Tuesday, April 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናከፍተኛ የዲሲፕሊን ጥፋት በመፈጸማቸው ከዳኝነት እንዲሰናቡ የተጠየቀባቸው ዳኛ ጉዳይ በድጋሚ እንዲታይ ተወሰነ

ከፍተኛ የዲሲፕሊን ጥፋት በመፈጸማቸው ከዳኝነት እንዲሰናቡ የተጠየቀባቸው ዳኛ ጉዳይ በድጋሚ እንዲታይ ተወሰነ

ቀን:

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት በማሰብ ደረቅ ቼክ የሰጡ ተከሳሾችን የዳኝነት ኃላፊነታቸውን በመጠቀም በሙያዊ ግዴታቸው ላይ ከባድ የዲሲፕሊን ጥሰት በመፈጸማቸው ከዳኝነት እንዲሰናበቱ የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ያሳለፈውን ውሳኔ በተመለከተ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛን ከሥራ ለማሰናበት ወይም ላለማሰናበት በቀረበ ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ የሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ቋሚ ኮሚቴ  ያቀረበውን ውሳኔ ሐሳብ ሳይቀበለው ቀረ፡፡

ምክር ቤቱ ሐሙስ ሚያዝያ 17 ቀን 2011 ዓ.ም. ባካሄደው 36ኛ መደበኛ ስብሰባ አቶ አየለ ዱቦ የተባሉ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛን ስንብት አስመልክቶ በሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ቋሚ ኮሚቴ የቀረበለት የውሳኔ ሐሳብ ላይ በጥልቀት የተወያየ ሲሆን፣ ጉዳዩ የምክር ቤት አባላቱን ባልተለመደ ሁኔታ በማከራከሩ ለውሳኔ አስቸጋሪ ሆኖ ተስተውሏል፡፡

ፓርላማው የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛውን ከሥራ እንዲያሰናብት የፌዴራል ዳኞች አስተዳዳር ጉባዔ ያቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ፣ ጥቅምት 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ተወያይቶ ለቋሚ ኮሚቴ መርቶት ነበር፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በውሳኔ ሐሳቡ መሠረት በዳኛው ስንብት ላይ ይወሰናል ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም፣ በውሳኔ ሐሳቡ ዝርዝር ጉዳዮች አባላቱ ስምምነት ላይ ባለመድረሳቸው ቋሚ ኮሚቴው ክርክር የተነሳባቸውን ነጥቦች ድጋሚ በማመን የውሳኔ ሐሳቡን አሻሽሎ እንዲያቀርብ ነው ውሳኔ ያስተላለፈው፡፡

ከስድስት ወራት በላይ የተመራለትን ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ ሲመለከት የቆየው ቋሚ ኮሜቴው፣ በዝርዝር ያከናወናቸውን የምርመራ ሥራዎችና የደረሰባቸውን ውሳኔዎች የቋሚ ኮሚቴ አባሏ በንባብ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡

በምርመራ ሥራው ወቅት በቋሚ ኮሚቴው አባላት በዝርዝር ከታዩ ጉዳዮች ውስጥ ዳኛው አቶ አየለ በዳኝነት ሥራ ተመድበው በሠሩበት ወቅት፣ ከፍተኛ የዲስፒሊን ጥፋትና ሙያዊ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባለመወጣት የሥነ ምግባር ጥፋት ፈጽመዋል የሚሉ ይገኙበታል፡፡ ከእነዚህም ጥፋቶች ውስጥ ዳኛው በሌላ ፍርድ ቤት የተወሰነን ጉዳይ ከሌሎች ጋር ‹‹በጣምራ›› እንዲታይ አድርገዋል፣ የክስ ሒደት አቋርጠዋል፣ በሕግ የተከለከለ ዋስትናን ለተጠርጣሪዎች ፈቅደዋል፣ ሰጥተዋል፣ የክስ ሒደት አቋርጠዋል፣ በሕግ የተከለከለ ዋስትና ለተጠርጣሪዎች ፈቅደዋል፣ የክስ መዝገቦች እልባት ሳያገኙ እንዲመክኑ አድርገዋል የሚሉ ይገኙበታል፡፡

በአንፃሩ ለቋሚ ኮሚቴው በአካልና በጽሑፍ ስለቀረበባቸው ክሶች ዳኛው አንድ በአንድ የሰጡት ምላሽ በቋሚ ኮሚቴው ሪፖርት ተዘርዝሯል፡፡ ዳኛው የሥነ ምግባር ጥሰትም ሆነ ከባድ የዲስፒሊን ጥፋት በመሥራት ሙያዊ ሥነ ምግባራቸውንም ሆነ ኃላፊነታቸውን አልተወጡም የሚሉ ክሶችን ተከራክረው፣ አብዛኞቹ ክሶች ሙያዊ ሥነ ምግባራቸውና ሕግ በሚፈቅደው አግባብ ያከናወኗቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔም ከቀረቡትና ከላይ ከተጠቀሱት ክሶች በተጨማሪ፣ ቋሚ ኮሚቴው ከተከሳሹ ዳኛ በኩል ያሉ ምላሾችንም በቃልና በጽሑፍ መቀበሉን የቋሚ ኮሚቴ አባሏ አብራርተዋል፡፡

ዳኛው የመደመጥ መብታቸው ተጠብቆ ጉዳያቸውን በአካልና በጽሑፍ ማቅረባቸውን የገለጸው ቋሚ ኮሚቴው፣ ጉዳዩ ከከባድ ዲሲፕሊን ጥፋትነት ይልቅ በፍሬ ነገር ሊታይ የሚችል የነበረ መሆኑን ጠቅሰው ዳኛው መከራከራቸውን አባሏ ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም ዳኛው የዲሲፕሊን ጥፋት መሥራታቸውን ያልካዱ መሆኑን ገልጸው፣ ጥፋቱ በፓርላማ ማሰናበት የሚለው ዕርምጃ ላይ ሳይደርስ በመደበኛ የዲሲፕሊን ዕርምጃ መታለፍ የነበረበት መሆኑን ተከራክረው እንደነበርም በቋሚ ኮሚቴው ሪፖርት ተጠቅሷል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው የራሱን ውሳኔ አስመልክቶ ባቀረበባቸው የውሳኔ ሐሳቦች፣ ሁሉም የምክር ቤቱን አባላት ወደ ተጋጋለ ክርክር እንዲገቡ አድርጓል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔን በመጥራት በቀዳሚነት በቀረበው የጉባዔው የውሳኔ (ረቂቁ) ላይ በዝርዝር በመወያየት፣ ተጨማሪ የምርመራ ሥራዎች ማከናወኑን አባሏ አብራርተዋል፡፡

ነገር ግን የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ አባላት ውስጥ ውሳኔውን ያስተላለፉት የቀድሞ አመራር ያልተገኙ ቢሆንም፣ የወቅቱ የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ሰብሳቢዋ ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ቋሚ ኮሚቴው በጠራው ስብሰባ ላይ ተገኝተው እንደነበር ገልጸዋል፡፡

ነገር ግን የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ውሳኔውን ያካሄደው በቀድሞው አመራር ስለነበረ፣ አዲሷ ሰብሳቢ ከቋሚ ኮሚቴው ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠታቸው ታውቋል፡፡

በዚህ መሠረት በአቶ አየለ ላይ የተወሰነው የስንብት ውሳኔ እሳቸው ከመሾማቸው በፊት የተወሰነ መሆኑን በመጥቀስ፣ ምክር ቤቱ የራሱን ውሳኔ መስጠት እንደሚችል ወ/ሮ መዓዛ መናገራቸውን የቋሚ ኮሚቴ አባሏ አመልክተዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በስተመጨረሻ የደረሰባቸውን ውሳኔዎች በተመለከተ የቋሚ ኮሚቴ አባሏ እንደገለጹት፣ የዳኞች አስተዳደር ውሳኔ  በዳኛው ላይ ቅድመ ምርመራ ሲያደርግ የአቶ አየለን የመደመጥ መብት አለማክበሩን በቋሚ ኮሚቴው አባላት ግንዛቤ ተወስዷል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም አቶ አየለ ከፍርድ ቤት ውሳኔ ጋር የወሰኗቸውም ሆኑ ያስተላለፉት ትዕዛዝ ስህተት ያለበት ቢሆን እንኳን፣ የፍርድ ቤት ውሳኔያቸው ከሌሎች የውሳኔ ሐሳቦች ጋር መቅረብ የማይገባው መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው ተረድቷል ሲሉ ለምክር ቤቱ ገልጸዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው የመጨረሻ ውሳኔ ጥቅል ሐሳብ በማንበብ በዳኛ አየለ ላይ ጉባዔው የወሰነውን ውሳኔ ቋሚ ኮሚቴ ያልተቀበለው መሆኑን ገልጸው፣ በዚህ መሠረት የፌዴራል ዳኞች አስተዳዳር ጉባዔ የዳኛውን ሕገ መንግሥታዊ የመደመጥ መብት በማክበር ጉዳዩን በድጋሚ እንዲመለከት ቋሚ ኮሚቴው በአብላጫ ድምፅ መወሰኑን ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም ምክር ቤቱ ውሳኔውን ተቀብሎ እንዲያፀድቀው ቋሚ ኮሚቴው ከጠየቀ በኋላ ከአባላቱ በርካታ ጥያቄዎች ተነስተውበታል፡፡

ጥያቄዎቹ ከዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ውሳኔ ውስጥ ከተዘረዘሩት ጉዳዮች ባሻገር፣ ቋሚ ኮሚቴው የተመራለትን ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ ዘግቷል የሚሉ ትችቶች ተሰንዝረውበታል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችል ሥልጣን እንደሌለው በመጥቀስ፣ ጉዳዩን ወደ ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ መመለሱን አስታውቋል፡፡ አለመቀበሉን በግልጽ አሳውቆ ለምክር ቤት ያቅርብ በመባሉ የጉባዔውን የውሳኔ ሐሳብ ለምክር ቤቱ ማቅረቡን አስታውቋል፡፡

በዕለቱ በተገኙ የምክር ቤት አባላት በውሳኔ ሐሳቡ ላይ ሰፊ ክርክር ተደርጐ ብዛት ያላቸው ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡ ክርክሩ በቀላል እንደማይቆም ያስተዋሉት አፈ ጉባዔው ከተነሱት አጠቃላይ ሐሳቦች በመጭመቅ በአራት ጉዳዮች ላይ ምክር ቤቱ በተናጠል ድምፅ እንዲሰጥ ሐሳብ አቅርበው ተቀባይነት ሊያገኙ ችለዋል፡፡

በዚህም መሠረት ቋሚ ኮሚቴው ግልጽ ያልሆነ የውሳኔ ሐሳብ ካለማቅረቡም በላይ ጉዳዩን ስለማጓተቱ የጠቀሰው ምክር ቤቱ፣ ሐሳቡ ውድቅ ይደረግ ወይስ ጉባዔው በድጋሚ ይመልከተው፣ ወይም ቋሚ ኮሚቴው መልሶ ዓይቶ የውሳኔ ሐሳብ ይስጥ በሚለው ላይ ድምፅ እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡

በተቆጠረው ድምፅ ውጤት መሠረት 12 የምክር ቤቱ አባላት የዳኞች አስተዳደር ጉባዔን ውሳኔ አንቀበለውም ሲሉ፣  130 አባላት ዳኛው የመደመጥ መብት ተነፍጎኛል በማለታቸው የመደመጥ መብታቸው ተከብሮ ጉዳዩ  እንደገና ይታይላቸው በማለት ድምፅ ሰጥተዋል፡፡ እንዲሁም  ቋሚ ኮሚቴው ጉዳዩን በድጋሚ ራሱ ዓይቶ የመጨረሻ ውሳኔ እንዲያቀርብ ያሉ 134 አባላት አብላጫ ቁጥር ያለውን ድምፅ ሲሰጡ፣ አራት አባላት ደግሞ ዳኛው ይሰናበቱ የሚል ድምፅ ሰጥተዋል፡፡ አምስት አባላት ደግሞ ድምፀ ተዓቅቦን መርጠዋል፡፡

በውጤቱም መሠረት ጉዳዩን ቋሚ ኮሚቴው በድጋሚ ዓይቶ የመጨረሻ የውሳኔ ሐሳብ ይዞ እንዲቀርብ  ምክር ቤቱ  በ134 ድምፅ  ወስኗል፡፡

ከአዘጋጁ፡- ረቡዕ ሚያዝያ 16 ቀን 2011 ዓ.ም. በወጣው ዕትም ‹‹ከፍተኛ የዲሲፕሊን ጥፋት በመፈጸማቸው ከዳኝነት እንዲሰናበቱ የተጠየቀባቸውን ዳኛ ጉዳይ በድጋሚ እንዲታይ ፓርላማው ወሰነ›› በሚል ርዕስ የወጣው ዘገባ ስህተት ስለሆነ፣ ከላይ በቀረበው ዘገባ መሠረት እንዲታረም እናሳስባለን፡፡ ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡

የዝግጅት ክፍሉ

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...