Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየአፋር እግር ኳስ ክለብ ከ‹‹ሜዳዬ›› ውጪ አልወዳደርም አለ

የአፋር እግር ኳስ ክለብ ከ‹‹ሜዳዬ›› ውጪ አልወዳደርም አለ

ቀን:

የአፋር እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በቁጥር ካእ/0061/11 ሚያዝያ 20 ቀን 2011 ዓ.ም. በጻፈው ደብዳቤ ባለው የደኅንነት ሥጋት ምክንያት የካዳባ ቡድን ከሜዳው ውጪ ተንቀሳቅሶ እንደማይጫወት አስታወቀ፡፡ የካዳባ እግር ኳስ ቡድን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ወይም አንደኛ ሊግ በምድብ ‹‹ለ›› ተደልድሎ ክልሉን በመወከል ሲወዳደር መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በሥሩ ከሚያወዳድራቸው ሊጎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ወይም አንደኛ ሊግ አንዱ ሲሆን፣ በስድስት ምድብ ተከፋፍለው በአጠቃላይ 58 ቡድኖች ይገኛሉ፡፡ ሌላው አካባቢያዊ ቀረቤታን ግምት ውስጥ በማስገባት በሦስት ምድብ የተከፈለው ከፍተኛው ሊግ 36 ቡድኖች ሲሆኑ፣ ፕሪሚየር ሊግ የሚለውን ስያሜ የያዘው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ደግሞ 16 ቡድኖች የሚሳተፉበት ነው፡፡ ይሁንና ቡድኖች በተለይም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከእግር ኳሳዊ ይልቅ አካባቢያዊ ስሜት እየተላበሱ እግር ኳሱ የብጥብጥና ሁከት ዓውድማ፣ አለፍ ሲልም ለሕይወትና ለከፍተኛ የንብረት ውድመት መንስዔ እየሆነ ይገኛል፡፡

የእግር ኳሱን መድረክ ሰላማዊ ለማድረግ ከክልል እስከ አገር አቀፍ መድረኮች ተዘጋጅተው መንስዔውና መፍትሔው ላይ ውይይቶች ቢደረጉም፣ ነገሮች በተቃራኒ እየሆኑ እግር ኳሱን ተከትሎ በሚፈጠሩ ችግሮች ዜጎች ከአንዱ ክልል ወደ ሌላው ክልልና ከተማ በሰላም ወጥተው በሰላም የሚመለሱበት ዕድል ጠብቧል፣ ዜጎች ለከፋ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እየተዳረጉ ይገኛል፡፡ ባለፈው ሳምንት በትግራይ የዋልታ ፖሊስ እግር ኳስ ቡድን ተጨዋቾች ላይ በአፋር ክልል ገዋኔ አካባቢ የተፈጠረው ክስተት የዚህ አንድ አካል ስለመሆኑ ጭምር የሚናገሩ አሉ፡፡

የአፋር እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ በትግራይ ዋልታ ፖሊስ እግር ኳስ ቡድን ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ በኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ በምድብ ‹‹ለ›› እየተወዳደረ የሚገኘውን የካዳባ እግር ኳስ ቡድን አሁን በአገሪቱ ያለው የደኅንነት ሥጋት እስኪረጋጋ ከሜዳው ውጪ ጨዋታ እንደማያደርግ ለብሔራዊ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡ የክልሉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለዚህ ውሳኔው ምክንያት ብሎ ያስቀመጠው፣ ቡድኑ መቀመጫውን ካደረገበት አሳይታ ተነስቶ ከሜዳው ውጭ ለሚደርጋቸው ጨዋታዎች ሲንቀሳቀስ ማለትም ከገዳማይቱ እስከ እንደፉአ አዳይቱና አካባቢው የሚገኙ መንገዶች የአደጋ ቀጣና በመሆናቸው እንደሆነ በግልጽ ይፋ አድርጓል፡፡

ደብዳቤው አክሎ እንደገለጸው ከሆነ፣ የክልሉ ቡድን በእነዚህ አካባቢዎች ተደጋጋሚ የጥቃት ሙከራዎች አጋጥመውት በፈጣሪ ኃይል ተርፏል፡፡ ከእንግዲህ ግን መንግሥት የኢትዮ ጂቡቲ መንገድ የደኅንነት ዋስትና እስኪሰጥ ድረስ ቡድኑ ቀሪዎቹን የተዟዙሮ ጨዋታዎች እንደማያደርግ አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኩባንያ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ባንኮች ውጤታማነት

የጠቅላላ ጉባኤ፣ የጥቆማና ምርጫ ኮሚቴ፣ የተቆጣጣሪ ቦርድ፣ የዳይሬክተሮች ቦርድና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...