Wednesday, September 27, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የሀብትና የንብረት ባለቤት ላልሆኑ ዕውቅና ይሰጣል ተብሎ ወቀሳ...

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የሀብትና የንብረት ባለቤት ላልሆኑ ዕውቅና ይሰጣል ተብሎ ወቀሳ ቀረበበት

ቀን:

የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲ ባለቤት ላልሆኑ አጭበርባሪ ግለሰቦች፣ የሀብትና ንብረት ባለቤትነት ምዝገባና ዕውቅና ይሰጣል የሚል ወቀሳ ቀረበበት።

ወቀሳውን የሰነዘረው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኤጀንሲውን የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሰኞ ሚያዝያ 28 ቀን 2011 ዓ.ም. በገመገመበት ወቅት ነው፡፡

የተለያዩ ግለሰቦችና ተቋማት የሌላ ሰውን ሀብትና ንብረት በተጭበረበረ መንገድ ለመያዝ እንደሚጥሩ የገለጸው ቋሚ ኮሚቴው፣ አንዳንድ ግለሰቦችና ድርጅቶች በተጭበረበረ ሰነድ የሌሎችን ሀብትና ንብረት የራሳቸው አድርገው በማቅረብ በኤጀንሲው ምዝገባና የባለቤትነት ዕውቅና ያሚያገኙበት ሁኔታ መኖሩን የተመለከተ መረጃ እንደ ደረሰው ቋሚ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡  

ኤጀንሲው የሰነዶችንና የሰነዶቹን ባለቤት ትክክለኛነት የሚያረጋግጥበት አሠራር ላይም ቋሚ ኮሚቴው ጥያቄ ማንሳቱን፣ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ለቀረበው ወቀሳና ተያያዥ ጉዳዮች ምላሽና ማብራሪያ የሰጡት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ መረሳ ገብረ ዮሐንስ፣ የኤጀንሲው ሠራተኞች በፍተኛ የሥራ ጫና ውስጥ የሚሆኑበትን አጋጣሚ በመጠበቅ፣በሌላ ሰው ሀብትና ንብረት ላይ የባለቤትነት ዕውቅና ለማግኘት እንደሚሞክሩ አምነዋል፡፡

ኤጀንሲው እንዲህ ዓይነት የማጭበርበር ድርጊቶችን በፍጥነት የሚለይበት ቴክኖሎጂ እንደሌለው፣ እንዲህ ዓይነት የማጭበርበር ድርጊቶችን በመደበኛ የማጣራት ሒደት ብቻ ለመለየት እንደሚጥር ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

እንዲህ ዓይነት ጥፋት በኤጀንሲው ሠራተኛ ተፈጽሞ ሲገኝ ሠራተኛው ታግዶ የተሰጠው ማረጋገጫ ወይም ምዝገባ እንደሚሻር የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ በተጭበረበረ ሰነድ የተደረገ ምዝገባ ወይም ማረጋገጫ ሪፖርት ከቀረበበት ወዲያው የሚታረምበት አሠራር መኖሩን አመልክተዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በሌላ ሰው ሀብትና ንብረት ዕውቅና ለማግኘት የሚደረጉ የሰነድ ማረጋገጥ አገልግሎት ሙከራዎች፣ የዜጎችን የንብረት ባለቤት የመሆንና ንብረት የማስተዳደር ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን ስለሚጋፋ ትኩረት እንዲሰጠው አሳስቧል፡፡

* በዚህ ዘገባ ላይ ‹‹ባለጊዜ ደላሎች›› በሚል ተገልፆ የነበረው በስህተት መሆኑን ከይቅርታ ጋር እንገልፃለን  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...