Thursday, June 13, 2024

ክቡር ሚኒስትሩ የሰው ሀብት አስተዳደሩን አስጠሩት

[ለክቡር ሚኒስትሩ ስልክ ይደወልላቸዋል]

 

 • ሄሎ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ማን ልበል?
 • አያውቁኝም ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ታዲያ ለምን ደወልክ?
 • ቆይ ይረጋጉ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ምን ይላል ይኼ?
 • ምነው ክቡር ሚኒስትር?
 • በጣም ቢዚ ሰው መሆኔን አታውቅም?
 • ቢዚ ብቻ መሆን ምን ይጠቅማል ብለው ነው?
 • ማን መሆኔን ለመሆኑ አውቀሃል?
 • ምን እያሉ ነው?
 • ክቡር ሚኒስትር እኮ ነኝ፡፡
 • ማዕረግ ብቻውን ምን ያደርጋል ነው እኮ የምልዎት?
 • እ…
 • ማዕረግ በባዶ ኪስ ምንም አይጠቅምም፡፡
 • አልገባኝም?
 • ክቡር ሚኒስትር ማዕረግ ብቻውን የትም አያደርስም፡፡
 • ምን እያልክ ነው?
 • ከአሁኑ ነው ማሰብ ያለብዎት፡፡
 • ምኑን?
 • ማዕረግዎትን የሚያፀናውን ነገር ነዋ፡፡
 • ማዕረጌንማ የሰጠኝ መንግሥት ነው እኮ፡፡
 • የሚያፀኑት ግን እርስዎ ነዎት ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • እንዴት? እንዴት?
 • ከቀድሞዎቹ ሚኒስትሮች አይማሩም እንዴ?
 • ምን ልማር?
 • ለበርካታ ዓመታት ማዕረግዎን ይዘው ለመቀጠል የሚያስፈልግዎት ነገር አለ፡፡
 • ምንድነው እሱ?
 • ገንዘብ፡፡
 • እ…
 • ክቡር ሚኒስትር ማዕረግ እንደ ጤዛ ነው፡፡
 • ምን?
 • አለ ሲሉት ወዲያው ይጠፋል፡፡
 • ምን አልከኝ?
 • መቼም ስለጊዜው ለእርስዎ አላስረዳዎትም፡፡
 • እንዴት ማለት?
 • ማለት ነገሮች የሚለዋወጡበትን ፍጥነት መቼም በሚገባ ይረዱታል፡፡
 • እ…
 • ሁሉ ነገር እኮ በብርሃን ፍጥነት ነው እየተቀያየረ ያለው፡፡
 • እሱማ ያው ለውጥ ላይ አይደለን?
 • ክቡር ሚኒስትር ፖለቲካ ብቻ ምንም አይጠቅምም፡፡
 • እንዴት?
 • ፖለቲካው በኢኮኖሚ መደገፍ አለበት፡፡
 • ምን እያልከኝ ነው ታዲያ?
 • ሥልጣንዎ እንዲፀና ይፈልጋሉ?
 • በሚገባ እንጂ፡፡
 • እንግዲያውስ በአፋጣኝ ይንቀሳቀሱ፡፡
 • እንዴት ነው የምንቀሳቀሰው?
 • ምነው ክቡር ሚኒስትር አይገባዎትም?
 • ምኑ ይግባኝ?
 • በቃ የራስዎን ኔትዎርክ ይፍጠሩ፡፡
 • እ…
 • በፍጥነት ገንዘብ ካልሰበሰቡ ቦታው ላይ መቆየት አይችሉም፡፡
 • እ…
 • ስለዚህ ነቃ ብለው ተፍ ተፍ ይበሉ፡፡
 • ምን ላድርግ?
 • ክቡር ሚኒስትር እሺ ካሉ እኔ ሁሉን ነገር እፈጽመዋለሁ፡፡
 • ማን ልበል አንተን ግን?
 • ባለጊዜ ደላላ!

[ክቡር ሚኒስትሩ የሰው ሀብት አስተዳደሩን አስጠሩት]

 • ፈለጉኝ ክቡር ሚኒስትር?
 • የምን ንቀት ነው?
 • ምነው ካስጠሩኝ ቆዩ እንዴ?
 • የሚነገርህን ለምን አትሰማም?
 • ምን አጠፋሁ?
 • መልስ አትስጠኝ፡፡
 • እ…
 • ለምንድነው ያዘዝኩህን የማትፈጽመው?
 • ምን አዘዙኝ ክቡር ሚኒስትር?
 • ባለፈው ቅጠር ያልኩህን ሰዎች ለምን አልቀጠርክም?
 • ስለእሱ ጉዳይ መነጋገር አለብን ክቡር ማኒስትር፡፡
 • ምንድነው የምንነጋገረው?
 • ሰዎቹ የሚሆኑ አይደሉም፡፡
 • እኔ ጠፋሁ፡፡
 • ምነው ክቡር ሚኒስትር?
 • ምን ማለት ነው?
 • ማለቴ ለቦታዎቹ የሚመጥን ምንም ዓይነት አቅም የላቸውም፡፡
 • አንተን ማን ነው አቅም ፈታኝ ያደረገህ?
 • የተቀመጥኩበት ቦታ ነዋ፡፡
 • ስማ በአንድ ብጣሽ ደብዳቤ ከቦታው ላነሳህ እንደምችል አትርሳ፡፡
 • ምን ማለት ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • የምነግርህን ዝም ብለህ ፈጽም፡፡
 • አልፈጽምም ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • የላኩልህ ሰዎች የወንዜ ልጆች ናቸው እኮ፡፡
 • ለሥራ ወንዝ ምንም አያደርግም፡፡
 • እንዳትሳሳት አለቃችን ለወንዝ ፕሮጀክቱ ምን ያህል እንደመደቡ አታውቅም?
 • እ…
 • ከተማችን በዚህ በወንዝ ፕሮጀክት ምን ያህል እንደምትቀየር ታውቃለህ?
 • እሱስ እውነትዎን ነው በጣም ትቀየራለች፡፡
 • ይኼን እኮ ነው ያልኩህ እኔም፡፡
 • ምንድነው የሚሉኝ?
 • ሰዎቹን ቅጠራቸው፡፡
 • ሰዎቹ ለመቀጠር ማሟላት የሚጠበቅባቸውን አላሟሉም እያልኩዎት እኮ ነው፡፡
 • ቢያንስ አንድ ነገር ያሟላሉ፡፡
 • ምን?
 • ወንዝ!

[ክቡር ሚኒስትሩ ቤት ሲገቡ ሚስታቸውን አገኟቸው]

 • እንኳን ደስ አለህ፡፡
 • ምን ተገኘ?
 • ና ሳመኝ፡፡
 • እኮ ምን አገኘሽ?
 • በጣም ደስ ብሎኛል፡፡
 • በምንድነው ደስ ያለሽ?
 • ምንም አልሰማሁም እንዳትለኝ?
 • ስለምን?
 • ስለዶላሩ ነዋ፡፡
 • ምነው ምንዛሪው ቀነሰ እንዴ?
 • ኧረ ምን ይቀንሳል?
 • ታዲያ ምን ተገኘ?
 • ብሔራዊ ባንክ ለባንኮች ዶላር ሰጥቷል፡፡
 • ጥሩ ነው፡፡
 • እንደ እኔ ደስ አላለህም?
 • በምኑ?
 • ምን ነካህ ሰውዬ?
 • ምን ሆንሽ?
 • ይኼ ሎተሪ እንደወጣልን ነው የሚቆጠረው፡፡
 • እንዴት ሆኖ?
 • ይኼን አጋጣሚ ተጠቅመን ስለምንተኮስ ነዋ፡፡
 • እንዴት አድርገን?
 • መቼ ነው አንተ የምትነቃው?
 • እ…
 • ይኼን አጋጣሚ ተጠቅመን መተኮስ አለብን፡፡
 • በምንድነው የምንተኮሰው?
 • በሀብት ነዋ፡፡
 • እኮ እንዴት?
 • ከፍተኛ ዶላር መቀበል አለብና፡፡
 • ከዚያስ?
 • ከዚያማ የጥቁር ገበያውን እናጧጡፈዋለና፡፡
 • እንዴት አድርገን ነው ግን ዶላሩን የምንቀበለው?
 • በሁሉም ድርጅቶቻችን ስም ነው የምንቀበለው፡፡
 • እ…
 • በዘመዶቻችን ስም በከፈትናቸው ድርጅቶች ሳይቀር ነው የምንቀበለው፡፡
 • ባንኮቹ እኮ ዶላሩን የሚሰጡት በወረፋ አይደል እንዴ?
 • ታዲያ ምን ችግር አለው?
 • እንዴት?
 • አሁኑኑ ለባንኮቹ ደውለህ ንገራቸዋ፡፡
 • ምንድነው የምነግራቸው?
 • እንዲያስቀድሙን?
 • ምኑን?
 • የዶላር ወረፋውን!

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ጋር ተገናኝተው እያወሩ ነው]

 • አለቀላችሁ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ምን?
 • ጉዳችሁ ነው የፈላው፡፡
 • በምኑ?
 • በአዲሱ ፓርቲያችን፡፡
 • አልገባኝም?
 • ለአገራችን የፖለቲካ ችግር ፍቱን መድኃኒት ነው ይዘን የመጣነው፡፡
 • ምን ዓይነት መድኃኒት?
 • የብሔር ፖለቲካ ማርከሻ  ነዋ፡፡
 • እ…
 • ለአገሪቱ የሚጠቅመው የዜግነት ፖለቲካ ነው፡፡
 • መስሎህ ነው? እሱን በምርጫ እናየዋለን፡፡
 • እንደ ድሮው የሚፍረከረክ ፓርቲ እንዳይመስልዎት፡፡
 • የእኛ አገር ተቃዋሚዎችን እኮ እናውቃቸዋለን፡፡
 • እንዳይሸወዱ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • በደንብ ነው የምንተዋወቀው ስልህ?
 • ሰባት ፓርቲዎች ራሳችንን አክስመን ስለመሠረትነው በጣም ጠንካራ ነው፡፡
 • እሱን ምርጫው ይለየዋል፡፡
 • ስነግርዎት እናንተ በከፍተኛ ኪሳራ ነው የምትጨርሱት፡፡
 • ምነው ጉራ አበዛህ?
 • የሕዝቡን አቀባበል አየነዋ፡፡
 • በቅርቡ እኛም አዲስ ስትራቴጂ ይዘን እንመጣለን፡፡
 • ምን ዓይነት ስትራቴጂ?
 • አዲሱ ፓርቲያችሁን የምናደርገውን እናውቃለን፡፡
 • ምን ልታደርጉት?
 • እናከስመዋለን!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...

የ‹‹ክብር ዶክትሬት›› ዲግሪ ጉዳይ

በንጉሥ ወዳጅነው ‹‹የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ግልጽ የሆነ መመርያ እስኪወጣ ድረስ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት የሚታወጁ ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን ማለቴ ነው። ምን ታወጀ? አንዴ ከዕዳ ወደ ምንዳ አላችሁ፡፡ እሺ? የእሱን ውጤት እየጠበቅን ሳለ ደግሞ... እ...? ኢትዮጵያ ታምርት...

[ክቡር ሚኒስትሩ ሰሞኑን በተጀመረው አገራዊ የምክክር መድረክ ላይ ስለተላለፉ መልዕክቶች በተመለከተ ከባለቤታቸው ጋር እያወጉ ነው] 

እኔ ምልህ? እ... አንቺ የምትይው? አለቃህ በምክክር መድረኩ ላይ ያስተላለፉትን መልዕክት አደመጥክ? አዎ፡፡ የሚገርም እኮ ነው አልተገረምክም? ምኑ ነው የሚያስገርመው? ለኢትዮጵያ የሚበጀውን ምከሩና አምጡ ብለው የምክክር መድረክ እንዲዘጋጅ ካደረጉ በኋላ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት የኬንያው ፕሬዚዳንት ያስተላለፉትን መልዕክት ተመልክተው ባለቤታቸውን በነገር ይዘዋቸዋል]

የኬንያው ፕሬዚዳንት ከሕዝባቸው ለቀረበባቸው ቅሬታ የሰጡትን ምላሽ ሰማህ? እንኳን ምላሻቸውን ቅሬታውንም አልሰማሁም። እንዴት? አልሰማሁማ? የምን ቅሬታ ቀርቦባቸው ነው? ሰሞኑን ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ውድና ቅንጡ አውሮፕላን ተከራይተዋል የሚል ቅሬታ...