Wednesday, March 22, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ብሔራዊ ባንክ ለንግድ ባንክ 200 ሚሊዮን ዶላር ለቀቀለት

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

መንግሥት ከውጭ ምንዛሪ እጥረት ጋር ተያይዞ ለግል ባንኮች ለማቅረብ ካቀደው 100 ሚሊዮን ዶላር በተጨማሪ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም 200 ሚሊዮን ዶላር እንደተለቀቀለትና ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ዘርፎች የውጭ ምንዛሪ መስጠት መጀመሩ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለንግድ ባንክና ለ16 የግል ባንኮች በጥቅሉ 300 ሚሊዮን ዶላር ለማቅረብ ወስኖ፣ በቅድሚያ ለንግድ ባንክ የፈቀደውን የውጭ ምንዛሪ መልቀቁን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ከመንግሥት የተፈቀደውን የውጭ ምንዛሪ ቅድሚያ ይሰጣቸው ተብለው ለተለዩ ዘርፎች ውጭ ምንዛሪ መስጠት ጀምሯል፡፡ ቅድሚያ ያገኛሉ ከተባሉት  ውስጥ የፋርማሲቲካል፣ የማኑፋክቸሪንግ፣ የፋብሪካ ጥሬ ዕቃዎችና ኬሚካሎች፣ የእርሻ ግብዓቶችና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

የግል ባንኮች 100 ሚሊዮን ዶላር እንደሚቀርብላቸው ከመገለጹ በፊት የተፈቀደለትን 200 ሚሊዮን ዶላር እጁ ያስገባው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣  ለውጭ ምንዛሪ ፈላጊዎች መስጠት መጀመሩ ታውቋል፡፡

የውጭ ምንዛሪ ጠያቂዎች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሁን የውጭ የሚያከፋፍልበትን አሠራር  በአግባቡ ሊያሳውቀን ይገባል እያሉ ሲሆን፣ የግል ባንኮችም የሚለቀቅላቸውን የውጭ ምንዛሪ በትክክል ለሚፈለገው ዓላማ ለማዋል በግልጽ የሚታወቅ አሠራር ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው የሚል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ለግል ባንኮች የተፈቀደው 100 ሚሊዮን ዶላር በቅርቡ ይለቀቃል ተብሎ እየተጠበቀ ሲሆን፣ ብሔራዊ ባንክ ከውጭ ምንዛሪ አፈቃቀድ ጋር ተያይዞ ተግባራዊ መሆን አለበት የተባለውን አሠራር የሚያሳየውን ዝርዝር መረጃ የግል ባንኮች እየተጠባበቁ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡  

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች