Saturday, April 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊሕፃናት ጤናማ የኑሮ ዘይቤ እንዲኖራቸው መመሪያ ተዘጋጀ

ሕፃናት ጤናማ የኑሮ ዘይቤ እንዲኖራቸው መመሪያ ተዘጋጀ

ቀን:

ከአምስት ዓመት በታች ያሉ ሕፃናት ጤናማ የወደፊት ሕይወት እንዲኖራቸው ያስችላል የተባለውን መመሪያ ዓለም አቀፍ ጤና ድርጅት ይፋ አደረገ፡፡

ድርጅቱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ ቁጭ የማለት አመልና እንቅልፍን በተመለከተ፣ ከአምስት ዓመት በታች ያሉ ሕፃናትን እንዴት መቅረፅ እንደሚገባ ከሳምንት  በፊት ይፋ ባደረገው መመሪያ እንዳሰፈረው፣ ከአምስት ዓመት በታች ያሉ ሕፃናት ብዙ እንዲጫወቱ፣ ጥቂት እንዲቀመጡ መክሯል፡፡

ሕፃናቱ ቲቪ እያዩ ረዥም ሰዓት እንዳይቀመጡ፣ በመቀመጫ ላይ ለረዥም ሰዓት ታስረው እንዳይቆዩ፣ ለጨዋታ ረዥም ጊዜ እንዲያገኙና ጤናማ እንቅልፍ እንዲተኙ ማድረግ ያስፈልጋልም ብሏል፡፡

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም (ዶ/ር)፣ ጤናማ የሆነ ሕይወትን ለመምራት የአኗኗር ዘይቤ የሚቀርረው ከሕፃንነት ጀምሮ መሆኑን ገልጸው፣ የሕፃንነት ጊዜ የሰው ልጅ ጤናማ ዕድገት የሚጀመርበትና ቤተሰብ የአኗኗር ዘይቤን ለልጆች የሚያስተምርበት በመሆኑ ሕፃናትን አምስት ዓመት እስኪሞላቸው ሥርዓት ማስያዝ ይገባል ብለዋል፡፡

በመመሪያው መሠረት ከአንድ ዓመት በታች ያሉ ሕፃናት በቀን በተለያዩ ጊዜያት አካላቸውን ለማንቀሳቀስ የሚታገዙበት ጊዜ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ በተለይ መሬት ላይ እንዲጫወቱ ማድረግ ከሁሉም በላይ የተመረጠ ነው፡፡ ጨቅላ ሆነው ራሳቸውን ማንቀሳቀስ ያልጀመሩ ሕፃናትን ደግሞ፣ ከእንቅልፋቸው በነቁ ቁጥር ለ30 ደቂቃ ያህል በደረታቸው እንዲተኙና እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ ይገባል፡፡

ከአንድ ሰዓት በላይ በሚታሰር መንበር ላይ ማስቀመጥም ሆነ ማዘል የማይመከር ሲሆን፣ የቲቪም ሆነ የኮምፒውተር ስክሪኖችን እንዲያዩ አይፈቀድም፡፡ እንቅልፍ ባልወሰዳቸው ሰዓት ቢነበብላቸውና ተረት ቢወራላቸው ለአዕምሮ ዕድገታቸው ጠቃሚ ነው፡፡

ከዜሮ እስከ ሦስት ወራት ላሉ ሕፃናት ከ14 እስከ 17፣ ከአራት እስከ 11 ወራት ዕድሜ ላላቸው ደግሞ ከ12 እስከ 16 ሰዓታት ለጥቂት ማሸለብን ጨምሮ የተረጋጋና ያልተረበሸ እንቅልፍ እንዲተኙ ማድረግም ይገባል፡፡

ከአንድ እስከ ሁለት ዓመት ያሉ ሕፃናት በቀን ቢያንስ ለሦስት ሰዓት ያህል የተለያዩ ዓይነት ጨዋታዎችን እንዲጫወቱና ሰውነታቸውን እንዲያንቀሳቅሱ ማድረግ ተመራጭ ነው፡፡ አንድ ዓመት ዕድሜ ላይ ከአንድ ሰዓት በላይ አንድ ቦታ ማስቀመጥም ሆነ ቲቪና ቪዲዮ ማሳየት እንዲሁም የኮምፒውተር ጌም ማጫወት አይፈቀድም፡፡ ሁለት ዓመት ሲሞላቸው በቀን ከአንድ ሰዓት ላልበለጠ ጊዜ ቲቪ ወይም ቪዲዮ ማየት የሚችሉ ሲሆን፣ ቁጭ በሚሉበት ሰዓት ተረት ማንበብ ይመከራል፡፡

ከ11 እስከ 14 ሰዓት ጥሩ እንቅልፍ እንዲተኙ፣ የመተኛና የመነሻ ሰዓታቸውም ሁሌም ተመሳሳይ እንዲሆን ማድረግም ይገባል፡፡

ከሦስት እስከ አራት ዓመት ያሉ ሕፃናትም በቀን በትንሹ ለሦስት ሰዓት ያህል የተለያዩ ጨዋታዎችን መጫወት አለባቸው፡፡ በመቀመጫ ላይ ከአንድ ሰዓት በላይ እንዲቀመጡ ማድረግ አይመከርም፡፡ እንቅልፍ ጊዜያቸው ደግሞ በቀን ከአሥር እስከ 13 ሰዓታት ሊሆን ይገባል፡፡ ከአምስት ዓመት በታች ያሉ ሕፃናት የእንቅልፍ ጊዜያቸው ሳይዛባ ቢያድጉ ጤናማ አካላዊና አዕምሮአዊ ዕድገት ይኖራቸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተወግዘው የነበሩ ሦስቱ ሊቀጳጳሳትና 20 ተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ውግዘት ተነሳ

_ቀሪዎቹ ሦስት ህገወጥ ተሿሚዎች የመጨረሻ እድል ተሰጥቷቸዋል ​ ጥር 14...

በሕወሓት አመራሮች ላይ ተመስርቶና በሂደት ላይ የነበረው የወንጀል ክስ ተቋረጠ

በቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤ,(ዶ/ር)ና ባለፈው ሳምንት በተሾሙት...

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...