Saturday, June 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየኤርፖርቶች ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ የመቐለ ከተማ ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሾሙ

የኤርፖርቶች ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ የመቐለ ከተማ ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሾሙ

ቀን:

የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅትን ለረዥም ዓመታት ያገለገሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ቴዎድሮስ ዳዊት፣ የመቐለ ከተማ ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሾሙ፡፡

የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅትን ለ15 ዓመታት ያህል ያገለገሉት አቶ ቴዎድሮስ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በምህንድስና፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ ከግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ በንግድ አስተዳደር አግኝተዋል፡፡

አቶ ቴዎድሮስ በኤርፖርት ኦፕሬሽንና መሠረተ ልማት ክፍል ያገለገሉ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በ2010 ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው አገልግለዋል፡፡ በ2013 የቀድሞ የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩትን አቶ ሽፈራው ዓለሙን ተክተው ድርጅቱን ሲመሩ ቆይተዋል፡፡

በአቶ ቴዎድሮስ አመራር የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ከፍተኛ ስኬት እንዳስመዘገበ ባልደረቦቻቸው ይመሰክራሉ፡፡ የተለያዩ አዳዲስ የክልል ኤርፖርቶች እንደተገነቡና በነባር ኤርፖርቶች የማስፋፊያ ሥራዎች እንደተከናወኑ ገልጸው፣ ግዙፍ የሆነው የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ማስፋፊያ ፕሮጀክት የተካሄደው በእሳቸው አመራር እንደሆነ አስታውሰዋል፡፡

አቶ ቴዎድሮስ በአሁኑ ወቅት ከኤርፖርቶች ድርጅት ረዥም ዕረፍት የወሰዱ ሲሆን፣ በቀጣይ ከመቐለ ከንቲባ አቶ አርዓያ ግርማይ ጋር አብረው እንደሚሠሩ ተገልጿል፡፡ አቶ አርዓያ ግርማይ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር እንደነበሩ ይታወሳል፡፡

አቶ ቴዎድሮስ ፈቃድ ሲወጡ የአዲስ አበባ ኤርፖርት ዳይሬክተር አቶ ጌታነህ አደራን ወክለው እንደሄዱ ታውቋል፡፡ በቋሚነት የሚተካቸው ኃላፊ ማን እንደሆነ አልታወቀም፡፡ ምንጮች ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ አዲሱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የአቪዬሽን ቡድን ሊሾም እንደሚችል ይጠበቃል፡፡

የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት በሚኒስትሮች ምክር ቤት አዋጅ እ.ኤ.አ. በ2017 የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን ቡድን መቀላቀሉ ይታወቃል፡፡ ድርጅቱ በዋነኛነት ኤርፖርቶችን የመገንባትና ማስተዳደር ሥራ ያከናወናል፡፡ በቀጣይ በሌሎች የአፍሪካ አገሮች ኤርፖርቶች ግንባታ፣ ጥገናና አስተዳደራዊ ሥራ ለመሳተፍ በዝግጅት ላይ ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አያሌ የውኃ “ጠርሙሶች”ን በጫንቃ

መሰንበቻውን በአይቮሪ ኮስት መዲና አቢጃን የምትኖር አንዲት ሴት፣ በሚደንቅ...

ወልቃይትን ማዕከል ያደረገው የምዕራባዊያን ጫና

በትግራይ ክልል የተከሰተው የዕርዳታ እህል ዘረፋ የዓለም አቀፍ ተቋማት...

ከቀጣዩ ዓመት በጀት ውስጥ 281 ቢሊዮን ብሩ የበጀት ጉደለት ነው ተባለ

ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት...