Friday, September 22, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ሦስተኛው የቻይና ንግድ ሳምንት ከ100 በላይ የቻይና ኩባንያዎችን በማሳተፍ ተጠናቀቀ

ተዛማጅ ፅሁፎች

ለሦስት ቀናት የቆየውና ከ100 በላይ የቻይና ኩባንያዎች የተካፈሉበት  በሚሊኒየም አዳራሽ የተካሄደው ሦስተኛው የቻይና ንግድ ሳምንት፣  የኢትዮጵያ ንግድ ማኅበረሰብ አባላት ከቻይና አምራቾችና የቴክኖሎጂ አቅራቢዎች ጋር በቀጥታ መገናኘት የቻሉበትን መድረክ ለማመቻቸት የተሰናዳ የንግድ ትርዒት ነው፡፡

የቀድሞው አምባሳደርና የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ዴኤታ ምስጋኑ አረጋ፣ ሚያዝያ 24 ቀን 2011 ዓ.ም. የከፈቱት የንግድ ትርዒት መቀመጫውን በዱባይ ያደረገው ኤምአይኢ ግሩፕና አጋር ድርጅቱ ፕራና ኢቨንትስ በጋራ በመሆን አዘጋጅተውታል፡፡

በቀላል ኢንዱስትሪዎችና ጨርቃ ጨርቅ፣ የግንባታ ዕቃዎችና ማሸኖች፣ የምግብና መጠጥ ማቀነባበሪያ ቴክኖሎጂ፣ የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎችና ፈርኒቸሮች፣ የኃይልና ብርሃን አማራጭ ምርቶች፣ ውበትና ጤና፣ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች፣ ባዮኬሚካልና የሞተር ተሽከርካሪ ክፍሎችና መለዋወጫዎች በሦስተኛው የቻይና ንግድ ሳምንት ትኩረት የተሰጣቸው ዘርፎች ናቸው፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ጉዳዮች ቋሚ ተጠሪ ደዋኖ ከድር (አምባሳደር)፣ በመክፈቻ ፕሮግራሙ ወቅት ‹‹የቻይና ንግድ በኢትዮጵያ በ35 በመቶ አድጓል፡፡ ነገር ግን ቁጥሩ ምንም ትልቅ ቢመስልም ቻይና ካላት አቅም አኳያ ከዚህ በላይ መሥራት ይጠበቅብናል፡፡ ከቻይና ጋር ካለን ጥሩ ግንኙነት አንፃር ይህ በጣም ጥቂቱ ነው፤›› በማለት ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ለማድረግ ቻይና ቀዳሚ አገር ስትሆን ህንድ ሁለተኛ፣ ጎረቤት አገር ሱዳን ሦስተኛ፣ አሜሪካና አውሮፓም በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ በሰፊው እየመጡ እንደሆነም አምባሳደር ደዋሞ አክለዋል፡፡

የቻይና ንግድ ሳምንት የቻይና ዓለም አቀፍ ንግድና የአንድ ቀበቶ አንድ መንገድ ኢንሼዬቲቭ የገበያ ጥናት ቀዳሚ መድረክ ሲሆን፣ በመካከለኛው ምሥራቅና አፍሪካ ማለትም በኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ጋና፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሩዋንዳ፣ ናይጄሪያ፣ ሳዑዲ ዓረቢያ እንዲሁም ሞሮኮ የሚካሄድ የንግድ ትርዒት ነው፡፡

ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ምቹ አገር በመሆኗ ከግብፅ ቀጥላ በአፍሪካ ሁለተኛ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ለመሆን ችላለች፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች