ዓመታዊው ጥበብ በአደባባይ ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ከተማ፣ ከግንቦት 2 እስከ 9 ቀን 2011 ዓ.ም. እየተካሄደ ነው፡፡ የአዲስ አበባው ጎተ ኢንስቲቲዩት ከአርባን ሴንተርና ከኢትዮጵያውያን ከያንያን ጋር ባዘጋጀው ድግስ አርክቴክቶች፣ ከተማ አቀናጆች፣ ዲዛይነሮች፣ የጨዋታ ኤክስፐርቶች፣ ቀረፃዎች፣ ፎቶግራፎች፣ ቪዢዋል አርቲስቶች፣ ዳንሰኞች፣ ሙዚቀኞች፣ የሰርከስ አርቲስቶች እየተሳተፉ ነው፡፡ ድግሱም በተለያዩ ቦታዎች መስቀል አደባባይ፣ ፒያሳ፣ ቦሌ ኤድና ሞል አደባባይ፣ ኢትዮ ኩባ መናፈሻና ብሔራዊ ቴአቴር በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ፎቶዎቹ የድግሱን ከፊል ገጽታዎች ያሳያሉ፡፡
ፎቶ ጀርመን የባህል ማዕከል