Saturday, September 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በውኃ ታሪፍ ላይ ጭማሪ አደረገ

 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በውኃ ታሪፍ ላይ ጭማሪ አደረገ

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በውኃ ታሪፍ ላይ ጭማሪ አደረገ፡፡ የውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የደንበኞች አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሞገስ አርጋው ለቅርንጫፎች በጻፉት ደብዳቤ፣ አዲሱ ታሪፍ ከመጋቢት 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን አስታውቀዋል፡፡

አዲሱ ታሪፍ ሰባት መደቦችን የያዘ ሲሆን፣ በወር ከሰባት እስከ 40 ሜትር ኩብ የሚጠቀሙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ ጭማሪ አላደረገም፡፡

ነገር ግን ከ41 ሜትር ኩብና ከ500 ሜትር ኩብ በላይ ውኃ በሚጠቀሙ ላይ ከ130 በመቶ እስከ 161 በመቶ የዋጋ ጭማሪ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡

አቶ ሞገስ በጻፉት ደብዳቤ አዲሱ ታሪፍ በበጀት ዓመቱ ከመጋቢት 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ወይም በቢል ወቅት አቆጣጠር፣ ከጥር 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኑን ገልጸዋል፡፡

‹‹ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች በዚህ ታሪፍ ላይ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች ተገቢውን ግንዛቤ መያዛቸውን በማረጋገጥ፣ በአፈጻጸም ላይ ክፍተት እንዳይኖር ተገቢው ጥንቃቄ እንዲደረግ ጭምር አስታውቃለሁ፤›› ሲሉ አቶ ሞገስ በደብዳቤ አስታውቀዋል፡፡

ነገር ግን የውኃና የፍሳሽ ባለሥልጣን የውኃ ታሪፍ ጭማሪ ስለማድረጉ በይፋ ባለመግለጹ፣ ክፍያ ለመፈጸም በሚሄዱና በክፍያ ሰብሳቢ ሠራተኞች መካከል አለመግባባት እየተፈጠረ መሆኑ ተስተውሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በውኃ ታሪፍ ላይ ጭማሪ ለማድረግ ካቀደ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ የአስተዳደሩ ካቢኔ በ2010 በጀት ዓመት አጋማሽ የታሪፍ ጭማሪ እንዲደረግ ቢወስንም፣ በወቅቱ በሥልጣን ላይ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አስተዳደሩ የውኃ ሥርጭቱንና አገልግሎቱን ሳያሻሽል ጭማሪ ማድረግ የለበትም በማለት አግደውት ነበር፡፡

ነገር ግን አሁንም ቢሆን አስተዳደሩም ሆነ ባለሥልጣኑ የውኃ አቅርቦቱንም ሆነ ሥርጭቱ ሳይስተካከል የታሪፍ ጭማሪ ማድረጋቸው፣ ለጉዳዩ ቅርበት ላላቸው ባለሙያዎች አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኗል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በቀን አንድ ሚሊዮን ሊትር ውኃ ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን እየተመረተ የሚገኘው ከ520 ሺሕ ሜትር ኩብ ውኃ አይበልጥም፡፡ ይህንንም ውኃ ለተጠቃሚዎች ለማድረስ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥና የቴክኒክ ችግር እንቅፋት እየሆነ አቅርቦቱን እያስተጓጎለ ነው፡፡

የታሪፍ ጭማሪውን በተመለከተ የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ አስተያየት እንዲሰጡ የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...