Wednesday, June 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናየ17 ሰዎች ሕይወት ያለፈበት የመተከል ግጭት ቆመ

የ17 ሰዎች ሕይወት ያለፈበት የመተከል ግጭት ቆመ

ቀን:

በትግራይ ፖሊስ እግር ኳስ ቡድን ላይ በተፈጸመ ጥቃት ሕይወት አለፈ

በቤኑሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ከሚያዝያ 17 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ፣ የግል ፀብን አስታኮ የተነሳ ግጭት የ17 ሰዎች ሕይወት ካለፈ በኋላ መቆሙን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ግጭቱ መጀመርያ በዳንጉር ወረዳ አይሰካ በሚባል አነስተኛ ቀበሌ ውስጥ መነሳቱን፣ ቀጥሎም ወደ ሌሎች የወረዳው ቀበሌዎች መስፋፋቱን የክልሉ የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አበራ ባይታ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

በቀበሌው ሚያዝያ 17 ቀን የጭነት መኪና አሽከርካሪና ተጠቃሚ በሆኑ ሁለት ግለሰቦች በትራንስፖርት ክፍያ ምክንያት በተፈጠረ አለመግባባት ግጭቱ መቀስቀሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በግለሰቦቹ አለመግባባት ምክንያት ወደ ቦታው  የፌዴራል ፖሊስ አባላት ለማረጋጋት መላካቸውን፣ በወቅቱም አንዳንድ ግለሰቦች ከፌዴራል ፖሊስ አባላት መሣሪያ ለመንጠቅ ሙከራ ማድረጋቸውንና በዚህም ሳቢያ ዕርምጃ መወሰዱን አቶ አበራ ገልጸዋል፡፡ በሥፍራው ነበርን ያሉ ግለሰቦች ግን አንድ የፖሊስ አባል የትራንስፖርት ተጠቃሚውን በመማታቱ ምክንያት ግጭቱ መቀስቀሱን ይናገራሉ፡፡

ግጭቱ ወደ ተለያዩ የዳንጉር ወረዳ አካባቢዎች በመስፋፋቱ፣ የሰው ሕይወትና ንብረት መጥፋቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ግጭቱ ለተከታታይ አራት ቀናት በመቆየቱም ብዛት ያላቸው ንፁኃን ዜጎች ሕይወት ማለፉ ተገልጿል፡፡  

ግጭቱን በማስፋፋትና በማስተባበር የተጠረጠሩ 15 ያህል ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን፣ ከክልሉ የፀጥታ ቢሮ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከ15 ግለሰቦች ውስጥ አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል ይገኝበታል ተብሏል፡፡

ላለመግባባቱና ለግጭቱ ምክንያት ነበሩ የተባሉት ሁለቱ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ስለመዋላቸው መረጃ እንደሌላቸው፣ አቶ አበራ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

በተለይ ከተጎጂዎቹ መሀል የአማራ ብሔር ተወላጆች ስላሉ፣ ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተወጣጡ የመንግሥት ኃላፊዎች ወደ ክልሉ መሄዳቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ግጭቱ በነበረባቸው አካባቢዎች የመከላከያ ሠራዊት የገባ ሲሆን፣ በተጨማሪም በሥፍራው የሚገኘው ፌዴራል ፖሊስ የፀጥታ ማስጠበቅ ሥራውን እያከናወነ እንደሆነ አቶ አበራ አስረድተዋል፡፡

በቀጣይ ለግጭቱ መንስዔ የሆኑና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ምርምራ ተደርጎ ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል ሲሉ የፀጥታ ኃላፊው አክለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የተከሰተው ግጭት ሙሉ በሙሉ ቆሟል ብለዋል፡፡

በተያያዘ ዜና ሚያዝያ 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ወደ ትግራይ ክልል በመኪና ይጓዙ በነበሩ የዋልታ ፖሊስ እግር ኳስ ቡድን አባላት ላይ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት፣ አማኑኤል ብርሃኔ የተባለ የቡድኑ አባል ሲገደል በአራቱ ላይ ደግሞ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡

የእግር ኳስ ቡድኑ አባላት በደብረ ብርሃን የነበራቸውን ጨዋታ አጠናቀው ወደ ትግራይ ክልል ሲመለሱ፣ በአፋር ክልል ልዩ ስሙ ገዋኔ የተባለ ቦታ ላይ ሲደርሱ ጥቃት እንደተከፈተባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

የትግራይ ብሔራዊ ክልል ባወጣው መግለጫ በተፈጸመው ጥቃት ማዘኑንና ጥቃት ፈጻሚዎቹ ለሕግ እንዲቀርቡ ጠይቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...