Saturday, December 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናዕጩ ሐኪሞች ወከባ እያጋጠመን ነው አሉ

ዕጩ ሐኪሞች ወከባ እያጋጠመን ነው አሉ

ቀን:

የመብት ጥያቄ  ያነሱ ዕጩ ሐኪሞች ድብደባና በፀጥታ አካላትም ወከባ እያጋጠማቸው እንደሆነ ገለጹ፡፡ በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ዕጩ ሐኪሞች ‹‹መብታችን ይከበር›› የሚል ጥያቄ አንግበው ሰላማዊ ሠልፍ በወጡበት ጊዜ ድብደባ እንደደረሰባቸው፣ በጂማ ዩኒቨርሲቲ የሚሠሩ ሁለት ሌሎችም በአስታማሚዎች መደብደባቸውን፣ ድርጊቱን ለመቃወም ሰላማዊ ሠልፍ የውጡም በፀጥታ አካላት መዋከባቸውን ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

ድብደባ ከደረሰባቸው መካከል ለታካሚዎች ደም በመለገስ የሚታወቅ ወጣት ይገኝበታል ተብሏል፡፡ ከሳምንታት በፊት የተጀመረው የሐኪሞች የመብታችን ይከበር ጥያቄ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

 በአርሲ፣ በጂማ፣ በመቀሌ፣ በሃሮማያ፣ በቅዱስ ጳውሎስ፣ በጥቁር አንበሳና ሌሎችም በዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች የሚማሩ ዕጩ ሐኪሞች ንቅናቄውን ተቀላቅለዋል፡፡ በቤተል ቲቺንግ ሆስፒታል፣ በሃያት፣ በሳንቴና በአፍሪካ ሜዲካል ኮሌጆች ከፍለው የሚመሩ የሕክምና ተማሪዎችም ድጋፋቸውን ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም በግል ኮሌጆች ሕክምና የተማሩትን ከዚህ በፊት በነበረው አሠራር  መንግሥት ይመድባቸው እንደነበር፣ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት አሠራሩ መቀየሩንና ይህም እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በግል ኮሌጆች ተምረው የተመረቁ 450 ሥራ ፈተው የተቀመጡ የሕክምና ምሩቆች እንዳሉ እየተነረ ነው፡፡ የሐኪሞች እጥረት በከፍተኛ ደረጃ ባለባት ኢትዮጵያ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በሐኪሞችና በሕዝቡ መካከል ያለው ንፅፅር አንድ ሐኪም ለ15 ሺሕ ሰው ነው፡፡

በቀን ያለ እረፍት ለተከታታይ ለ36 ሰዓታት እንደሚሠሩ የሚገልጹት ሐኪሞች፣ አምሽተው ሲሠሩ አበል እንደማይከፈላቸው ገልጸዋል፡፡ በተለይ በጥቁር አንበሳ ሪፈራል ሆስፒታል ተመድበው የሚሠሩ ደግሞ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች እንኳ እንደማይታዘዟቸው፣ የነርሶችንና የተላላኪዎችን ሥራ ደርበው እንዲሠሩ እንሚገደዱ ሪፖርተር ያነጋገራቸው ሐኪሞች ገልጸዋል፡፡

‹‹የሕዝቡ የጤና ችግር እንዲፈታ፣ የእኛ ሁለንተናዊ መብት እንዲከበር እንፈልጋለን፤›› ሲሉም ተደምጠዋል፡፡ በቂ የሕክምና መሣሪያና የተለያዩ ቁሳቁሶች እጥረት ባለበት ሁኔታ እንዲያገለግሉ መደረጉ ታካሚውን ለእንግልት፣ ዕጩ ሐኪሞችን ደግሞ ለተለያዩ የጤና ችግሮች እየዳረጉ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ ዕጩ ሐኪሞች ያለ በቂ የደኅንነት መጠበቂያ ግብዓት ታማሚዎችን ሲያክሙ ለኤችአይቪ፣ ለሄፒታይተስ፣ ለቲቢና ለመሳሉት በሽታዎች እንደሚጋለጡ ይናገራሉ፡፡

ሐኪሞች እንዲከፍሉ የሚጠበቀው 427,000 ብር የወጪ መጋራት ከአቅም በላይ እንደሆነና ሌላው ችግር መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ ‹‹36 ሰዓታት ሠርተን ደከመን ማለት አንችልም፡፡ ትንሽ ዘግየት ካልን እንኳ በእኛ ጊዜ ይኼንን ማድረግ ዓመት ያስደግም ነበር፡፡ እኛ በሥራ ቀን እስከ ማታ ሦስት ሰዓት አንወጣም ነበር፤›› እንደሚባሉ ‹‹ሐኪም›› በተሰኘው በማኅበራዊ ድረ ገጻቸው አስነብበዋል፡፡

 ‹‹ይኼንን ያህል ያለ እረፍት መሥራታችን ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለታካሚዎችም ጥሩ አይደለም፤›› በማለት፣ በተረጋጋ አዕምሮ መሥራት ቢችሉ ውጤቱ ያማረ ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

‹‹የልጅነት ህልሜን አታጨናግፉት››፣ ‹‹ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍትሕ እንፈልጋለን››፣ ‹‹ሙያችን ይከበር››፣ ‹‹ጥያቄያችን የደመወዝ ብቻ አይደለም››፣ ‹‹ኢንተርኖች ሰዎች ናቸው ማሽን አይደሉም›› የሚሉ መፈክሮችን ይዘው ሠልፍ ወጥተዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...