‹‹ይናገራል ፎቶ ለምን አይናገር. . .›› ይላል ገጣሚው፤ አዲስ አበባ በቀዳሚዎቹ ዘመናት በተለይም በመጨረሻው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን (1923-1967) የነበሯት ተቋማት ከፊል ገጽታዎች እነዚህ ፎቶዎች ያሳያሉ፡፡ ንጉሠ ነገሥቱን ጨምሮ የንግድ ሚኒስቴርን፣ የንግድ ኩባንያን፣ መድኃኒት ቤትን፣ ሲኒማ ቤትን፣ አራዳ ፖስታ ቤት በ1928 ዓ.ም. የፋሺስት ወረራ ጊዜ የነበራትን ገጽታ ፎቶዎቹ ይዘዋል፡፡