Monday, March 27, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየኢትዮጵያ ቀን በዋሽንግተን ዲሲ በ‹‹ታላቁ የአፍሪካ ሩጫ›› ሊከበር ነው

የኢትዮጵያ ቀን በዋሽንግተን ዲሲ በ‹‹ታላቁ የአፍሪካ ሩጫ›› ሊከበር ነው

ቀን:

የጣሊያን መዲና የሮም ከተማ በታሪክ ትልቅ ሥፍራ ከምትሰጣቸው መድረኮች አንዱ ከስድስት አሠርታት በፊት ባስተናገደችው የሮም ኦሊምፒክ በማራቶን ውድድር ሻምበል አበበ ቢቂላ በባዶ እግሩ ሮጦ ያሸነፈው ጎልቶ ይጠቀሳል፡፡ በአበበ ቢቂላ የባዶ እግር ስኬት አንድ ብሎ የጀመረው የኢትዮጵያውያንና የአትሌቲክስ ቁርኝት በትውልድ ቅብብሎሽ አሁን ላይ እንዲደርስ ትልቁን ድርሻ ይይዛል፡፡ እነሆ ዛሬ ደግሞ የኢትዮጵያውን ቀን በዋሽንግተን ዲሲ እንዲከበር ‹‹ታላቁ የአፍሪካ ሩጫ›› በሚል ኢትዮጵያውያንን ከአፍሪካውያን እህት ወንድሞቻቸው ጋር ሊያቆራኛቸው ዝግጅት መጀመሩ ታውቋል፡፡

ባለፈው ሐምሌ 2010 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በሰሜን አሜሪካ በሦስት ከተሞች ተገኝተው፣ ከተፈጠረው ለውጥ ጋር ተያይዞ ከኢትዮጵያውያን ጋር መወያየታቸው ይታወሳል፡፡ በዋሽንግተን በነበረው የጠቅላይ ሚኒስትሩና የኢትዮጵያውያን ፕሮግራም፣ የከተማዋ ከንቲባ መሪያል ባውሰር ቀኑን ‹‹የኢትዮጵያውያን ቀን በዲሲ›› ተብሎ እንዲከበር መወሰናቸውም አይዘነጋም፡፡

ዝግጅት ክፍሉ ለሪፖርተር በላከው መግለጫ፣ ቀኑን በየዓመቱ ማክበር እንዲቻል ‹‹ታላቁ የአፍሪካ ሩጫ›› በሚል መጠሪያ ብዙኃኑን የሚያሳትፍ የጎዳና ላይ ሩጫ በመጪው ሐምሌ 14 ቀን 2011 ዓ.ም. እንደሚያከናውን ሚያዝያ 22 ቀን 2011 ዓ.ም. በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የአፍሪካ ሕብረት ጽሕፈት ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠቱን አስታውቋል፡፡

ውድድሩ ኖቫ ኮኔክሽን በመባል ከሚታወቀው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት፣ ከኢትዮጵያ ኢምባሲ፣ በዋሽንግተን ዲሲ የአፍሪካ ሕብረት ጽሕፈት ቤት፣ በዋሽንግተን ዲሲ የከንቲባ ጽሕፈት ቤትና የአፍሪካ ጉዳዮች ክፍል እንዲሁም ከስቲም ፓወር ጋር በመተባበር ይዘጋጃል፡፡ በውድድሩ የዳያስፖራውን ማኅበረሰብ ጨምሮ ተጋባዥ ታዋቂ የአፍሪካ አትሌቶች እንደሚሳተፉና ምዝገባው ከሚያዝያ 22 ቀን 2011 ዓ.ም.  ጀምሮ በድረ ገጽ ላይ መመዝገብ እንደሚቻል ተገልጿል፡፡

በጋዜጣዊ መግለጫው የተገኙት በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ፍፁም አረጋ እንደተናገሩት፣ ኢትዮጵያውያን ከሌሎች የአፍሪካ እህቶቻቸውና ወንድሞቻቸው ጋር ሆነው ዕለቱን ያከብሩታል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ በአፍሪካ ቀንድ የጀመሩትን የአህጉራትን ግንኙነት የማጠናከር ጥረት ከግንዛቤ ያስገባ እንዲሆንና ትውልደ አፍሪካውያንን ለማቀራረብ የሚያግዝ መሆኑንም መግለጻቸው ታውቋል፡፡ ከሁሉም በላይ  ደግሞ ዝግጅቱ ከአንድ ቀን ሩጫ ያለፈ ፋይዳ እንዳለውና ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሕብረት ምስረታ ላይ የጎላ ሚና እንደተጫወተች ሁሉ በዚህ ዝግጅትም ከሌሎች አፍሪካውያን እህትና ወንድሞች ጋር ለመሆን ‹‹የአብሮነት መነሻ ነው›› ማለታቸው ታውቋል፡፡

‹‹ባለፉት ስድስት አሠርታት አፍሪካውያን አትሌቶች አህጉሪቱ በመልካም መልኩ እንድትጠራ አድርገዋል›› ያሉት በጋዜጣዊ መግለጫው ማብራሪያ የሰጡት በዋሽንግተን የአፍሪካ ሕብረት ጽሕፈት ቤት ዋና ተጠሪ ዶ/ር አሪካና ችሆምቦሪኮ ናቸው፡፡ ተጠሪው አያይዘውም ዝግጅቱም የአፍሪካ ሕብረት በአጀንዳ 2063 ያስቀመጠውን ዳያስፖራው በአፍሪካ የሚኖረውን ተሳትፎ የማሳደግ ጥረት አካል ነው ብለዋል፡፡

የውድድሩ ዋና አዘጋጅ ጋሻው አብዛ (ዶ/ር) ዝግጅቱ ከሩጫው ጎን ለጎን ለሚኖሩበት የአሜሪካ ማኅበረሰብና ለትውልድ አገራቸው የጎላ አስተዋፅኦ ለሚያደርጉ የዳያስፖራው ወገኖች ሽልማት የሚሰጥበት መድረክ ጭምር መሆኑን መናገራቸው በመግለጫው ተካቷል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...