Saturday, April 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምየደቡብ ሱዳን የአንድነት መንግሥት ተስፋ

የደቡብ ሱዳን የአንድነት መንግሥት ተስፋ

ቀን:

ደቡብ ሱዳናውያንን ከሞትና ከስደት ይታደጋል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የአንድነት መንግሥት፣ ዕውን ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ደቡብ ሱዳንን ለእርስ በርስ ግጭት በዳረጓት ፕሬዚዳንት ሳልቫኪርና በቀድሞ ምክትላቸው ሪክ ማቻር መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ተወግዶ የአንድነት መንግሥት ይመሠረታል የተባለው እስከ ግንቦት 4 ቀን 2011 ዓ.ም. ነበር፡፡

 

ከስምንት ወራት በፊት ኢትዮጵያ በምትመራው የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥት (ኢጋድ) አማካይነት ሁለቱ ተቀናቃኞች ሰላም አውርደው የአንድነት መንግሥት እንዲመሠረት ቀነ ገደብ ቢቀመጥም፣ የአንድነት መንግሥቱ ሊመሠረት አልቻለም፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ተቀናቃኞቹም ከሳምንት በፊት በአዲስ አበባ ላይ በተደረገ ውይይት የአንድነት መንግሥቱ ምሥረታ ለስድስት ወራት እንዲራዘም ጠይቀው ከስምምነት ተደርሷል፡፡

የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኞች እ.ኤ.አ. ከ2013 ወዲህ በሥልጣን ይገባኛል ሳቢያ በገጠሙት ጦርነት በመቶሺዎች የሚቆጠሩ ተሰደዋል በአሥርሺዎች የሚቆጠሩ ሞተዋል፡፡ በአገሪቱ የርስ በርሰ ጦርነቱ በገነነባቸው በመጀመሪያዎቹ አምስት ዓመታት፣ በተደጋጋሚ የተኩስ አቁም ስምምነት ቢደረስም፣ ይኼንን ቃል መፈጸም አልተቻለም ነበር፡፡

  የደቡብ ሱዳን የአንድነት መንግሥት ተስፋ

 

 ለደቡብ ሱዳን ተስፋ ሰላም የሰነቁ የቀጣናው አገሮችንም ሆነ ዓለም አቀፉ መንግሥታትን ተስፋ ያስቆረጠ ነበር፡፡ እ.ኤአ. በ2018 መስከረም በሁለቱ ተቀናቃኝ ወገኖች መካከል የተደረሰው የአንድነት መንግሥትን የመመሥረት ውሳኔ፣ በተያዘለት ቀነ ገደብ ባይጠናቀቅም፣ የብዙዎችን ሕይወት ግን ከሞት ታድጓል፡፡ አካሄዱም ከዚህ ቀደም ከተደረሱ ግን ካልተፈጸሙ የተኩስ አቁም ስምምነቶችም የተሻለ ነበር፡፡

በኢጋድ አስማሚነት ከስምንት ወራት በፊት የተደረሰው ስምምነት እዚህም እዚያም የተከፋፈለውን ጦር ማዋሃድና በአገር ውስጥ የተፈጠረውን የድንበር ጉዳይ መፍትሔ ማስያዝ ነበር፡፡ ብዙ ባይሆንም እዚህ ላይ ጥቂት ጅምር ታይቷል፡፡ ሆኖም ከሁለቱም ወገኖች በኩል ባሉ ችግሮች የተተበተበው የአገሪቱ የሰላም ጉዞ በአገሪቱ ሰላምን የማስፈንንም ሆነ የአንድነት መንግሥት የመመሥረትን ዕቅድ አደናቅፎታል፡፡ የፕሬዚዳንት ሳልቫኪርም ሆነ የሪክ ማቻር የተወሰነውን ለመፈጸም አለመቻል ችግሩን አጉልቶታል፡፡

በሳልቫኪር በኩል የተደረሰውን ስምምነት ለመተግበር በተለይም ሥልጣን ለማጋራት ብዙም አለመራመዳቸው ሲጠቀስ፣ ሥልጣን መጋራቱን አበክረው የሚጠይቁት ሪክ ማቻር ደግሞ ወታደሮቻቸውን ወደካምፕ ለማስገባት የገንዘብ እጥረት አለብን በማለት ዳተኛ ሆነዋል፡፡

የሚቀጥሉት ስድስት ወራት ግን እንዲሁ መምከን እንደሌለባቸው በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግሥታት ልዑክ አስታውቋል፡፡

ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ከአፍሪካ ኅብረትና ከኢጋድ የተውጣጣውና በጁባ መግለጫ የሰጠው ልዑክ፣ በቀጣይ ስድስት ወራት ሁለቱ ተቀናቃኞች የአንድነት መንግሥት እንዲመሠርቱ፣ ከዚህ በኋላም ተጨማሪ ጊዜ እንደማይሰጥ አሳስቧል፡፡

‹‹በግልጽ የምንናገረው ይህ የመጨረሻ ጊዜ ማራዘሚያ ነው›› ያሉት፣ በአፍሪካ ኅብረት የሰላምና ደኅንነት ኮሚሽነር ሳሜል ቼርጉ፣ ሁለቱም ተቀናቃኞች የሚችሉትን ጥረት አድርገውና መስዋዕትነት ከፍለው በኅዳር 2012 ዓ.ም. የአንድነት መንግሥቱን እንዲመሠርቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የልዑክ ቡድኑ ሳልቫኪርና ሪክ ማቻር ልዩነታቸውን አጥብበው ለደቡብ ሱዳናውያን ሰላም እንዲያመጡ እንደሚያግዝ የተገለጸ ሲሆን፣ ስድስት ወሩ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረትና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደቡብ ሱዳናውያን ሕይወት ለመታደግ ያስችላል ተብሏል፡፡

ቀጣዮቹ ስድስት ወራት ባለፉት ስምንት ወራት ሲነሱ የነበሩ ጉዳዮች የሚደገሙበት ሳይሆኑ፣ ቀጥታ ወደተግባር ተገብቶ ፍጻሜው የሚታይበት መሆን እንዳለበት ልዑኩ አስታውቆ፣ በተለይ የደኅንነት አካላትን አንድ ማድረጉ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ እንደሆነ አክሏል፡፡

ከ2013 እስከ 2016 በነበረው የርስ በርስ ውጊያ ምንም እንኳን በየቦታው የተደራጁ ትናንሽ ጁንታዎች ቢኖሩም፣ በዋናነት ሲዋጉ የነበሩት ለሳልቫኪርና ለሪክ ማቻር በየፈርጁ የወገኑ ወታደሮች ነበሩ፡፡ ይህ በዚህ ሁኔታ መቀጠል ስለሌለበትም መከላከያ ሠራዊቱ ወደ አንድ መምጣት አለበት፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ በሁለቱ ወገኖች በኩል መተማመን ማስፈን ግድ ነው፡፡ ስለሆነም በመካከላቸው ያለውን ግንኙነት በማሻሻል በመካከላቸው ያለውን ጥልቅ መጠራጠር ማርገብ ግድ ይላል፡፡

ሁለቱ ተቀናቃኞች አንድ እንዲሆኑ ከውጭ ሆነው የሚረዱ አካላት ሚናም ወሳኝ ነው ተብሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...