Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየኢትዮጵያ ዝግጅትና የዶሃ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሥጋት

የኢትዮጵያ ዝግጅትና የዶሃ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሥጋት

ቀን:

በምዕራብ እስያ የምትገኘው ኳታር በነጃጅ ምርቶቿ ብቻ ሳይሆን በበረሃማነቷም ትታወቃለች፡፡ የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (አይኤኤኤፍ) 2019 የዳይመንድ ሊግ ውድድር መክፈቻን ከሳምንት በፊት አስተናግዳለች፡፡ በነሐሴ ወር መጨረሻ ደግሞ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ለማስተናገድ ዝግጅቷን አጠናቃ እንግዶቿን በመጠባበቅ ላይ ትገኛለች፣ መዲናዋ ዶሃ፡፡

በበረሃማዋ ዶሃ ከተማ በነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ እንደሚከናወን በሚጠበቀው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሜዳሊያ ሠንጠረዡ ከሚጠበቁ አገሮች ትጠቀሳለች፡፡ ይሁንና ከአስተናጋጇ ዶሃ አየር ንብረት ጋር ተያይዞ ለኢትዮጵያውያን አትሌቶች አስቸጋሪ ስለሚሆን፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከወዲሁ አየር ፀባዩን ታሳቢ ያደረገ ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባው አንጋፋዎቹ የብሔራዊ ቡድን አሠልጣኞች ይናገራሉ፡፡

እንደ አሠልጣኞቹ ከሆነ፣ ኢትዮጵያ ውጤት ከምታስመዘግብባቸው ውድድሮች መካከል የአምስትና የአሥር ሺሕ ሜትሮች ይጠቀሳሉ፡፡ አንደሚታወቀው የረዥም ርቀት ውድድሮች ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተለይም በአወዳዳሪነት የሚታወቁ አገሮች ‹‹ስፖንሰር አናደርግም›› በሚል ርቀቶቹ ትኩረት እንዳያገኙ በመደረጉ ምክንያት ብዙዎቹ አትሌቶች ፊታቸውን ወደ ጎዳና ላይ ውድድሮች በማዞራቸው የቀድሞ ተፎካካሪ አትሌቶችን ማግኘት አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡ 

ከብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የዝግጅት መርሃ ግብር መረዳት እንደሚቻለው ከሆነ፣ የረዥም ርቀት አትሌቶችን መርጦ ከወዲሁ ዝግጅት ለማድረግ፣ ለሻምፒዮናው የሚያስፈልገውን ሚኒማ ለማሟላት የትራክ ውድድሮችን ማግኘት የግድ እንደሚል፣ ተቋሙ ለዚህ ሲባል በማናጀሮች አማካይነት ሙሉ ወጪውን ችሎ በሆላንድ ሄንግሎ ከሐምሌ 15 እስከ 17 ባለው ጊዜ ውስጥ ማጣሪያዎችን እንደሚያደርግ ነው፡፡ አንጋፋዎቹ አሠልጣኞች ግን ምንም እንኳን ችግሩ ከአቅም በላይ ቢሆንም ቀሪው የዝግጅት ጊዜ ለበረሃማዋ ዶሃ የአየር ፀባይ በቂ እንደማይሆን ሥጋታቸውን ይገልጻሉ፡፡ በማሳያነትም ከዚህ በፊት በኬንያ ሞምባሳ በተካሄደው የዓለም አገር እቋራጭ ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ምን ያህል ተቸግረው የነበረ መሆኑን ያስታውሳሉ፡፡

ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ለ48ኛ ጊዜ ያካሄደው ፌዴሬሽኑ፣ ቀጣዩ የዶሃ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና እንደ መሆኑ ተሳትፎውን በሚመለከት በሥራ አስፈጻሚ ደረጃ እየተነጋገረበት መሆኑ የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኩባንያ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ባንኮች ውጤታማነት

የጠቅላላ ጉባኤ፣ የጥቆማና ምርጫ ኮሚቴ፣ የተቆጣጣሪ ቦርድ፣ የዳይሬክተሮች ቦርድና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...