Thursday, May 30, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊከ320 ሺሕ በላይ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ይፈተናሉ

ከ320 ሺሕ በላይ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ይፈተናሉ

ቀን:

የአገር አቀፍ ፈተናዎች ቀናት ይፋ ሆኑ

የ2011 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈታኞች ቁጥር 322,238 መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት አስታወቀ፡፡

የ10ኛ ክፍል የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ተፈታኝ ተማሪዎች 1,275,465 መሆኑን የገለጸው ዳይሬክቶሬቱ፣ ለ10ኛ ክፍል 2,866 እንዲሁም ለ12ኛ ክፍል 1066 መፈተኛ ጣቢያዎች መዘጋጀታቸውንም አስታውቋል፡፡

- Advertisement -

በፈተናው ጊዜ 13,173 የጣቢያ ኃላፊዎች፣ የወረዳ ተወካይና ርዕሳነ መምህራን፣ 12,407 ሱፐርቫይዘሮች እንዲሁም 41,060 የክፍል ፈታኞች ተሳታፊ እንደሚሆኑም ታውቋል፡፡

የ10ኛ ክፍል የኢትዮጵያ የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከግንቦት 21 እስከ 23፣ የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ከግንቦት 26 እስከ 30፣ እንዲሁም የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከሰኔ 5 እስከ 7 መሆኑም ተገልጿል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የዘንድሮውን የትምህርት ዘመን የአገር አቀፍ ፈተና አፈጻጸምን አስመልክቶ ከወር በፊት ባካሄደው የምክክር መድረክ፣ በየትምህርት እርከኑ ማጠቃለያ ላይ የሚሰጡ ፈተናዎች እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ከተወሰኑ ችግሮች ውጭ በሰላማዊ መንገድ ሲሰጡ የነበረ ቢሆንም፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ለበርካታ ችግሮች እየተጋለጡ መቆየታቸውን የትምህርት ሚኒስትር ጥላዬ ጌቴ (ዶ/ር) ተናግረው ነበር፡፡

ፈተናዎችን በአግባቡ መስጠት ባለመቻሉም፣ ብቁ ትውልድ የማዘጋጀት ሥራው ላይ አስቸጋሪ ሁኔታ ከማስከተሉ በተጨማሪ ከ600 ሺሕ በሚበልጡ መምህራን ላይ የሚያደርሰው የሥነ ልቦና ጫና ከፍተኛ ነውም ብለዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የነበሩ ችግሮች ዘንድሮ እንዳይከሰቱ በፌዴራል ደረጃ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፣ ከሰላም ሚኒቴርና በሥሩ ተጠሪ ከሆኑ ተቋማት ጋር ፈተናው በሰላማዊ መንገድ የሚሰጥበት ሥርዓት ተዘርግቷል፡፡ ሥራውም ተጠናቋል ተብሏል፡፡

የየክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ምክትል ከንቲባዎች፣ የፌዴራልና የክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮችና የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በተካሄደው አገር አቀፍ የፈተና አፈጻጸም ውይይት፣ ፈተናው ከአዲስ አበባ ከወጣ በኋላ በክልልና ከተማ አስተዳደር እንዲሁም በዞንና ወረዳ አስተዳደር ሥር ስለሚሆን ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ሚኒስቴሩ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት የኬንያው ፕሬዚዳንት ያስተላለፉትን መልዕክት ተመልክተው ባለቤታቸውን በነገር ይዘዋቸዋል]

የኬንያው ፕሬዚዳንት ከሕዝባቸው ለቀረበባቸው ቅሬታ የሰጡትን ምላሽ ሰማህ? እንኳን ምላሻቸውን...

የኢትዮ ኤርትራ ሰሞነኛ ሁኔታና ቀጣናዊ ሥጋቱ

“ግንቡን እናፍርስ ድልድዩን እንገንባ” የሚል ፖለቲካዊ መፈክር ጎልቶ በሚሰማበት፣...

ኦሮሚያ ባንክ ከተበዳሪ ደንበኞቼ ውስጥ 92 በመቶ የሚሆኑት አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ናቸው አለ

ኦሮሚያ ባንክ ለደንበኞቹ ከሰጠው ብድር ውስጥ ለአነስተኛና ለመካከለኛ ኢንተርፕራይዞች...

ሽቅብና ቁልቁል!

ጉዞ ከመገናኛ ወደ ሲኤምሲ ጀምረናል። ተሳፋሪዎች የዕለት ጉርሳቸውን መሸፈን...