Thursday, December 1, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊበኢትዮጵያ ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ ለመታደግ ከመቼውም የበለጠ ርብርብ ያስፈልጋል ተባለ

  በኢትዮጵያ ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ ለመታደግ ከመቼውም የበለጠ ርብርብ ያስፈልጋል ተባለ

  ቀን:

  በሔለን ተስፋዬ

  በኢትዮጵያ ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ ለመታደግ ከማንኛውም ጊዜ የበለጠና የሁሉንም ትኩረትና ድጋፍ የሚሻ ርብርብ እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አስታወቀ፡፡

  የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ73ተኛ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ ለ61ኛ ጊዜ የተከበረውን የዓለም ቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ቀን አስመልክተው  የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ተወካይ አበባ በየነ (ዶ/ር) እንዳሉት፣ ዜጎችን ከከፋ ችግር ለመታደግና በዘላቂነት እንዲቋቋሙ ለማድረግ ማኅበሩ ከአጋሮቹ ጋር እየሠራ ይገኛል፡፡

  ይህም ሆኖ በአገሪቱ ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ ለመታደግ የሁሉም ርብርብ እንደሚያስፈልግ ተወካይዋ ሳይናገሩ አላለፉም፡፡

  የቀይ መስቀል ማኅበር በ2011 በጀት ዓመት ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ 11.9 ሚሊዮን ዶላር በመመደብ እየሠራ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ ከአጠቃላይ ገንዘብ ውስጥ 3.1 ሚሊዮን ዶላሩ ከአጋር ማኅበራት፣ ቀሪው 8.8 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ ከለጋሾች የሚሰበሰብ ነው፡፡

  ማኅበሩ በበጀቱ ግማሽ ዓመት ከአገር ውስጥ ማኅበራት ጋር በመሆን ለ435 ሺሕ የድርቅ ተጠቂዎችና በግጭት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች፣ የእንስሳት መድኃኒትና ምግብ፣ የውኃና ንፅህና መጠበቂያ እንዲሁም የኑሮ መሠረት ማሻሻያ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ለዚህም 2.9 ሚሊዮን ዶላር ወጪ መደረጉ ተገልጿል፡፡

  ከአጠቃላይ ተጠቃሚዎች ውስጥ 240 ሺዎቹ በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት ከቀያቸው የተፈናቀሉ ወገኖች ሲሆኑ፣ 170 ሺዎቹ ደግሞ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ለድርቅ የተጋለጡ ናቸው፡፡

  መንግሥት እ.ኤ.አ. በ2018 መጀመርያ 3.5 ሚሊዮን ጡት ለሚያጠቡና ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት ባወጣው አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ መሠረት ማኅበሩ አንድ ሚሊዮን ዶላር ወጪ በማድረግ ለ53,640 ወገኖች ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

  ማኅበሩ በ2010 በጀት ዓመት 2.7 ሚሊዮን ዶላር ወጪ በማድረግ ለ940,537 ሰዎች የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችና የኑሮ መሠረት ማሻሻያ ድጋፎች ማከናወኑንም አክሏል፡፡

  በኢትዮጵያ የተከሰተውን የዜጎች ግጭትና ከመኖሪያ ቀዬአቸው መፈናቀል በማውሳት፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የበላይ ጠባቂ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ፣ ‹‹ልማት ሊያድግ የሚችለው የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀዬአቸው መመለስ ሲቻል ነው፤›› ብለዋል፡፡

  በክብረ በዓሉ ‹‹በኢትዮጵያ የሰላም ግንባታ ውስጥ ሰብዓዊ ድርጅቶች ያሏቸው ሚና›› በሚል ውይይት የቀረበ ሲሆን፣ ‹‹ሥነ ጥበብ ለሰብዓዊና ለሰላም›› በሚል የኢትዮጵያ ሠዓሊያንና ቀራፂያን ማኅበር አባላት ሥዕሎቻቸውን በተለያዩ ምክንያት ለተጎዱ ዜጎች እንዲውል ለሽያጭ አቅርበዋል፡፡

  የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ አቶ ወንድወሰን ከበደ ‹‹አንድ ሥዕል አንድ ሰው ሲገዛ እንደ ሽልማት መቁጠር አለበት፣ ምክንያቱም ገንዘቡ ለተጎጂ ዜጎች ስለሚውል›› ብለዋል፡፡

  ከ60 በላይ ሠዓሊያን በተሳተፉበት የሥዕል ዐውደ ራዕይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርት ሠዓሊት ደስታ ሐጎስ፣ የውጭ አገር ሠዓሊያን እንዲሁም ሌሎችም እንደተሳተፉ አቶ ወንድወሰን ከበደ አስረድተዋል፡፡ የሚገኘው ገቢም ለተጎጂዎች እንደሚውል አክለዋል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...