Thursday, December 1, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፖርትበፋይናንስ እጥረት የፈረሰው ደደቢት እግር ኳስ ክለብ

  በፋይናንስ እጥረት የፈረሰው ደደቢት እግር ኳስ ክለብ

  ቀን:

  በ1983 ዓ.ም. ኢሕአዴግ መንግሥታዊ ሥልጣኑን ከጨበጠ በኋላ ነበር፣ በአዲስ አበባ ስታዲየም እግር ኳስን ማዘውተር የጀመሩት ኮሎኔል አወል አብዱራሂም ክለብ ከማቋቋም ውሳኔ ላይ የደረሱት፡፡

  የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ለመከታተል ሁሌም ወደ ስታዲየም የሚያቀኑት ኮሎኔል አወል፣ በጊዜው የመብራት ኃይል ደጋፊ ነበሩ፡፡ ድጋፋቸውን ወደ ልምምድ ሜዳ በመሄድ በወር የማበረታቻ ድጋፍ እስከማድረግ ደርሰው ነበር፡፡ በሒደት የራሳቸውን ክለብ ለመመሥረት ከውሳኔ ላይ ይደርሳሉ፡፡

  በ1989 ዓ.ም. ላይ ታዳጊዎችን በመመልመልና በተለያዩ ውድድሮች ላይ በማሳተፍ፣ እንዲሁም ውጤታማ ጊዜ በማሳለፍ የደደቢት እግር ኳስ ክለብ የመመሥረቱ ሒደት ዕውን ሆነ፡፡

  ከፕሮጀክት ውድድር ጀምሮ አንደኛ ዲቪዚዮን፣ ከፍተኛ ዲቪዚዮን፣ የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና በማለት ብሔራዊ ሊግ መቀላቀል ቻለ፡፡ በ2002 ዓ.ም. ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ሲያድግ በከፍተኛ የዝውውር ሒሳብ ታላላቅ ተጫዋቾችን ማስፈረም ችሏል፡፡

  ከእነዚህም ፈራሚዎች መካከል እስከ 2010 ዓ.ም. ከክለቡ ጋር መቆየት የቻለው አጥቂው ጌታነህ ከበደ ተጠቃሽ ነው፡፡ ተጫዋቹ በክለቡ ውስጥ እያለ ከፍተኛ ዕውቅናና ዝና ከማትረፉም በላይ ለ16 ዓመታት የተያዘውን የሊጉ የግብ ክብረ ወሰን 2010 ዓ.ም. ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 25 ጎል በማስቆጠር አዲስ ታሪክ ማስፈር ችሏል፡፡

  ደደቢት ከተፎካካሪነት ባሻገር በ2005 ዓ.ም. የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫም አንስቷል፡፡

  ይሁን እንጂ ዘንድሮ መቀመጫውን ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ማዘዋወሩን ካሳወቀ በኋላ በተሳፈበት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እንደ ቀድሞ ነገሮች አልጋ በአልጋ የሆኑለት አይመስልም፡፡ ክለቡ በከፍተኛ የገንዘብ ቀውስ ውስጥ መግባቱ ይነገር ጀመር፣ ተጫዋቾቹም ጨዋታውን ለማቋረጥ እንደሚገደዱ ሲነገር  ቆይቷል፡፡

  ክለቡ በዘንድሮ ውድድር ካከናወናቸው 23 ጨዋታዎች በሦስት ጨዋታ ብቻ አሸንፎ በአንድ አቻ ሲወጣ በ19 ጨዋታ ሽንፈትን ቀምሷል፡፡ ሚያዝያ 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ደደቢት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በላከው ደብዳቤ መሠረት ቀሪ የሊጉን ውድድሮች መቀጠል እንደማይችል አሳውቋል፡፡

  ክለቡ በደብዳቤው ላይ እንደገለጸው፣ ከ2010 ዓ.ም. የውድድር ዘመን ጀምሮ የትግራይ መልሶ ማቋቋም ድርጅት (ማረት) ያፀደቀለትን 25 ሚሊዮን ብር ዓመታዊ በጀቱ ለማግኘት ባለመቻሉ የፋይናንስ እጥረት ቀውስ ውስጥ መግባቱን ገልጿል፡፡

  እንደ ክለቡ ማብራሪያ ከሆነ በውድድር ዓመቱ ማግኘት የተቻለው ሰባት ሚሊዮን ብር ብቻ እንደሆነና ቀሪ 18 ሚሊዮን ብር በወቅቱ ባለመለቀቁ የዕዳ ወለድና ቅጣት ጨምሮ 20 ሚሊዮን ብር ውዝፍ እንዳለበት በይፋ መግለጹን አስታውሷል፡፡

  ‹‹ለከፋ የፋይናንስ ችግርና ዕዳ ተዳርጌያለሁ›› የሚለው ክለቡ የትግራይ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ባደረገለት አምስት ሚሊዮን ብር የበጀት ድጎማ እስካሁን በውድድሩ ላይ መቆየት መቻሉን አመልክቷል፡፡

  በዚህም መሠረት ከ24ተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ጀምሮ በሊጉ መቀጠል እንደማይችል በይፋ አሳውቋል፡፡

  በርካታ ተጫዋቾችን ለማበርከት የቻለውና በፕሪሚየር ሊጉ ከፍተኛ ተፎካካሪ የነበረው ደደቢት ሙገር ሲሚንቶንና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ተከትሎ ከፈረሱ ክለቦች ተርታ ተቀምጧል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...