የአንድ መቶ ሠላሳ ሁለት ዓመት ዕድሜ ያላትን የአዲስ አበባ ከተማ ለማስዋብ፣ በተለይ የወንዞች ዳርቻዎችንና ሌሎች ተያያዥ መናፈሻዎችን ለማልማት ፕሮጀክት ተነድፎ በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ‹‹ገበታ ለሸገር›› የተሰኘውና በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ የተወጠነውን ዕቅድ ዕውን ለማድረግ ባለፈው እሑድ (ግንቦት 11 ቀን 2011 ዓ.ም.) የእራት ምሽት ተካሂዷል፡፡ ቦታውም አዲስ አበባን በመሠረቷት ዳግማዊ ምኒልክ ቤተ መንግሥት (እንቁላል ቤት) አጠገብ በሚገኘው ግብር ቤት ውስጥ ነው፡፡ ከ200 በላይ ግለሰቦች፣ የውስጥና የውጭ ተቋማት የመቀመጫ ቦታ በመግዛት በእራት ምሽት የተገኙ ሲሆን፣ አብረዋቸውም ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴና ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይም ታድመዋል፡፡ በባህላዊ ሥርዓት በአገር ትውፊት መለከት እየተነፋ፣ ነጋሪት እየተገሰመ ታዳሚዎቹ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አጋፋሪነት ወደ እልፍኙ ገብተዋል፡፡ ፎቶዎቹ የሁነቱን ከፊል ገጽታ ያሳያሉ፡፡
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -
ፌርማታ ፅሁፎች
ትኩስ ፅሁፎች
- Advertisement -
- Advertisement -