አስፈላጊ ግብዓቶች
- 1 ኪሎ ዓሣ፣ የተቆራረጠ
- 1 ኪሎ ድንች
- ½ ኪሎ ጎመን – ቆስጣ
- ½ ኪሎ ስፒናች
- 6 የሾርባ ማንኪያ ፐርስሜሎ
- 2 ሽንኩርት ቺፖሊኒ
- 8 ፍንካች ነጭ ሽንኩርት
- 2 ኩባያ ዘይት
ጨው፣ ቁንዶ በርበሬ
አሠራር
- ጎመን፣ ቆስጣ፣ስፒናች፣ ፐርሰሜሎ፣ ቺፖሊኒ አጥቦ መክተፍና ውኃው እስቲንጠፈጠፍ በፓስታ ማጥለያ ላይ አቆይቶ ጨው መነስነስ፡፡
- ድንች ልጦ መክተፍ፡፡
- ነጭ ሽንኩርት በደቃቁ ከትፎ ዓሣው ላይ ጨውና ቁንዶ በርበሬ ነስንሶ በሳህን ውስጥ ማቆየት፡፡
- የተከተፈው ጎመን ላይ ቀንሶ ድስት ውስጥ ማንጠፍ፡፡ ከዓሣና ከድንቹ እንዲሁም ከነጭ ሽንኩርት ጨምሮ ላዩ ላይ ዘይት ጨምሮ ሙቀቱ 300 ዲግሪ ፋራንሃይት በሆነ ምድጃ ለአንድ ሰዓት ያህል ሳይማሰል አብስሎ ማውረድ፡፡
– ደብረወርቅ አባተ (ሱ ሼፍ) ‹‹ባህላዊ ምግቦች አዘገጃጀት›› (2003)