የ2011 ትምህርት ዘመን የአገር አቀፍ ፈተናዎች ማስፈጸሚያ የንቅናቄ ዕቅድ ረቂቅ ሰነድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ የመፈተኛ ጊዜውን ወስኖ የነበረው ትምህርት ሚኒስቴር፣ የፈተናውን ጊዜ ማራዘሙን አስታወቀ፡፡
የአገር አቀፍ ፈተናዎች ኮማንድ ፖስት የፈተና ቀናትንና ዒድ በዓልን አስመልክቶ ባደረገው ስብሰባ የአሥረኛ ክፍል የኢትዮጵያ የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ሰኔ 3፣ 4 እና 5 ቀን 2011 ዓ.ም.፣ የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ሰኔ 6፣7፣10፣ እና 11 እንዲሁም፣ የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ሰኔ 12፣ 13 እና 14 ቀን እንዲሆን መወሰኑን ገልጿል፡፡
ሚኒስቴሩ ከዚህ ቀደም ባስታወቀው መሠረት የሦስቱም ክፍሎች ፈተናዎች ከግንቦት 26 እስከ ሰኔ 7 ቀን 2011 ዓ.ም. ባሉት ቀናት ተከፋፍሎ ይሰጣል፡፡