Saturday, June 15, 2024

ለክቡር ሚኒስትሩ አንድ ባለሀብት ስልክ ደወለላቸው

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሾፌራቸው ጋር እያወሩ ወደ ቢሮ እየሄዱ ነው]

 • እንኳን አደረስዎት ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • እንኳን አደረሰህ፡፡
 • ምነው ፊትዎት?
 • ምን ሆነ?
 • በጣም ተጫጭኖዎታል፡፡
 • ያስታውቅብኛል ማለት ነው?
 • ምኑ ክቡር ሚኒስትር?
 • ሕመሙ ማለቴ ነው፡፡
 • ለዚያ ነው እንዴ ትናንት የቀሩት?
 • ይኼን ጮማ አገኘሁ ብዬ ስውጥ ነበር፡፡
 • እ. . .
 • ቀኑን ሙሉ መፀዳጃ ቤት ስመላለስ ነው የዋልኩት፡፡
 • ምን ተገኝቶ?
 • ኧረ ተወኝ፡፡
 • እውነቴን እኮ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • የመጣልኝ የፍየል ሙክት፣ ሙክት እንዳይመስልህ፡፡
 • እኮ ከየት?
 • እሱ አይጠየቅም፡፡
 • ማለቴ ጸሐፊዎ እኮ ምንም የበዓል ሥጦታ እንዳልመጣልዎት ነበር የነገረችኝ፡፡
 • እሱማ ልክ ነህ፡፡
 • ታዲያ ይኼኛው ሙከት ከየት መጣ?
 • አንድ ባለሀብት ሰርፕራይዝ አደረገኝ፡፡
 • እ. . .
 • ፈጣሪ ልመናዬን ሰምቶት ነበር፡፡
 • ባለሀብቱ ልመናዎን ሰምቶ ነበር ቢባል አይሻልም?
 • ዋናው ልመናዬ መሰማቱ ነው፡፡
 • ባለሀብቱም በተራው መለመኑ አይቀርም፡፡
 • ምንድነው የሚለምነው?
 • መሬት ነዋ፡፡
 • ምን ችግር አለ ላልጠፋ መሬት?
 • ጀማሪ ባለሥልጣን እኮ ይኼ ነው ችግሩ፡፡
 • እንዴት?
 • እርስዎ በሬ ቢያመጣልዎት ክልል ነው የሚሰጡት ማለት ነው፡፡
 • እ. . .
 • ወዲህ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ለማንኛውም በጣም አስደሳች በዓል ነበር፡፡
 • ሌላ ምን አደረጉ?
 • ስነግርህ ያን የሙክት ፍየል ጥሬ እየጎረድኩ በውስኪ ሳወራርደው ነበር፡፡
 • የደላው ሙቅ ያኝካል አሉ፡፡
 • አንተስ ጋ በዓል እንዴት ነበር?
 • ምንድን ነበር በዓል ክቡር ሚኒስትር?
 • መቼም ቀልደኛ ነህ አንተ?
 • የእውነቴን ነው እኮ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ታዲያ በዓል አላከበርክም?
 • የበግ ዋጋ ሰባት ሺሕ መሆኑን ሰምቼ እኔም እንደ ምርጫ አራዘምኩ፡፡
 • ምኑን?
 • ፆሙን ነዋ፡፡
 • ፆሙን አልፈታሁም እያልከኝ ነው?
 • ክፍል ሁለትን ልጀምር ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • የምን ፆም ልትጀምር?
 • የረመዳን!

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚስታቸው ጋር እያወሩ ነው]

 • ስብሰባ ትሰበሰባላችሁ ግን?
 • የምን ስብሰባ?
 • ማለቴ የፓርቲ ስብሰባ ነው፡፡
 • በሥራ እንጂ በስብሰባ የሚባክን ጊዜ የለንም ስንል አልሰማሽም?
 • ሥራ ግን እየሠራችሁ ነው አገር እንደዚህ የሚታመሰው?
 • ምን ለማለት ፈልገሽ ነው?
 • እኔማ የአገሪቱን ሁኔታ ተቀምጣችሁ ትገመግማላችሁ ለማለት ፈልጌ ነው?
 • እ. . .
 • ግን እንዳልከው ብትሰበሰቡ ደግሞ ከዚህም በላይ ልትታመስ ስለምትችል ይሁን፡፡
 • የምን አሽሙር ነው?
 • ሁሉ ነገር እኮ ተቀዛቅዟል፡፡
 • ምን እናድርግ?
 • ኧረ እንደዚህ ስትል ሰው እንዳይሰማህ?
 • ለምን?
 • መሪ ሆነህ ምን እናድርግ ስትል አታፍርም?
 • የቀደሙት እኮ የለኮሱት እሳት ነው የሚያቃጥለን፡፡
 • ሰውዬ ወንበሩ ላይ የተቀመጣችሁት እናንተ እስከሆናችሁ ድረስ ማድረግ ያለባችሁን አድርጉ፡፡
 • ምን ሆነሽ ነው ለመሆኑ?
 • ኢኮኖሚውን እያያችሁት ነው ግን?
 • ምን ሆነ?
 • እየተሽመደመደ ነው፡፡
 • እ. . .
 • ሁሉም ዘርፍ እየተቀዛቀዘ ነው፡፡
 • እሱማ እናውቃለን፡፡
 • እኔ ራሴ ሥራ ከፈታሁ ሰነባበትኩ እኮ?
 • እ. . .
 • ለማንኛውም እኔ ያለ ሥራ መቀመጥ እንደማልወድ ታውቃለህ፡፡
 • ምን አሰብሽ?
 • ያው በአገሪቱ መነቃቃት ላይ ያለው ዘርፍ የኤንጂኦ ቢዝነስ ነው፡፡
 • ሕጉን ስላሻሻልነው ነው፡፡
 • አዎ በየዘርፉ ሰው እየተደራጀ ፈንድ እያሰባሰበ ነው፡፡
 • እዚያም ልትገቢ አሰብሽ?
 • ምን ነካህ ጥሩ ቢዝነስ መሆኑን ደርሼበታለሁ፡፡
 • ምን ለመሥራት አስበሽ ነው ግን?
 • የአንድ ዘርፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ልሆን እኮ ነው፡፡
 • ለነገሩ ትክክል ነሽ፡፡
 • እኔም ማንም ያልነካው ዘርፍ ላይ ለመሥራት አስቤያለሁ፡፡
 • ምን ዓይነት ዘርፍ?
 • በሥራዬ ላይም እንዳየሁት እነሱን አደራጅቼ ለመብታቸው ብከራከር ያዋጣኛል ብዬ አስቤያለሁ፡፡
 • ለማን መብት ነው የምትሟገችው?
 • ለሠርቶ አደሮች!

[ክቡር ሚኒስትሩ ከቀድሞ ጓደኛቸው ጋር ተገናኝተው እያወሩ ነው]

 • እንዴት ነዎት ክቡር ሚኒስትር?
 • እንዴት ነህ ወዳጄ?
 • በጣም ጠፍተዋል?
 • ምን የእኛን ሥራ እያወቅከው?
 • ለመሆኑ ሥራ እንዴት ነው?
 • አገር መምራት በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡
 • በእርስዎ ላይ በጣም ተስፋ ነበረኝ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • እ. . .
 • በደህናው ዘመን ስለአገርዎ የሚነግሩኝ በጣም የሚያስደንቅ ነበር፡፡
 • ለዚያ ነው እኮ አገሬን የማገለግለው፡፡
 • በፊት እኔም እንደዚያ ይመስለኝ ነበር ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ምን እያልክ ነው?
 • አገር ወዳድ ይመስሉኝ ነበር፡፡
 • አይደለህም እያልከኝ ነው?
 • ክቡር ሚኒስትር የሚያወሩትና የሚሠሩት የተለያየ ነው እኮ፡፡
 • እ. . .
 • አገሪቷን እየተመለከታችኋት ነው?
 • ምን ሆነች?
 • ከዚህ በላይ ምን ትሁን?
 • ያው ለውጥ ላይ መንገራገጭ ያለ እኮ ነው፡፡
 • ይተው እንጂ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ምነው?
 • በአፍ ቅቤ መቀባት ብቻ ለማንም ምንም አይጠቅምም፡፡
 • ምን እያልክ ነው?
 • ሕዝቡ ወሬ ሳይሆን ተግባር ነው የናፈቀው፡፡
 • የቻልነውን እያደረግን ነው እኮ፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር ከልብ ካለቀሱ እንባ አይገድም ሲባል አልሰሙም?
 • አሁን ለቅሶን እዚህ ጋ ምን አመጣው?
 • ከልብ ካሰባችሁ የአገሪቱ ችግር ከቁጥጥር ውጪ አይደለም ለማለት ነው፡፡
 • መሪ ብቻውን እኮ በአንድ እጅ እንደ ማጨብጨብ ነው የሚቆጠረው፡፡
 • ሕዝብም መሪውን እንደሚከተል አይርሱ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • እሱስ ልክ ነህ፡፡
 • ለካ አብዛኞቻችሁ ሥልጣን የምትጠሙት ለአንድ ነገር ነው፡፡
 • ለምን?
 • ለራሳችሁ ጥቅም፡፡
 • እኔ እዚህ ጎራ ውስጥ የለሁም፡፡
 • እሱን በወሬ ሳይሆን በተግባር ነው ማሳየት ያለብዎት፡፡
 • እ. . .
 • ለማንኛውም አሁን ሕዝቡ ነቅቶባችኋል፡፡
 • ምንድነው የነቃብን?
 • ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት መሆኑ ገብቶታል፡፡
 • ምን ማለት ነው?
 • ቁማርተኛ!

[ለክቡር ሚኒስትሩ አንድ ባለሀብት ስልክ ደወለላቸው]

 • እንዴት ነዎት ክቡር ሚኒስትር?
 • ማን ልበል?
 • አላወቁኝም ክቡር ሚኒስትር?
 • ማን ነህ?
 • ዘይት አስመጪው ነኝ፡፡
 • አንተ ነፍሰ ገዳይ፡፡
 • ምነው ክቡር ሚኒስትር?
 • እናንተ ናችሁ እኮ እኛን በሕዝብ የምታስጠሉን፡፡
 • ምን አድርገን?
 • ይኼን የጭቃ ዘይት እያመጣችሁ ሕዝቡን በሽተኛ አደረጋችሁት፡፡
 • ይኸው አሁን መንግሥት ሊከለክለው ነው እኮ፡፡
 • ሕዝቡ ካለቀ በኋላ ቢከለክል ምን ያደርጋል?
 • ቢያንስ ለተረፈው መንግሥት መድረሱ ትልቅ ነገር ነው፡፡
 • ምን ፈልገህ ነው ለመሆኑ?
 • ቢዝነስ እንድንሠራ ነዋ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • የምን ቢስዝነስ?
 • አዲስ የሚመጣውን ፈሳሽ ዘይት እንዳስመጣ እንዲያግዙኝ ነዋ፡፡
 • ትንሽ አታፍርም?
 • ምነው ክቡር ሚኒስትር?
 • ያን ሁላ ሰው በዚያ ጭቃ ዘይት በሽተኛ አድርገህ አሁን ደግሞ የቀሩትን በፈሳሹ ልትጨርሳቸው ነው?
 • ክቡር ሚኒስትር ከበፊቱ ሚኒስትር ጋር ይኼን ሥራ ሠርተን ሦስት ቤት ነበር የገዙት፡፡
 • እ. . .
 • እርስዎም ይኼኛውን ዘይት እንዳስመጣ ካደረጉኝ ትልቅ ሽልማት ያገኛሉ፡፡
 • ምን?
 • ፎቅ!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...

የ‹‹ክብር ዶክትሬት›› ዲግሪ ጉዳይ

በንጉሥ ወዳጅነው ‹‹የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ግልጽ የሆነ መመርያ እስኪወጣ ድረስ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት የሚታወጁ ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን ማለቴ ነው። ምን ታወጀ? አንዴ ከዕዳ ወደ ምንዳ አላችሁ፡፡ እሺ? የእሱን ውጤት እየጠበቅን ሳለ ደግሞ... እ...? ኢትዮጵያ ታምርት...

[ክቡር ሚኒስትሩ ሰሞኑን በተጀመረው አገራዊ የምክክር መድረክ ላይ ስለተላለፉ መልዕክቶች በተመለከተ ከባለቤታቸው ጋር እያወጉ ነው] 

እኔ ምልህ? እ... አንቺ የምትይው? አለቃህ በምክክር መድረኩ ላይ ያስተላለፉትን መልዕክት አደመጥክ? አዎ፡፡ የሚገርም እኮ ነው አልተገረምክም? ምኑ ነው የሚያስገርመው? ለኢትዮጵያ የሚበጀውን ምከሩና አምጡ ብለው የምክክር መድረክ እንዲዘጋጅ ካደረጉ በኋላ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት የኬንያው ፕሬዚዳንት ያስተላለፉትን መልዕክት ተመልክተው ባለቤታቸውን በነገር ይዘዋቸዋል]

የኬንያው ፕሬዚዳንት ከሕዝባቸው ለቀረበባቸው ቅሬታ የሰጡትን ምላሽ ሰማህ? እንኳን ምላሻቸውን ቅሬታውንም አልሰማሁም። እንዴት? አልሰማሁማ? የምን ቅሬታ ቀርቦባቸው ነው? ሰሞኑን ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ውድና ቅንጡ አውሮፕላን ተከራይተዋል የሚል ቅሬታ...