Wednesday, March 22, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ዓባይ ባንክ ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚያደርግበትን ዋና መሥሪያ ቤት ሊገነባ ነው

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

ዓባይ ባንክ አክሲዮን ማኅበር በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገነባውና 26 ወለል ያለውን የዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ለማስገንባት ከቻይና ተቋራጭ ጋር ስምምነት ፈረመ፡፡

ከ827.2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ይደረግበታል የተባለው ይህንን ሕንፃ ሜክሲኮ አደባባይ፣ ሆቴል ዲአፍሪክ በሚገኝበት አካባቢ የሚገነባ ሲሆን፣ በስምምነቱ መሠረት ግንባታው በአራት ዓመታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡

ቻይና ዉ ዪ በተሰኘው ተቋራጭና በዓባይ ባንክ መካከል የተደረገው የግንባታ ስምምነት፣ ዓርብ ሚያዝያ 25 ቀን 2011 ዓ.ም. ሲፈረም፣ የዓባይ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ የኋላ ገሠሠ እንደገለጹት፣ ስምምነቱ የዲዛይንና የግንባታ ሥራውን በማጠቃለል  ተቋራጩ እንዲያከናውን የሚያስችል ነው፡፡

ፕሮጀክቱ ሰማይ ጠቀስ ከሚሰኙ ሕንፃዎች መካከል እንደሚመደብ የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፣ የሕንፃውን ባህሪያት ሲጠቅሱም፣ ዲዛይንና ግንባታን በማጣማር ወይም ‹‹ዲዛይን-ውልድ›› የተሰኘውን የግዥ ሒደት በመከተል መገንባቱ አንዱ ነው፡፡ በመሆኑም ሥራ ተቋራጩ የዲዛይንና የግንባታ ሥራዎቹን ኃላፊነት ሙሉ በሙሉ ተረክቦ የሚያከናውንበት የግንባታ ዋጋም በቁርጥ ዋጋ ትመና መሠረት የተተመነ ነው፡፡ ለወደፊቱ የሚከሰቱ የዲዛይን አለመግባባቶችም ሆኑ የዋጋ ንረቶች ሥጋትን ማስቀረቱም የግንባታ ስምምነቱ ለየት ያለ ባህርይ ነው ብለዋል፡፡

የግንባታ ቦታ ውሱንነትን ባገናዘበ ሁኔታና በአዲስ አበባ ከተማ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስተዋለ የመጣውን የመኪና ማቆሚያ ችግር ለመፍታትም ሕንፃው የራሱ የመኪና ማቆሚያ ይኖረዋል፡፡ በዲዛይኑ መሠረት ሕንፃ ዘመናዊ የሆነና በአንድ ጊዜ ከ150 መኪና በላይ ማቆም የሚችል መካኒካል ፓርኪንግ ሲስተም የሚኖረው እንደሆነም ታውቋል፡፡

ዘመኑ የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ዕድገት በመጠቀም ሕንፃው የግንባታ አስተዳደር ሥርዓት (Building Management System) ያለውና በአሁን ወቅትም በኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እየተሠራበት የሚገኘው የግንባታ መረጃ ሞዴል (Building Information Modeling) ሶፍትዌር ሥራ ላይ የሚያውል መሆኑንም ከፕሬዚዳንቱ ንግግር ለመገነዘብ ተችሏል፡፡

አይይዘውም የሕንፃ ግንባታው ለማጠናቀቂያ የሚሆኑ ግብዓቶች በጥራታቸው ዘመን ተሻጋሪ የሆኑና በከፍተኛ ጥንቃቄ ተመርተው እንዲሁም የውጭ አገር አማካሪዎች ተሳትፈው የሚገነባ በመሆኑ የሕንፃውን ዕድሜ፣ ውበት፣ ጥንካሬና የአጠቃቀም ምቾት ተጠብቆ የሚቆይም ነው ይላሉ፡፡

ዓባይ ባንክ በአሁኑ ወቅት ከ2.3 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያለው ሲሆን፣ 2011 የሒሳብ ዓመት የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸሙን የሚያመላክት መረጃ የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ 11 ቢሊዮን ብር፣ ጠቅላላ ሀብት 14.3 ቢሊዮን ብር መድረሱ ነው፡፡  የደንበኞች ቁጥር 600,000፣ በመላ አገሪቱ የተከፈቱ ቅርንጫፎች ቁጥር 190 የደረሰና 3,253 ሠራተኞች ያሉት ነው፡፡ የዓባይን ባንክ የዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ለመገንባት በጨረታ አሸናፊ ሆኖ ሥራውን የተረከበው China Wu Yi Co.Led በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ግንባታ ሥራዎች ላይ የቆየ ሲሆን፣ በተለይ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ በፋይናንስ ተቋማት እየተገነቡ ካሉ ረዥም ሕንፃዎች መካከል አንዱ የሆነውን የዘመን ባንክ ሕንፃ በመገንባት ላይ ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች