Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናከመንግሥት ግዥ ጋር በተያያዘ በከፍተኛ ሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ኃላፊዎችና ባለሀብቶች ንብረትና ገንዘብ...

ከመንግሥት ግዥ ጋር በተያያዘ በከፍተኛ ሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ኃላፊዎችና ባለሀብቶች ንብረትና ገንዘብ ታገደ

ቀን:

39 ግለሰቦችና 16 ድርጅቶች ዕግድ ተጥሎባቸዋል

በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የመንግሥት ግዥ፣ ንብረት አስተዳደርና ማስወገድ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን፣ የመድኃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ፣ የውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ኃላፊዎችና ቤተሰቦቻቸው ንብረትና በባንኮች የሚገኝ ገንዘብ ዕግድ ተጣለበት፡፡

የአራቱም ተቋማት ኃላፊዎች ማለትም የመንግሥት ግዥ ንብረት አስተዳደርና ማስወገድ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ይገዙ ዳባና አራት ቤተሰቦቻቸው፣ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ኃላፊ አቶ መንግሥቱ ከበደና ሦስት ቤተሰቦቻቸው፣ የቀድሞ መድኃኒት ፈንድና አቅርቦት ኃላፊ አቶ ኃይለ ሥላሴ ቢሆንና ስድስት ቤተሰቦቻቸው፣ የውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ኃላፊ የነበሩት አቶ አታክልት ተካና አራት ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ ሌሎችም ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎችና ባለሀብቶች በአጠቃላይ 39 ሰዎች ቋሚ፣ ተንቀሳቃሽና በተለያዩ ባንኮች የተቀመጡ ገንዘቦች ዕግድ ተጥሎባቸዋል፡፡

ሆቤካ ኮንስትራክሽን፣ ጃይንት ኧርዝ ሙቪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ዕቁባይ ዮሐንስ ኮንስትራክሽን፣ ማኅተቤ አርጋቸው ኮንስትራክሽን መሣሪያዎች አከራይ፣ አብርሃም ኃይሌ ኮንስትራክሽን መሣሪያዎች አከራይ፣ ክፍሌ አብርሃም አጠቃላይ አስመጪና ላኪ ኮንስትራክሽን መሣሪዎች አከራይ ድርጀት፣ ዮናስ ኃይሌ ኮንስትራክሽን ማሽነሪ አከራይን ጨምሮ በአጠቃላይ 16 ድርጅቶችና ባለቤቶቻቸው ንብረት እንዳይንቀሳቀስ ዕግድ ተጥሎበታል፡፡

የመንግሥት ግዥ ንብረት አስተዳደርና ማስወገድ አገልግሎትና የኢትዮጵያ ንግድ ኮርፖሬሽን ኃላፊዎች፣ ከ400,000 ሜትሪክ ቶን ስንዴ ግዥ ጋር በተገናኘ በአጠቃላይ 23,798,376 ብር ጉዳት ማድረሳቸው ተገልጿል፡፡ የመድኃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ ደግሞ የግዥ መመርያን በመተላለፍ የ92,502,316 ብር፣ በውስን ጨረታ የ23,124,196 ዶላርና የ24,833,834 ብር መድኃኒት በመግዛት፣ እንዲሁም ለመድኃኒት መጋዘን ግንባታ በማለት ዕጥፍ ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ክፍያ በመፈጸም፣ በመንግሥት ላይ ጉዳት ማድረሳቸው ተጠቁሟል፡፡

የውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ደግሞ ያላግባብ በቦርድ የፀደቀ ዕቅድ ሳይኖር ከ58 ሚሊዮን ብር በላይ የግንባታ ብረት በመግዛት፣ ለከፍተኛ ክሊኒኮች የማያስፈልጉ መሣሪያዎችን በ4,192,876 ብር በላይ በመግዛትና ከስፔሲፊኬሽን ውጪ ከ14 ሚሊዮን ብር በላይ ክሬን በመግዛት በመንግሥት ላይ ጉዳት በማድረስ ተጠርጥረው፣ የ14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ተፈቅዶባቸው ለሚያዝያ 24 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

ተጠርጣሪዎች በፍርድ ቤት ትዕዛዝ በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያደረገባቸው ያለው የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን ሲሆን፣ መዝገቡን እየተከታተለ ትዕዛዝ የሚሰጠው ደግሞ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አሥረኛ ወንጀል ችሎት ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...