነው፡፡ በዞኑ ከሚገኙ 39 የጤና ተቋማት 11ዱ ጉዳትና ዘረፋ ደርሶባቸዋል፡፡ ከ227 የጤና ባለሙያዎች ውስጥ 115ቱ ለቀው ወጥተዋል፡፡ ይህንን ችግር ለመቅረፍ የጤና ባለሙያዎች ወደ ቦታው መላክ ተጀምሯል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ከታኅሳስ 22 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ እስካለፈው ሳምንት ድረስ በአጠቃላይ 3,611 ሰዎች በኩፍኝ በሽታ የተያዙ ሲሆን፣ በተሰጠው ክትባት አማካይነት የበሽታው ተዛማችነት ቀንሷል፡፡ በሮቤ ከተማ ግን በሽታው እንደቀጠለ ነው፡፡ በሶማሌ ክልል ከታኅሣሥ ወር ጀምሮ በበሽታው የተያዙት ቁጥር 1,470 ደርሷል፡፡ ክትባት በተሰጣቸው ቦታዎች ተዛማችነቱ የቀነሰ ቢሆንም፣ በሸበሌና በጀራር ዞኖች በሽታው እንደቀጠለ ነው፡፡ ለሁለቱም ክልሎች ክትባት ለመጀመር የሚያስችል ቅድመ ዝግጅትም ተጠናቋል፡፡

አፋር ክልል አዳር ወረዳ በኢልውኃ ከተማ የተከሰተው የችኩንጉኒያ ትኩሳት በሽታ ከየካቲት 29 እስከ ሚያዝያ 14 ቀን 2011 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር በድምሩ 1,118 ደርሷል፡፡ ሆኖም ከባለፉት ሳምንታት ጋር ሲነፃፀር አዲስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር ቀንሷል፡፡

ዘንድሮ ተፈናቃይ ወገኖች ለሚገኙባቸው ክልሎች 528 ሚሊዮን ብር ወጪ መሆኑንም ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...